• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ዓለምነህና ጸጋዬ አራርሳ

October 28, 2016 11:05 pm by Editor 1 Comment

ዓለምነህ በአዋዜ ፐሮግራሙ ላይ ጸጋዬ አራርሳ ‹‹ኢትዮጵያዊ ማንነት የለም›› ያለውን ይዞ በለዘበ ቋንቋና በለዘበ ድምጽ ደቁሶታል፤ ብዙ ሰዎች የገባቸው አልመሰለኝም፤ በጉዳዩ የተማረውና የተመራመረው ዶር. ጸጋዬ አራርሶም የገባው አይመስለኝም፤ እስቲ እኔ የገባኝን ልንገራችሁ፡፡

በመጀመሪያ በሁለቱ ሰዎች መሀከል ያለውን የትምህርት ደረጃ ልዩነት ዓለምነህ ራሱ እንዳለው እሱ ‹‹በትምህርት እጅግም አልገፋም›› ጸጋዬ ግን የትምህርቱን ደረጃ ጣራው ላይ አድርሶታል ተብሎ በስሙ ላይ ‹‹ዶክተር›› የሚል የትምህርት ማዕርግ እንዲጨምር አድርጓል፡፡

በትምህርት እጅግም ያልገፋው ሰው በትምህርት ጣራ ላይ በደረሰው ሰው አስተያየት ላይ የሰጠው ትችት የትምህርት ደረጃ የሚባለውንም ሆነ የሁለቱን ሰዎች እውቀትና ብስለት የሚለካ ነው፤ የዓለምነህ ትችት ስለቱ ያረፈው ጸጋዬ የሚልዮኖችን እምነት መካዱ ላይ ነው፤ ጸጋዬ እሱ ኢትዮጵያዊ ማንነት አንደሌለው ብቻ አልተናገረም፤ ማንም ቢሆን ኢትዮጵያዊ ማንነት የለውም በማለትም እምነቱን ለጥጦታል፤ (ምናልባትም ኢትዮጵያዊ ማንንት ባለመኖሩ ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው የለም ብሎ ‹‹ያስብ›› ይሆናል፤ ግን የባሰ ገደል ውስጥ ያስገባዋል!) በጸጋዬ ላይ ያረፈው የዓለምነህ የሀሳብ ጉማሬ ጸጋዬ አንድ ብቻውን ሆኖ የሚልዮኖችን እምነት በመካዱ ላይ ነው፤ አንድ የተማረ ሰው (ያውም ጸጋዬ የሚል ስም ይዞ) ‹‹ኢትዮጵያዊ ማንነት›› የለም ሲል እሱ የካደውን ሌሎች በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችም ከሱ ጋር በክህደት የቆሙለት ያስመስላል፤ በሌላ በኩል ስናየው አንድ የተማረ ሰው ክርስቲያን የሚባል ሃይማኖት የለም ቢል፣ አንድ የተማረ ሰው እስልምና የሚባል ሃይማኖት የለም ቢል … አለማወቅ ብቻ ነው ብለን አናልፈውም፤ ተንኮልም ያለበት መሆኑን ማጋለጥ አስፈላጊ ይሆናል፤ ዓለምነህ እዚህ አልደረሰም፤ ወይም ሊደርስ አልፈለገም፤ ዓለምነህ የሚለው የጸጋዬ ንግግር ብዙ ኢትዮጵያውያንን አቁስሎአል፤ ስለዚህም ይቅርታ መጠየቅ አለበት ነው፡፡

ጸጋዬ ለኢትዮጵያዊ ማንነት የሞቱትን ሁሉ እንደሰደበ አያውቅም ለማለት ያስቸግራል፤ ጸጋዬ የሕግ ምሁር ነው፤ በተለይም በሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮረ ይመስለኛል፤ እሱ እንዳደረገው የራስን ስሜት በአጠቃላይ ሕዝቡ ላይ መጫን፣ ወይም የሱን ክህደት በሕዝብ ላይ መጫን ከባድ ጥፋት ነው፤ ወደዚህ ጥፋት ያደረሰው ሌላ የተሳሳተ እምነት ነው፤ የግለሰብ መብቶች የመብቶች ሁሉ የማዕዘን ድንጋይ ነው፤ ጎሠኞች ከራሳቸው በቀር ግለሰብ አያውቁም፤ ሌላው ሁሉ ጎሣው ነው፤ የጸጋዬ አስተሳሰብ ከጎሠኛነቱ ያገኘው ነው፤ በጎሠኛነት አስተሳሰብ ጎሣ እንጂ ግለሰብ የለም፤ ጸጋዬ ይህንን አስተሳሰብ ወደጎሣ ፖሊቲካ ሲመነዝረው ኢትዮጵያዊ ማንነትን እንዲክድ አደረገው፤ ዶር. ጸጋዬ አራርሳ በአንድ እጁ የኦሮሞን ሕዝብ በሙሉ ጨብጦ በሌላ እጁ ደግሞ የቀሩትን ኢትዮጵያውያን ጨብጦ በሁለቱም ላይ የራሱን የተለያዩና ተቃራኒ እምነቶች ሊጭንባቸው ይሞክራል፤ (ቅዠት እንዳይመስላችሁ!) እንኳን ከዚያ ታች (አንደሚባለው) ከአውስትራልያ ይቅርና ከአዲስ አበባም ቢሆን የእነዚህን ሰዎች አንድ ከመቶ ለማግኘት የሚችል አይመስለኝም፤ መንጠራራቱ ባልከፋ! ሲመለስ በምን ላይ ያርፋል አንጂ! ጸጋዬ የሕግ ምሁር በመሆኑ እንደሚያውቀው የግለሰቦችን መብቶች ይዞ ባልተነሣ ጥቅል እምነት ላይ ተመሥርቶ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ማንነት ላይ ፍርድ መስጠት ‹‹ይህን ያህል ያልተማረው›› ዓለምነህ እንዳለው ስሕተት ነው፤ ጥፋት ነው፡፡

እግዚአብሔር ለሁላችንም ብርሃኑን ያሳየን!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ጥቅምት 2009

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    October 30, 2016 06:31 am at 6:31 am

    __ “ዘመኑ የትብብርና አጋርነት ነው…ኢትዮጵያዊ ማንነት (አንድነት) የሚባል ነገር የለም! ኢትዮጵያዊነት የትግር እና አማራ ነው ለእነ ፓስፖርት ብቻ ነው” የሕግ ምሁር ዶ/ር ጸጋይ አራርሳ…. ድንቅ ቪዥን (ምድረ ደንባራ!) በለው!
    *** ከሁሉ አስቀድሞ እንደተለመደው ጋዜጠኛ ካሳሁን ስቦቃን በጣም አደንቃለሁ አመሠግናለሁ:: በእውነትም በሙያው ተክኗል: አይፈራም! ያለውን አወዛጋቢ ብዥታ : በጥርጣሬ የሚባለውን ሐሚትና ተቃውሞ ሕዝብን በሚያነጋግሩም ሆነ በሚያደናብሩ ሐሳቦችን በሚገርም ሁኔታ እንደወረዱ ያቀርባቸዋል::
    ~~ ዶ/ር ፀጋዬ ረጋሳ ሙያቸውን በተመለከተ የተምታታና የተወሳሰበ ፍላጎትና መሪ ያለው ኦሮሞ ሥርዓቶች ከበደሉት በባሰና በከፋ መልክና ቅርጽ በነጻ አውጭ አመራሮቹ መብዛትና መጓተት አያት ቅድም አያቶቹ ደሙን አፍሶ አጥንቱን ከስክሶ ያቆማትን ኢትዮጵያ እንደጭራቅ ምድር አስበርግገው ከልለውና ከልክለው የበይ ተመልካች ያደርውጉትን ሰብስቦ በማነጋገር በአንድ የሐሳብ ውሳኔ በግልጽ አቋምና በሕግ ማዕቀፍ ለውጭውም ገላጋይ ለውስጡም ደጋፊ ያመች ዘንድ የቤት ሥራው ባልከፋ ነበር ::
    ~~~ የግለሰቡ ችግር የመጣው ከሙያቸውና ከባሕሪያቸው ውጭ የታሪክ ድሪቶ: ሌሎችን የፖለቲካ ተንታኝ (በታኝ) ወይም ታሪክ ገልባጮችንን ላለማስከፋት የተጓዙበት የ5 ደቂቃ መንገድ ሁሉንም በአስቀያሚ መልኩ ገደል ከተውት ሄዱ::
    ” ዘመኑ የትብብር : የአጋርነት ዘመን ነው::” ይህ ማለት ከዚህ በፊትም ጠቅሰውታል “አንድነት” የሚባል ነገር የለም አንድ አደለንም ብለዋል:: እሳቸው እንዳሉት ኢትዮጵያ የትግሬና የአማራ ማንነት ነው:: ዳቦ: ጠላ: ዶሮ: ወጥ: ነጠላና ጋቢ: የአማራና የትግሬ ነው? ለመሆኑ የሌሎችን ሀገር ኦሮሞዎች ባሕላቸውን ምግባቸውን አላውቅም የኢትዮጵያ ኦሮሞዎች በግድ ጋቢ ተጫነብኝ ዶሮ ወጥ ብላ ተብዬ ተገረፍኩ ሲሉ አልሰማሁም አላየሁም ብዙ ጥበበኛ ሸማኔ ለአማራና ትግሬ ሸጦ ግብር ከፍሎ እናንተን እዚህ ያደረሰው ከዚያው ከኢትዮጵያ በተገኘ ፍራንክ እንጂ በአውስትራሊያና አሜሪካ ዶላር አደለም::አራት ነጥብ::
    ** ኦነግ ስም: ባንዲራ ቦታ እየቀያየረ በህወአት /ኢህአዴግ ጥላ ሥር እጅግ በጣም ተጠቃሚ ቡድን ነው ችግራቸው ሥልጣን እንጂ ዓላማቸው አንድና አንድ ነው:: ትብብርና አጋርነት ሥልጣንና መከላከያውን እስክንይዝ አዳርሱን ማለት ነው:: ሜ/ር ጀ አበበ ተክለሃይማኖት ሕገመንግስታችንን ክሚያደንቁልን የኦሮሞ የሕግ ምሁራን ተብለው ከተጠቀሱት ዶ/ር ጸጋዬ ከብዙዎች አሮሞ አንዱ ናችው:: ዶ/ር ጸጋዬ እና ጆቤ እንደ እርሾ ይጠቅመናል ያሉት ሕገመንግስት በጥቅማጥቅም (መደለያ) እንጂ በሙሉ መብት አለመሆኑን አያውቁም? ግን ይህ ነቄ ትውልድ የአድርባይ ቦልጥቀኛ የ43 ዓመት ቁማር ገብቶታል..በቅርቡ ኢትዮጵያ ኬኛ ይላል::
    ** የኦሮሞ ልሂቃን ፓርቲና ባንዲራ አበዛዝ ሳሙናው ጁንዲን ሰዶ” በህወአት ባለሥልጣናት እየተገረፍኩ: እየተሰደብኩና እየተዋረድኩ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ግን ማንነቴ ታውቆ: በቋንቋዬ ተናግሬ: ባሕሌና ማንንቴ ታውቆ ኖሬአለሁ: የኦሮሞን ልጅ ከሌላው ወገኑ እንዳይግባባ በቁቤ ጠርንፎ : ባሕሉን እንዳይወራረስ: እንዳይጋባ ግራ አጋብቶ:ሌላው እንዱስትሪ ሲገነባ ለኦሮሞና አማራ ተከልካዮች እስታዲየምና ቢራ ፋብሪካ ሲገነባ ድመት ሆኖ ኖረ የፌደራል ሥርዓት ሳይገባው ዛሬም በሲቭል ሰርቭስ ሥራ ውስጥ ብዙ የአማራ ልጅ መኖሩ ይቆጨኛል” ይለናል ‘የሕዝብ ዓይንና ጆሮ?’ ነኝ በሚለው ኢሳት ላይ ተጥዶ!! አሁን እንደ ዶ/ሩ እብደት በባህል:በዘፈን: እንጀራና ዶሮ ወጥ:ነጠላና ጋቢ: ትግሬና አማራ ኢትዮጵያዊነት መገለጫቸው ከሆኑ አኤርትራም እኔም ኩታ ገጠም ነኝ ካለችስ? ሚስኪን ኦሮሞስ? ወይ ‘ለትብብርና አጋርነት ብቻ አብሮ ማሸቋለጥ’ ከዚያስ? ዘ ይገርም አሉ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule