ለጥቁር ገበያ ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ ነዳጅ እና ግምቱ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ከኅብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ መያዙን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ “ትዕግስት ብሩክ ቶታል ማደያ” ውስጥ ጥር 12 ቀን 2011 ዓ/ም በ44 ጀሪካን 995 ሊትር ቤንዚን ከማደያው በመቅዳት ላይ እንዳሉ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተቀዳውን ከአስራአንድ ሺ ብር በላይ ዋጋ የሚያወጣ ቤንዚን እና ሌላ ሊቀዳበት የነበረ አርባ አራት ባዶ ጀሪካን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 29642 ከሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ጋር በቁጥጥር ሥር አውሏል።
ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 5 ግለሰቦችም ፖሊስ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ እንደገለፁት የማደያው ሠራተኞች ቤንዚን በጥቁር ገበያ ከሚሸጡ ህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ድርጊቱን ፈፅመዋል።
ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም ልዩ ቦታው አማኑኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ኮድ 3-47453 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከላይ ሲሚንቶ በማድረግ ከሥር ስድሳ ሦስት ጀሪካን ቤንዚን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በድንገተኛ ፍተሻ መያዙን ኮማንደሩ አስረድተዋል።
በተያያዘ ዜና ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም ምዕራብ ሆቴል አከባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-80502 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ በኮንትሮ ባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ ተይዟል።
ፖሊስ መምሪያው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተሽከርካሪው ቢያዝም አሽከርካሪው ግን ለጊዜው እንደተሰወረ እና ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ኮማንደር ጌታነህ ገልፃዋል።
ተሽከርካሪው ሲያዝ በርካታ ጣቃ ጨርቆች፣ 2ሺህ የሞባይል ቻርጀሮች፣ 3480 አይነቱ “ኑር ሴላ” የሆነ ሲጋራ እና አንድ ሺ የሪሲቨር ሪሞት ኮንትሮል ይዞ ለማምለጥ ሲሞክር እንደነበር ኃላፊው አስረድተዋል።
ምንጭ፦ ኢ.ፕ.ድ.
gi Haile says
ከቀድሞ የምሮ የረገራችን ችግር ፈጣሪዎች በለስልጣንና ሐጉምሩክ ሰራተኞች ከለይ ጀምረው በኔትዎርክ ኮንትሮባንድ ሲያስገቡ ያሉ ሰለሆነ ማጠናከር የሚገባው የበላይ ለሥልጣንን ከአቀጣጣር ጀምሮ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። በተለይም ከድሮ ጀምሮ ጉምሩክና ከኳድ መኪና ሹፌሮች በሰሜን ክልል ተወላጆች የተያዘ ነበር ከአይለስላሴ ጊዜ ጀምሮ መፍትሔ ያጠው ኮንቶሮባንድ አደገኛ የወንጀል ሰራ የሚሰራበት ቦታ ነው የየክልል ጉሙሩክ ኬላዎች በካሜራና በልዪ የምርመራ ስልት ቁጥጥር ሊደረግበት ያለ ክፍል ቢኖር በአየር ትራንስገኸፖርት፣ በወደብ ና በክልል ጉምሩክ ጣቢያ ላይ ፈዴራልና የክልል መንግስት ተባብረው ሊሰሩና ይህን የመሰለ ወንጀልና ዪንግስት ገቢ በከንቱ በሌቦች እጅ መግባት የለበትም። ሌብነት የሰው ልጅ የመጨረሻው የሞራል ዝቅተኛው ሰፍራ ነው። በሰው ልጅ ሊጠላ የሚገባው አመል ነው። ኢትዮጵያና አፍሪካ ሰሌብነት ነፃ ይወጣሉ ሌብነት ወንጀል ነው።