• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ምጽዓት

October 24, 2014 07:40 pm by Editor Leave a Comment

“በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፡– ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፤ — የእሥራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤- እነሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል፤ በዚያ ቀን አድንሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም፤ ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም፤ በበእኔ ታምነሃልና ይላል እግዚአብሔር፡፡” ትንቢተ ኤርምያስ 39/15-18

ኑዛዜ ኤርምያስን አነበብሁ፤ጉድ ነው! አንድ የማውቀውን ነገር አረጋግጥሁ፤ ብዙ የማላውቃቸው ነገሮችን አወቅሁ፤ የማውቀው ነገር ሂሳብ የተማረ ሰው ምን ጊዜም ጭፍን ሎሌ መሆን የማይችል መሆኑን ነው፤ ሂሳብ የተማረውን ሰው ለጭፍን ሎሌነት የሚቀጥረው ሰው ግን አንጎሉ የፈረጠ ነው፡፡

የማላውቃቸው ነገሮች ዝርፊያ በየፈርጁ! በቃሊቲ ወህኒ ቤት የትምህርት ቤት የነበረ ሕንጻ ወደ እስር ቤት መለወጡን አይቼ ነበር፤ አሁን ደግሞ የሕዝብ ትምህርት ቤት ለግለሰብ መሸጡን አወቅሁ፤ ጡንቻ ነው እንጂ ትምህርት ምን ዋጋ አለው! ይህ ሁሉ ዝርፊያ፣ ይህ ሁሉ ወንጀል ሲፈጸም ሌላው ሁሉ ጮሆ አቤት ለማለት እንኳን የማይደፍር ሆኖ ነው ወይስ የሕግ አስከባሪ በአገሩ ጠፍቶ ነው? ድፍረቱን አጥፍተውት ከሆነ በከበደ ሚካኤል ብእር ፋሺስቱ የተናገረው ልክ ነበር ማለት ነው፤–

መሬት የሁሉ ነች ባለቤት የላትም!

ኃይለኛ እየሄደ ያስገብራል የትም፤

መሬት ባለቤት ከሌላት ሰዎች አገር የላቸውም ማለት ነው፤ አገር የሌላቸው ሰዎች ዶላር ይዞ ለመጣ ቤታቸውንና መሬታቸውን እንዲያስረክቡ ይገደዳሉ፤ ሕገ መንግሥቱ መሬት የሕዝብና የመንግሥት ነው ስለሚል ባለዶላር ወይም ባለሀብት ሕዝብ የሚለውን ይተካል።

ኑዛዜ ኤርምያስን ያነበበ የወያኔ ባለሥልጣኖችን ራቁታቸውን ያያቸዋል፤ ካልዋሸ ራሱንም ራቁቱን ቆሞ ያየዋል፤ ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ ደጋግሜ እንዳልሁት ጨቋኝና ተጨቋኝ ተደጋጋፊዎች ናቸው፤ አንዱ ያላንዱ አይኖርም፤ በኑዛዜ ኤርምያስ ላይ ጎልቶ ለሚታየው የጨቋኞቹ ቆራጥነትና ጭካኔ ጉልበቱን ከየት አገኙት ቢባል መልሱ ቀላል ነው፤ ከተጨቋኞቹ ተንጋልሎ ጭቆናን ከመቀበል ችሎታ ነው፤ ድፍረታቸውን አደንቃለሁ፤ ድፍረታቸው ወደወንበሩ ስቧቸው ወጡበትና (ተቀመጡበት እንዳልል አልተመቻቸውም፤) ዘመኑ የፍርሃት፣  እንቅልፍ አጥቶ የመባነን፣ የመደናበር ሆኖባቸዋል፤ የፍርሃት በሽታ ዓይንን ይሰውራል፤ ጆሮን ይደፍናል፤ አቅምን እንዳያውቁ ያደርጋል፤ በዚህ ሁሉ ምክንያት ከማይችሉት ጋር ያላትማል።

ምጽዓት የሚል ግጥም አለኝ፤ ትዝ አለኝ!

ባሳብ ባሕር ዘፍቆ የሰው ልጅ ሲጨነቅ፣

ሃይማኖት ሲራባ ፍልስፍና ሲረቅ፣

ነፍስ እምነትን አጥታ፣ መንምና በችጋር፣

እውነቱ ሲያሳፍር፣ ሲያስጠላ፣ ሲያስመርር፣

ኃይል ክፋት ሲሆን የደካሞች ጭነት፣

ፍቅር ጥምቡን ጥሎ ሲገዛ እንደኩበት፣

ፍርሃት ትእግስት ሆኖ ድንቁርና ኩራት፣

ውርደትም ትሕትና ጮሌነትም እውቀት፣

ትምህርትም ጌጥ ሆነ ያውም የተውሶ፣

ስንፍናም ጨዋነት ሰውነት ረክሶ፣

ማተብ ክርስትና ነጭ ጥምጥም ክህነት፣

ሀብት ብልጽግና ምቾት ትልቅነት፣

ምኞት ተስፋ ሆኖ መቃብርም ኑሮ፣

እንጉርጉሮው ዘፈን፣ ዘፈኑ እንጉርጉሮ፣

ባዳ ሆነ ዘመድ ባለቤቱ እንግዳ፣

ሆድም አምላክ ሆነ አውሬውም ለማዳ፣

ገንዘብ ዳኛ ሲሆን ወንጀል ከሳሽ ሆኖ፣

ግብዝነት ደላው ጽድቅ ተኮንኖ!

ወጣትነት ጫጨ እርጅና እየለማ፣

የኋሊት መገስገስ የጊዜው ዓላማ!

ከራስ በላይ ነፋስ ትልቁ ሃይማኖት፣

ዘረፋን ሲያውጀው ቂም ሲያስረግዝ ጥቃት፣

ዓይን አያይም አሉ፤ ጆሮም አያዳምጥ!

ተለጉሞ አንደበት ሁሉም ይዞታል ምጥ!

በቁንጣን በስካር ጥቂቶች ሲንሩ፣

ብዙዎቹ ደግሞ በረሃብ መንምነው በቁንጫ ሲያርሩ.

የደሀ እንባ ሲጎርፍ መሬቱ ሲሸበር፣

ፍትሕ በሌለው ፍርድ ሚዛኑ ሲሰበር፣

ዝብርቅርቁ ወጣ!

ህይወት ትርጉም አጣ!

ኧረ የት ነው ጉዞው? ዓላማው ምንድን ነው?

ቀድመው የሄዱትን ምነው አናያቸው!

የት ገቡ? የት ጠፉ? ፋና እንኳን አይታይ፤

ብልጭ የሚል የለ፤ ከመሬት ከሰማይ!

መንገዱ ጠበበ ትርምስምሱ በዛ፤

እሪታው ኡኡታው ቀለጠ እንደዋዛ፤

መሬቱም ዓየሩም በክፋት ጠነዛ፤

ጥላቻና ቂሙ በሰፊው ተነዛ፤

እምቢልታው ሲጣራ፣ ነጋሪት ሲያገሳ፣

የአለው ሁሉ ሞቶ የሞተው ሲነሣ፣

ምጽዓት መድረሱ ነው፤ ሊስተካከል ነው ፍርድ፤

በግና ፍየሉ ሊለዩ በገሀድ!

የሚጠየቅ ሰው ቢኖር አንድ ቀላል ጥያቄ መጠየቅ እፈልግ ነበር፡- የዝርፊያው ፉክክር የት ለመድረስ ነው? በአንድ ቤተ ክርስቲያን ወይም መስጊድ ጓሮ ሁለት ሜትር በአንድ ሜትር ክፍል የሬሳ ቤት ለማሠራት? አይ ሰው!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

መስከረም 2007

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Filed Under: Opinions Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule