• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በግብፅ እየሆነ ያለው ለእኛ ምን ትምህርት ይሰጣል?

August 16, 2013 07:22 am by Editor 1 Comment

ከትናንት ጀምሮ ብዙዎች በግብፅ እየሆነ ያለውን በማህበራዊ ድህረ ገፆቻቸው ላይ በፎቶ የተደገፈ መረጃ እየሰጡ ነው።ሁኔታው እጅግ ዘግናኝ እና አሳዛኝም ነው።በተለይ ከጉዳዩ ጋር ምንም ተያያዥነት የሌላቸው አብያተ ክርስትያናት መቃጠል አጋጣሚን ተጠቅሞ የእረጅም ጊዜ እኩይ ዕቅድን የመፈፀም ድርጊት ነው። እኔን የሚያሳስበኝ እኛ በተወሳሰበ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ውስጥ ያለን ተመሳሳይ የታሪክ ክስተት ያሳለፍነው ኢትዮጵያውያን ከእዚህ ተምረን ምን እናድርግ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ነው ቁም ነገሩ።ከእዚህ በተረፈ ግን ለሀገራችን መፍትሄ የምንለውን ለመናገር ፈርተን ወይንም የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታዎችን ሳናነሳ ስለ ግብፅ ብንናገር ምን ይሆን ፋይዳው?

የፖለቲካ ለውጥ ከመነሻው እስከመድረሻው የሚሄድባቸው ሂደቶች እጅግ አስገራሚ እና ውጤቱም ከተጠበቀው ይልቅ ያልተጠበቀው ክስተት የበላይ መሆኑ አንዱ እና አይነተኛው ተፈጥሮው ነው።ለእዚህም የቅርብ ጊዜ ምሳሌ የሚሆነን የሰሜን አፍሪካው የለውጥ ማዕበል ነው።የለውጥ ማዕበሉ አነሳስ፣ሂደት፣ግብ እና ውጤት የሃገራቱን ተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ቢሆንም በአግባቡ የተደራጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያሉባቸው እና የሌሉባቸው ሃገራት ልዩነት ግን ፍንትው ብሎ ታይቷል። የቱኒስያን እና የአልጀርያ የለውጥ ማዕበል ከሊብያ ጋር ያለው ልዩነት እና  በአንፃሩ ደግሞ የግብፅ እና የየመን ሁኔታ አሁንም ድረስ በእንጥልጥል መሆኑ ለሰሜን አፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ቀንድ ብሎም ለኢትዮጵያ የሚኖረው ተዘዋዋሪ ተፅኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።ቢያንስ የሁለቱ ሃገራት አለመረጋጋት በእዚሁ ከቀጠለ የአካባቢ ትናንሽ ጉልበተኞች የመፈጠራቸው አባዜ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የጦር መሳርያ ንግድ የሚደራባቸው ሃገራት የመሆናቸው ፋይዳ ውሎ አድሮ እንደ ኢትዮጵያ ላለች ሃገር አይነተኛ ፈተና መሆኑ አይቀርም።ፈተናውም ከሃይማኖታዊ ነውጠኞች እስከ ንግድ አዋኪዎች ድረስ የሚፈጥረው ተፅኖ ቀላል አይደለም።

የአፍሪካ ቀንድን እና ቀጠናውን ስንመለከት በብዙ ፖለቲካዊ፣ምጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ችግሮች የተወጠረ በመለስተኛ የነገሮች ክስተት ከባድ ስብአዊ ቀውስ የመድረሱ ዕድል ከፍተኛ እንደሆነ እንመለከታለን። የአሁኑ ጊዜ የአካባቢው የፖለቲካም ሆነ የወታደራዊ  ኃይላት(የኢህአዲግ መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ ኃይሎች) ነገሮችን በአንክሮ አይተው አማራጩን እና አዋጪውን የፖለቲካ መስመር የመቀየሻ ወሳኝ ጊዜ ላይ  መሆናቸውን ቢረዱት ለሀገራችን አንዱን የፈተና ወቅት የምታልፍበት ጊዜ ሆነላት ነበር።ብልህ እና ቆራጥ መሪ የሚናፈቀው የእዚህ ጊዜ ነው። ከእዚህ ባለፈ ግን ውጥረቶችን ለማርገብ በመሞከር መተኮር በሚገባው በዋናው እና እጅግ አደገኛው ሁኔታ ላይ ማትኮር ካልተቻለ ተያይዞ መጥፋት ብቸኛ ዕጣ መሆኑ የማይቀር መሆኑን መረዳት ብዙም ብልህነት አይጠይቅም።

በሰላማዊ መንገድ መንግስት መቀየር ያልታደለቸው ሀገራችን ከውጭ ያሉት ቅራኔዎች ነፀብራቅ እና በውስጥ በእራሷ እና ከቀጠናው ጋር ያሉት ቅራኔዎች ወደ አልታሰበ እና አልተፈለገ ጫፍ ኢትዮጵያን ይዘዋት እንዳይሄዱ ማሰብ የዜጎች ትልቁ ድርሻ መሆን አለበት።ለመሆኑ ውሎ አድሮ ኢትዮጵያ ላይ በተዘዋዋሪም ሆነ በቀጥታ  ተፅኖ ከሚፈጥሩት ቅራኔዎች እና ቀውሶች ውስጥ-
ከውጭ –
– በሱማሌ ያለው የአልሸባብ እንቅስቃሴ፣
– የዑጋዴን ግጭት፣
– የግብፅ ሁኔታ አለመረጋጋት እና እስካሁን ወጥ የውጭ ፖሊስዋ አለመታወቁ፣
– የአቶ ኢሳያስ ድብቅ እና ግልፅ ያልሆነ አስተዳደር በኤርትራ መኖሩ፣
– የፅንፈኛ እስልምና እንቅስቃሴ፣
– ጠንካራ ያልሆነው የደቡብ ሱዳን መንግስት ቅርፅ ገና በአግባቡ አለመለየቱ የሚሉት ጥቂቶቹ ሲሆኑ፣

ከውስጥ –
– ኢህአዲግ ከምርጫ ጋር በተያያዘ ከህዝብ እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የገባው ቅራኔ፣
– ኢህአዲግ ከተለያዩ ባለድርሻ የህብረተሰብ አካላት ጋር የፈጠራቸው ቅራኔዎች። (ለምሳሌ ከሙስሊሙ ህብረተስብ ጋር፣ ከዋልድባ ገዳም ይዞታ ጋር ይጠቀሳሉ)፣
– የሕዝብ ብዛት እየጨመረ መሄድ፣
– የዋጋ ግሽበቱ ጭማሪ አለማቆም (ባለፈው ወር ብቻ በመንግስት ዘገባ መሰረት አጠቃላይ ግሽበቱ በ 8% መጨመሩ ይታወቃል)፣
– የሐብት ክፍፍሉ መራራቅ፣
– የስራ አጥነት መጨመር፣
– የማህበራዊ ኑሮ ቀውስ (ከቀዬው የሚፈናቀለው መብዛት፣የጎዳና ተዳዳሪ መጨመር፣ሃገሩን ጥሎ የሚሰደደው መብዛት ወዘተ) የሚሉት ከብዙ በጥቂቱ ናቸው።


ከኢህአዲግ መንግስት እና ከተቃዋሚ ኃይሎች ምን ይጠበቃል?

እነኚህ ከላይ የተመለከትናቸው ቅራኔዎች እና ቀውሶች በአግባቡ ካልተፈቱ እና ለመፍትሄነት ሁሉም ድርሻ እንዳለበት ካልተገነዘበ ነገ ሀገራችን ብለን የምንጠራት ምድር እንዳናጣ ባንመኘውም መፍራት ግን ለጥንቃቄ ይረዳል። ለሀገራችን ውስብስብ ችግር መፍትሄ ለመስጠት ተቃዋሚ መሆን ብቻ መድሃኒት አይሆንም።የመንግስትን ታላቅነት በመስበክ እና አቶ መለስ ታላቅ መሪ ነበሩ እያሉ በማስተጋባትም ሀገር አይገነባም። በሆደ ሰፊነት፣ በጋራ ነጥቦች ላይ በማተኮር፣እጅግ አደገኛ የሆኑትን የሀገሪቱን ችግር ቀድሞ ለመቅረፍ በመሞከር፣ ኢትዮጵያዊነትን መሰረት አድርጎ ሀገራችንን የነበረ እሷነቷን በክብር በማስቀጠል ግን በጋራ ከመጥፋት ያድናል።እዚህ ላይ ትልቁን በሃጋራችን ላይ የሚያንዣብበውን አደጋ  የተጠያቂነት  ድርሻ የሚይዘው የኢህአዲግ መንግስት መሆኑን መርሳት አይገባም። ለእዚህም ዋናው እና አቢይ ምክንያት ኢህአዲግ  በመንግሥትነት እስከተቀመጠ ድረስ ቅራኔዎችን ለመፍታትም ሆነ የፖለቲካ ኃይላትን እና የህብረተሰቡን አካላት ጥያቄ ለመመለስ የዋና ባለድርሻ አካልነቱን በመያዙ ነው። በሌላ በኩል የተቃዋሚ ኃይላትም ከኢህአዲግ ጋር የሚያደርጉት ማናቸውም አይነት የፖለቲካ ለውጥ ማምጫ የተፅኖ መፍጠርያ መንገዶች ማለትም ሰላማዊ ሰልፍም ሆነ  የትጥቅ ትግል የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የማይጎዳ እና ለዘመናት ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ለሚሹ ኃይላት የማይመች ሀገሪቱንም ወደማትነሳበት አዘቅት የማይከት መሆኑን በሚገባ ማጤን ተገቢ ነው።

ባጠቃላይ የሀገራችን ውስጣዊ የፖለቲካ ቅራኔ፣የኢህአዲግ ግትር እና ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ አሰልቺ ፖሊሲ፣ የአካባቢያችን ሃገራት የፖለቲካ ንፋስ ተለዋዋጭነት፣ የኢትዮጵያን የመኖር ህልውና የሚፈታተኑ እንቅስቃሴዎች መኖር (የኑሮውድነቱ፣ የህዝብ ብዛት መጨመር) ስንመለከት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ለውጥ በመጣው መንገድ ቢመጣ በነበረ እሷነቷ የማስቀጠል ዋስትናውን ያሳንሰዋል። ይህ ማለት ደግሞ ኢህአዲግም ሆነ ተቃዋሚዎች በጋራ ስለሚጠሯት ሀገር ለማውራት ዕድል የማያገኙበት አስከፊ ጊዜ ይመጣል ማለት ነው። ስለዚህ ኢህአዲግ የዲሞክራሲውን መንገድ እና እውነተኛ የምርጫ ስርዓት ከልብ ባሳየ መንገድ መከወን (እውነተኛ የፖሊሲ ለውጥ ማድረግ ለምሳሌ በዋና ዋና ቁልፍ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይ) ፣ ነፃ የሚድያ አገልግሎት እንዲኖር ከልዩነት ይልቅ አንድነትን የሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ላይ መስራት ቢጀምር (ሃያ አንድ አመት ሙሉ ሲጠየቅ የነበረን ጉዳይ ካለመሰልቸት ስደግመው አንባቢ እንዳይሰለች ይቅርታ ከመጠየቅ ጋር) እና  እራሱንም ሆነ ሀገሪቱን ወደማትወጣበት አዘቅት ከመክተቱ በፊት በ2006 ዓም  በአንክሮ ቢያስበበት ለኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ እንደዋለ ይቆጠርለት ነበር።እዚህ ላይ ላሰምርበት የምፈልገው እነኚህን ተግባራት ቀድሞ ኢህአዲግ ማድረግ ካልቻለ የለውጥ ማዕበሉ በተፈለገውም ሆነ ባልተፈለገው መንገድ መምጣቱ የግድ ነው። አሳዛኙ ግን ውጤቱ እና የመጨረሻ ግቡን በጥሩ መልኩ ለመተንበይ አለመቻሉ ነው።በትንሹ ለመተንበይ ግን የተቃዋሚዎችን አያያዝም ሆነ የመንግስትን ቅራኔ አፈታት መንገድ መመልከት በቂ ነው። ሁለቱም የሚቀራቸው መንገድ እንዳለ ይስተዋላል።ለኢህአዲግ ግን እራሱን የእውነተኛ ለውጥ ማዕበል ለማድረግ እና ሀገርንም ህዝብንም ይቅርታ ለመጠየቅ ከነገ ይልቅ ዛሬ ይቀርበዋል። 2006 ዓም ምን እንሰማብሽ ይሆን?

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. koster says

    August 19, 2013 04:44 pm at 4:44 pm

    Fascists will not give up power either by begging or Ballot, they have to be forced and this is only possible by a united anti-Woyane force. 21 years of cheating, looting and terrorizing the Ethiopian People should be stopped by all means possible. http://vimeo.com/18242221

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule