![](https://www.goolgule.com/wp-content/uploads/2015/04/ANAASO-Blue.jpg)
በዚህ ባሣለፍነው ሣምንት በኢትዮጵያውያን ላይ በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ የደረሰው እጅግ በጣም ዘግናኝ ጭካኔ የጅምላ ግድያ ማለትም በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ወደ ዕስልምና እንዲቀየሩ ጠይቀዋቸው እምቢ ስላሏቸው ብቻ ግማሾቹን በቢላዋ አንገታቸውን አርደዋቸዋል፡፡ ግማሾቹን ደግሞ በጥይት እራሣቸውን በመምታት ሠላሳ(30) ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በግፍ አይስል (ISIL) ተብሎ በሚጠራው የእስላማዊ አሸባሪ ቡድን ተሰውተዋል፡፡ በደቡብ አፍሪካም እንዲሁ ኢትዮጵያውያን ሰደተኞች ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ ከተሽከርካሪ ጐማ ጋር በማሰር ሦስት ኢትዮጵያውያን በእሣት ተቃጥለው እንዲሞቱ ተደርጓል፡፡ በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውን ስደተኞችን በእሣት ያቃጠሉት የደቡብ አፍሪካ ጥቁር ዜጐች ናቸው፡፡ በሁለቱም አገሮች የደረሰው አሠቃቂው የኢትዮጵያውያን ጅምላ ሞት ምከንያት ስር መሠረቱ ቁጥጥር ያጣው የአገሪቱ ሕዝብ ስደት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ከየትኛውም የአገሪቱ ክልሎች በየቀኑ በጣም ከፍተኛ ሕዝብ በሕገ-ወጥ ደላሎች ከቤታቸው እንዲኮበልሉ እየተደረገ የስደት ገፈት ቀማሽ እንዲሆን ተገዷል፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply