
አስናቀ እንግዳ
ገና ከጠዋቱ፡ ጎህ እንደቀደደ፡ ገና በማለዳ
ከቆላ ከደጋ ተሸክሞ ዕዳ
ከደቡብ ከሰሜን
ከምዕራብ ከምሥራቅ ዘልቆ በመደዳ
ለሀገሩ ለቀዬው ሰው እንዳይሆን ባዳ
አበው ያወረሱት ታሪክ እንዳይጠፋ
መላውን ዕድሜውን ያለ ቀና ደፋ
ሀሰትን ኮንኖ፡ ሀቅን ይሚያፋፋ
ምዝበራን ተጋፍጦ፡ ለሕዝብ የተዋጋ
አልገዛም ያለ ላምባገነን መንጋ
ሕይወቱን አስተምሮ፡ ሕይወትን የኖረ
ንዋይ፡ ሀብት፡ ዝና ከቶ ያላፈቀረ
የዕድሜ ባለጸጋው ጀግናው የእንግዳ ልጅ
ይድረስህ ምስጋና ከዚህ ካሲምባ ደጅ
ከዘመድ ከወዳጅ።
ያገር ፍቅር ስሜት ውስጡን እየበላው
የወገኑ ብሶት እያብከነከነው
የሰንደቁ ክብር እያንገበገበው
ኢትዮጵያ ታሪኳ ተከብሮ እንዲኖር
አንድነቷ ጸንቶ እንዲሆነን ማገር
ሉዓላዊነቷ ጸንቶ እስከዘላለም
የሕዝቧ አንድነት እንዲኖር እስካለም
ታግሎ ያታገለ፡ መካሪ የረቀቀ
ከቶ ወዴት አለ? እንዳተ አስናቀ። (ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply