የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውን እንመሰክራለን(ዮሐ 3፡11)
ከዚህ በፊት በተከታታይ በወጡት ጦማሮች ተዋጊ ፋኖዎች በእነ በላይ ዘለቀ፣ መንገሻ ጀንበሬ፣ ራስ ሀይሉ በለው፣ በበዛብህ ነጋሽና ሌሎችም የየጦር መሪነት፤ አርበኞች ካህናት በእነ ሊቀጠበብት አድማሱ ጀንበሬ፣ መላከ ሰላም አለማየሁ ሻሾና ሌሎችም ካህናት አስተባባሪነት፤ በእነ ክቡር ሀዲስ አለማየሁ፣ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴና ሎችም አርበኞች ደራስያን አስተማሪነትና ቀስቃሽነት እንደዚሁም በእነ ራስ ሀይሉ ተክለሃይማኖት የጦር አማካሪነትና የጣልያንን ምስጢር አውጪነት የተፈፀመውን የጦር ጀብዱና የተገኘውን ድል ጨልፌ አቅርቤአለሁ፡፡ በቀጣይ ጦማሮቼ ደግሞ ሊቀጠበብት አድማሱ ጀንበሬ ከድህረ ጦርነት በኋላ የፈፀሟቸውን ገድሎች ለማሳሰብ አቀርባለሁ፡፡
(የክፍል አንድ ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ
ክፍል ሁለት ሙሉ ጽሁፍ እዚህ ላይ ይገኛል)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
አንተነህ ጌትነት says
ስለ በላይ ዘለቀና ስለ ጫኔ ተረፈ ሲነሳ አንድ ነገር ትውስ ስለለኝ ነው።
በላይ ዘለቀና ጫኔ ሲፎካከሩ ሲፎካከሩ አንድ ቀን በላይ ዘለቀ ጫኔን ይይዛታል። ጫኔ በሴት ስም የምትጠራው በጣም አጭር ስለሆነች ነው ይባላል።
እናም በለይ ዘለቀ አድብቶ ጫኔን ሲይዛት ጀግና ምን ጊዜ ጀግና ነውና
እንደው ዘንጋ ብዬ እንደው ቸላ ብዬ፣
አንበሳ በነብር አይጨክንም ብዬ። ብላ ጫኔ ግጥም ስትገጥም በላይ ዘለቀ የእጁን መሳሪያ ለጫኔ ሰጣት።
አሁን ቢሆን ኖሮ ምላሹ ምን ይሆን ነባር?