• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አሸንዳ/ሻደይ ከሰሜን ኢትዮጵያ እስከ ደቡብ ኤርትራ የሚከበር “የጋራ ጸጋና ህዝባዊ በረከት እንጂ የምንጣላበት፣ እንደ አላቂ ሃብት በድርሻ-ድርሻ የምንካፈለው አይደለም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ

August 21, 2018 07:08 am by Editor 1 Comment

አሸንዳ/ሻደይ/አሸንድየ የሰሜን ኢትዮጵያ ህዝቦች የአንድነትና የወንድማማችነት ህያው ማስረጃ!

በሁሉም አቅጣጫ ያሉትን የሃገራችንን ህዝቦች እንዳይበታተኑ ያስተሳሰሩ፤ እንዳይለያዩ ያጣመሩ፣ እንዳይፈርሱ ያማገሩ በርካታና ጠንካራ ማጎች በሀገራችን ሁሉም ጫፎች በክብር እና በፍቅር እዚም እዚያም አሉ። ህዝቦቻችን በጋብቻ ተዛምደው፣ በማንነት ተዋህደው የኖሩ፣ ያሉና የሚኖሩ ህዝቦች ናቸው።

ልክ እንደ ምስራቁ፣ ደቡቡና ምእራቡ ህዝባችን ሁሉ የሰሜን የሃገራቸን ህዝቦችም በባህል፣ በቋንቋ፣ በዘር፤ በሃይማኖት ወዘተ ተሰናስልው፤ ተዋደውና ተዋህደው የኖሩ፣ ያሉና የሚኖሩ ስለመሆናቸው በርካታ የታሪክ፣ የባህል፤ የእምነት እና የቋንቋ ማስረጃዎች ማቅረብ የሚያስፈልገው ሁነት ሳይሆን በህይወታቸው ውስጥ ከተረበረቡ እልፍ መገለጫዎቻቸው የሚስተዋል ግሩም እውነት ነው።

የዚህ አንድነትና የጋራ ማንነት- የዚህ ዘመንን እንኳ የሚያስገብር ከነፍስ የተሸመነ እውነት ማሳያ ከሆኑ የማህበረሰባችን እሴት ባህሎች ውስጥ ደግሞ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የሚኖሩ የትግራይ፣ የአማራ፣ የአገው፣ የኩናማ እና የኢሮብ ህዝቦች መመሳሰልና መተሳሳርን የሚያሳየው የአሸንዳ/ ሻደይ ክብረ በአል አንዱና ምናልባትም ዋነኛው ነው።

የዚህን በአል አከባበር ለሚመለከት የውጭ ታዛቢ የሰሜን ህዝቦቻችን በሁሉም መለክያ አንድ ህዝብ እንጂ ሁለት ወይም ሶስት ሆነው ሊታዩት እንደማይችሉ እሙን ነው።

የሰሜኑ ክፍል የሀገራችን ህዝቦች ልክ እንደ ደቡብ፣ ምስራቅ፣ ምእራቦቹ ህዝቦቻችን ከሚያለያዩዋቸው ይልቅ አንድ የሚያደረጉዋቸው እንደሚበዙ ብዙ ከማስረዳት ይልቅ የአሸንዳን አንድ ሰበዝ በፍቅር ማሳየት ሁሉን ነገር ይገልጸዋል።

ስለ አንድነታቸው ከመግለጽ ይልቅ ስለ ልዩነታቸው ለመግለጽ ይቸገራሉ። ምክንያቱም አንድ የሚያደርጓቸው መገለጫዎች ከሚያለያያቸው ይበዛሉና ነው።

አንዱን ከአንዱ ለይቶ ለመረዳት ማንነቱንና ብሄሩን በመጠየቅ ከአንደበቱ መስማት ካልሆነ በስተቀር፣ ከአመጋገቡ፣ ከአለባበሱ፣ ከባህሉ፣ ከእሴቱና አኗኗሩ እንዲዚሁም ከክብረ በአላቱ ተነስቶ ማንም ይህ ከዚህ ነው፤ ያ ከዚያ ነው ለማለት አይችልም።

የህዝቦቻችን ትስስር፣ በማንም ጫና ወይም አስገዳጅነት ሳይሆን ከህዝቦቹ የጋራ ማንነትና የጋራ ታሪክ የሚቀዳና የትላንት ታሪካቸውም ሆነ የዛሬ እውነታቸው ነው፡፡

የነዚህን ህዝቦች የአብሮነት ታሪክ እና ባህል ስንመረምር የምናገኘው የአሸንዳ/ሻደይ በአላቸውም በየትኛውም የዘመን ሀዲድ ላይ የትኛውም መንገራግጭና ንትርክ ቢኖር እንኳን በሁልጊዜ ህይወታቸውም ሆነ በታሪክ መሰውያቸው ላይ ያለው እውነት አንድ እንደሆኑ የሚናገር፤ በሚመጣውም ዘመን አንድ ሆነው እንደሚቀጥሉ የሚያመለክት በርካታ ህያው ምስክር ያለበት ውብ ሰነድ ነው።

የአሸንዳ/ሻደይ በአልን የመሳሰሉት የጋራ እሴቶቻችን ከቀደምት አባቶቻችን ጋር በመንፈስ የሚያስተሳሱሩን ድሮች፣ ወደፊትም አብረን እንድንጓዝ የሚያደረጉን መንገድ እና አጓዦቻችንም ጭምር ናቸው።

ስለ ትላንት፣ ስለ ዛሬና ስለነገ አንድነትና አብሮነት ከሚናገሩ ህያው ምስክሮች አንዱ የጾመ ፍልሰታ ለማርያምን መፈታት ተከትሎ ከነሃሴ 16 ጀምሮ ቀጥሎ ባሉ ቀናት በተለያያ እድሜ ደረጃ ያሉ ሴቶች በዋናነት ግን በወጣቶችና ልጃገረዶች የሚከበረው የአሽንዳ/ሻደይ በኣል ነው።

ይህ በአል በሀገራችን ከሚከበሩ ደማቅና ሀሴትን ከሚሞሉ በአላት አንዱ ሲሆን፤ ከሌሎች በአላት የሚለየውም የበአሉ ባለቤቶች ሴቶች በተለይም ወጣት ሴቶች መሆናቸው ነው።

ይህ በአል የሴት ልጆች በተለይም ወጣት ሴቶች አንገታቸውን አቀርቅረው በሚሄዱበትና በአደባባይ ወጥተው ፍላጎታቸውን በማይገልጹበት ወቅት ሁሉ በሙሉ ነጻነት ይልቁንም በጋራና በአደባባይ የወደዱትን የሚያሞጉሱበት፣ የጠሉትን ሃሳብና ተግባር በነጻነት የሚያወግዙበት ድንቅ በአል ነው።

የአሸንዳ/የሻደይ በአል ዜጎቻችን ሃሳባቸውን በነጻነት እንዲገልጹ ከፈቀድንና ባህል ካደረግነው የሚያስፈራንና የሚያስደነግጠን ሳይሆን በአሸንዳ/ሻዳይ በአል ላይ እንደሆነውና እየሆነ እንዳለው እጅግ ማራኪና ውብ የሆነ የጥንካሬና የነጻነት መገለጫ ሆኖ በመኖር በፍቅር የምናከብረው ብቻ ሳይሆን ለአብሮነታችን ማሰረገጫ ማህተብ ሆኖ ከየልባችን የምናኖረው ባህላዊ የአብሮነት ሙዳያችን ነው።

ልክ በአሁኑ ሰአት በአሸንዳ/ሻደይ እንደምንደሰተው ሁሉ ልጆቻችና ቀጣዩ ትውልድ ሃሳብን በነጻነት በአደባበይ የመግለጽ ባህል ስለአወረስናቸው ሲያሞግሱን ይኖራሉ።

አሸንዳ/ሻደይ የሴቶች ውበት፣ ክብር እና ነጻነት ማሳያ ብቻ ሳይሆን ነጻነት ራሷ ነጻ የምትወጣበትና በአደባበይም ስጋ ለብሳ የምትታይበት ታላቅ ቀን ነው።

አሸንዳ/ሻዳይ ስለ ሴቶች ክብር፣ ስለባህሎቻችን ውበት፣ ስለህዝቦቻችን ወንድማማችነትና አንድነት የሚናገር ብቻ ሳይሆን፤ በሁሉም መስክ ህዝቦቻችን ነጻ ቢሆኑ፤ ሃሳቦቻቸውን በነጻነት ነገር ግን በሰላም በአደባባይ የሚገልጹበት ሁኔታ ቢፈጠር ምንኛ ውብና ድንቅ ሃገር ሊኖረን እንደሚችል አፍ አውጥቶ የሚነገር ህያው ትእምርት ከመሆኑም ባሻገር ለዘመናዊው የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታችንም ከባህላዊው ድንቅ ሀብታችን ብዙ የምንመነዝርበት ድንቅ ሀብታችን ነው። አሸንዳ/ሻደይ ከሀገራችን አልፎ ለአለም ቅርስነት የሚበቃ የማይዳሰስ ሃብት ነው።

ይህ ሀብት ከሰሜን ኢትዮጵያ አልፎ በደቡብ ኤርትራም ጭምር የሚከበር ውብ በአል ሲሆን፤ ልናከብረው፣ ልንንከባካበው፣ እና ታሪካዊ እሴቱን ሳይለቅ ከትውልድ ወደ ትውልድ ልናስተላለፈው የሚገባን መሆኑ አጽንኦት ሰጥቼ ለመግለጽ እፈልጋለሁ።

በአሉ የህዝቦቻችንን ትስስር አጉልቶ የሚያሳይ የጋራ ጸጋና ህዝባዊ በረከት እንጂ የምንጣላበት፣ እንደ አላቂ ሃብት በድርሻ-ድርሻ የምንካፈለው አይደለም።

ይህ አስደሳችና አስደናቂ ባህል፣ የሰሜን የሀገራችን ህዝቦች ብቻ ሳይሆን የመላ ኢትዮጵያ ህዝቦች፤ የኢትዮጵያውያንም ብቻ ሳይሆን የአለም ሀብትና ቅርስ መሆን እንዲችል በአለም በማይዳሰስ ሀብትነት እንደሚዘገብ አጥብቀን መስራት ይኖርብናል።

በአሉን የምናከብረውና የምንከባከብው የውጭ ሃገር ቱሪስቶችን ለመሳብ፣ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማግኘት ሳይሆን ራሳችንን፣ ክብራችንን፣ ታሪካዊ እሴቶቻቸንንና በልዩነቶቻቸን ውስጥ ያለውን የማይናወጥ አንድነት ለማሳየት ነው።

ነገር ግን ይህንን ማድረግ የሚቻለው እና አሴቶቻቸንን ከራሳችን አሳልፈን የአለም ማድረግ የምንችለው በዋናነት ሰላም፣ አንድነት እና ፍቅር ሲኖርና ተደምረን ጠንካራ ህዝቦች ስንሆን ብቻ ነው። ስለሆነም ልክ እንደ ባህላዊ እሴቶቻችንና በኣላቶቻችን ሰላማችንን፣ ሃገራዊና አንድነታችንን እና አብሮነታችንን ልንንከባከብ፣ ልናጎለብት እና አጥብቅን ልንጠብቅ ይገባል።

ለሁላችንም መልካም የአሸንዳ/ሻደይ በዓል እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ እና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!

[ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር]

(ፎቶ፤ የበዓሉ አከባበር በአማራ ከለለ፤ ከአማራ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ)

ተጨማሪ ማብራሪ ከጎልጉል፤ በዓሉ በራያ፣ እንደርታ እና ተምቤን አካባቢ በትግሪኛ አሸንዳ ተብሎ ይጠራል፤ ከዛሬ (ነሐሴ 16) ጀምሮ እስከ አዲስ ዓመት ድረስ ይከበራል፡፡ በዋግ ሕምራ ዞን አካባቢ ሻደይ፤ በራያ ቆቦ ደግሞ ሶለል ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ነሐሴ 16 ቀን ይከበራል፡፡ በአዲግራት ከተማ ደግሞ ማርያ ተብሎ በመጠራት እንዲሁ ከነሐሴ 15-17 ሲከበር በአክሱም ከተማ ደግሞ ዓይኒዋሪ በመባል ከነሐሴ 23-25 ድረስ ይከበራል፡፡ በደቡባዊ ኤርትራም እንዲሁ በልዩ መንገድ ከበራል፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: ashenda, Right Column - Primary Sidebar, shaday

Reader Interactions

Comments

  1. Mulatu Derbew says

    August 22, 2018 12:34 pm at 12:34 pm

    Well I was born and raised in Sekota. I left my birth place when I was very young and never paid attention about shadey, but I do remember growing up, young girls playing shadey. Young men follow sometimes first to see the play and after a few days these young men are allowed to take a piece of the ahenda/the grass type that the girls ware on their waist.
    I met a fellow Ethiopian from Tigray on our conversation I said something about shadey/ashenda and he was very surprised that I too know about it. This conversation was about twenty years ago here in Canada. Now, I hear that (most probably and as usual by the Woyane) they want it only to be recognized as intangible asset of Tigray. Well, what is left that woyane did not want just for itself, never enough that 27 years, they have taken/stolen everything Ethiopian and now when they are cut to size, they want every little thing for themselves again. Really? The exact expression of woyane is “Ye’qen Giboch” only Gib is the one who likes “meqeramet”. However, Shadey is Ethiopian not woyane’s, and we will celebrate it with real Tigrayan sisters and brohers as well as introduce it to the rest of Ethiopia and the world. Woyane has to go from Tigray too, they are no good for no one even for the Tigray people they promise to stand for. They are simply Fascists.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm
  • “ሃሳብ ሲነጥፍ ነፍጥ አንግቤ እዋጋለሁ” የሚሉ አካላት ላይ እርምጃ ይወሰዳል – የመከላከያ ሠራዊት August 1, 2023 09:25 am
  • ደቡብ አፍሪካ የመሸጉ ወንጀለኞች ለሕግ ተላልፈው ሊሰጡ ነው July 31, 2023 09:27 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule