ኢትዮጵያ አገራችን በዘመኗ ሁሉ ብዙ ፈተናዎችን አሳልፋለች።አሁን የገጠማት በዓይነቱም ሆነ በብዛቱ በወርዱም ሆነ በቁመቱ ዘመናት ከደቀኑባት ሁሉ የተለየ ነው።ከዚህ ውስጥ አንዱ ሕዝቦቿ ጎራ ለይተው በጎጥ ተቧድነው፣ ዘረኞች እር በርሳቸው እንዲፋጁ የደገሱላት የመጠፋፋት ድግሥ ነው። ለዚህ ዕኩይ ግባቸው የመስዋዕት ጠቦት ያደረጉት ደግሞ ዐማራውን ነው። ወደ ተሻለና የሁሉም ዕኩልነት የተረጋገጠባት ዴሞክራሲያዊት አገር እንደመመሥረት እና ሁኔታዎችም ይህንኑ ፈቅደውላቸው እያለ ወደ ኋላ ቀር የዘርና መንደር ናፋቂነት የወሰዱን ዘረኞች፣ በሕዝባችን ላይ የፈጸሙትን የግፍ ዓይነት ዘርዝሮ ለመግለጽ አዳጋች ነው። ይህንን ኢሰብአዊ ወንጀል ለመፋረድና ፍትሕ ለሁሉም በዕኩል እንዲደርስ ወንጀለኞችን በፍትህ አደባባይ ለመፋረድ ሕዝቡ ሙሉ ዝግጅቱነቱን በአደባባይ እየገለጠ ነው።
ይህ ብቻ ሳይሆን፣ ዘመንና ወቅትን እየጠበቁ ጊዚያዊ ጉልበት ያገኙ፣ ጉልበት አልባዎችን እንዳይበቀሉ እና ይህ ዕውደት እንዳይቀጥል የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እንዳለበት የምዕላተ-ሕዝቡ አቋም እየሆነ ነው። ሁሉም በእቅሙ ሳይታበይ በፍትሕ እንዲዳኝ፣ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ ሞትና ግድያ ያለእዳቸው በማንነታቸው ብቻ በተጨፈጨፉት ዐማራ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ያብቃ፤ ለዚህም ወንጀለኞች በሕግ አደባባይ ይዳኙ፤ የሚሉ ድምፆች አድማስ አድማስ እያስተጋቡ ነው። «ዓይን ያጠፋ፣ ዓይኑ ይጥፋ» የሚለው ብሂል ፣ወደ በቀልና ወደ እማያቋርጥ ተካታታይ የእልቂት አዙሪት ስለሚከት፣ ለሕዝባችንም የጋራ መፃዒ ዕድል አዎንታዊ ጎሕ ስለማይቀድ፣ከመጠፋፋቱ አዟሪት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መውጣት ይኖርብናል። ይህን ዘመኑ የሚዋጀውን የሰለጠነ መንገድ በመከተል የተበደሉና የተገፉ ወገኖች ፍትህና ርትዕ ሊያገኙ የሚችሉበትን የአሠራር ጎዳና መከተል ተገቢ እንደሚሆን ድርጅታችን የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በጽኑ ያምናል።
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Mulugeta Andargie says
ቂቂቂቂ!!! በኣዴን ቀረና ሌላ ብቅ ኣለ እንዴ??? ኣልሰሜ እንዴት ኣደርሽ?? ግድየለም ዘራችሁን ቀስ ብለን እንቋጠራለን፣ እስቲ ስማችሁን ኣስተዋውቁን!!