• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሚወለዱበት፣ የሚሞቱለትና የሚሞቱበት መሬት

July 16, 2013 08:24 am by Editor 1 Comment

የሚወለድበትን መሬት ማንም ሰው አይመርጥም፤ የዘመኑ ቅንጦት ኢትዮጵያ አርግዞ አሜሪካ መውለድ ቢሆንም፣ ልጁ ምርጫው ውስጥ የለበትም፤ አንኳን ልጁ አባትዬውም ምርጫው ውስጥ የሚገባ አይመስለኝም፤ በእንደዚህ ያለው ኢትዮጵያን አስጠልቶ-ሌላ-እንዲሆን በተፈጠረ ቅንጦት የሚወለድ ኢትዮጵያዊ ምን እንደሚሆን መተንበይ ያዳግታል፤ ልጁ ወይም ልጅቱ በራሳቸው ዝንባሌ፣ ፍላጎትና ጥረት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸው ግንኙነት በእልህ ከአልተለወጠ እናቶቻቸው የተለሙላቸው ማንነት ከኢትዮጵያዊነት ይገነጥላቸዋል፤ ነገር ግን የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንዲህ በቀላሉ ተቀርፎ የሚወድቅ አይደለም፤ ሲደንቀኝ የቆየ ነገር ልናገር፤ አንድ ጊዜ በኢሰመጉ ተልእኮ ካናዳ ሄጄ አንድ ስብሰባ ላይ አንድ አርመን ወጣት ነበረ፤ ይህ ሰው ለኢትዮጵያ ያለው ስሜት በጣም የጋለ ነበር፤ በሌላ ዘመን ደግሞ ፋጡማ ሮባ በአትላንታ ማራቶን በአሸነፈች ጊዜ ደግሞ በቴክሳስ የሚኖር ከአንድ ግሪክ ገንፍሎ የወጣው ንግግር በጣም ልብን የሚነካ ነበር፤ ለዚህ አርመንና ለዚህ ግሪክ የኢትዮጵያዊነት ስሜት በዘር የተላለፈላቸው አይመስለኝም፤ ስለዚህም አሜሪካ የሚወለዱትም ኢትዮጵያውያን ልጆች እናቶቻቸው ሳያውቁ ከውስጣቸው የሚያስተላልፉላቸው ስሜት ኢትዮጵያዊነታቸውን ይገነባው ይሆናል፤

እንደሚመስለኝ የሚሞቱለት መሬት ከውስጥ ከነፍስ ጋር በተገናኘ ስሜት የተቆራኘ ነው፤ መሬቱንና ስሜቱን ምን አገናኛቸው? ምን አቆራኛቸው? እንዴት ተቆራኙ? የሚሉትንና ሌሎችንም ጥያቄዎች ለመመለስ መሞከር እዚህ ቦታው አይደለም፤ ለዚች መሬት የሞቱላት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖራቸውን አምነን በመቀበል እንነሣ፤ ምናልባትም አብዛኛዎቹ ቁራጭ መሬትም አልነበራቸውም፤ እንዲያውም አብዛኞቹ ለመቃብር ያህል ሁለት ክንድ መሬት አንኳን አላገኙም፤ በተሰለፉበት ወድቀው የአውሬና የአሞራ ምግብ ሆነው የቀሩ ናቸው፤ ለመሬት ፍቅር ሞተው ለመቃብር የሚሆናቸው መሬት እንኳን አላገኙም፤ ነገር ግን የሚደንቀው እነሱ ሞተው ለመቃብርም የሚሆን መሬት ሳያገኙ የሚቀጥለውን ትውልድ ባለመሬት አደረጉት።

እንደሚመስለኝ የአንድ አገር አንዱ ትውልድ በሞቱ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፈው መሬት ብቻ አይደለም፤ ሲሞት ይዞት የነበረውን ጎራዴና ጋሻ፣ ለሞት ያበቃውን የመሬት ፍቅር፣ ክብርና ኩራትም ጨምሮ ነው፤ መሬቱን ብቻ ተረክቦ ሌላውን መጣል የውርደት መጀመሪያ ይሆናል፤ እዚህ ላይ ብዙ ሰዎች በሚጠሉት ቃል መጠቀም ልገደድ ነው፤ ባንዳ የሚባለው መሬቱን ከክብርና ከኩራቱ ጋር ለጠላት ያስረከበ ነው፤ (እውነተኛው ባንዳ እንዲያውም ዜግነቱንና ወገኖቹን ክዶ፣ የሰውነቱን ክብር ሸጦ የጠላት ሎሌ በመሆን ወገንን እያስጠቃ ተዋርዶ የሚያዋርድ ነው)፤ ለባንዳው መሬት ርስትና ዓጽመ-ርስት የሚባሉ ነገሮች ትርጉም የላቸውም፤ ዓጽመ-ርስት የሕይወት መስዋእት የተከፈለበት መሬት መሆኑ ለባንዳው ባዕድ ነገር ነው።

የኢትዮጵያ መሬት ከአድዋ ዘመቻ እስከዛሬ ስድስት ያህል ትውልዶችን አስተናግዶአል፤ ከአድዋ አስከማይጨው ሁለት ትውልዶች፣ ከማይጨው እስከ1967 ሁለት ትውልዶች፣ ከ1967 አስከ2005 ሌላ ሁለት ትውልዶች እነዚህ ትውልዶች በኢትዮጵያ መሬት ላይ ያመጡትን ለውጥ ሁሉም የሚያውቀው ይመስለኛል፤ ቢሆንም ልዩነታቸውን ማመልከት የሚያሻ ይመስለኛል፤ በአድዋ የዘመተው ትውልድ በርስትና በዓጽመ-ርስት ላይ የተተከለ ልበ-ሙሉ ባለቤት ነበር፤ የማይጨው ዘማች በግርማዊነታቸው ቸርነትና መልካም ፈቃድ  ላይ የተመሠረተ ስጦታና የማደሪያ መሬት ነበረው፤ በአንዳንድ ቦታ ብዙ ገበሬዎችን ከመሬት ባለቤትነት የነቀለና ወደጭሰኛነት የለወጠ ሥርዓት ነበር፤ ከ1967 ወዲህ ሁለት ዓይነት የመሬት አጠቃቀም ይታያል፤ አንዱ የደርግ ሥርዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ ከዳር አስከዳር እኩል ባለመሬት ለማድረግ ያወጣው አዋጅ ርስትንም ማደሪያንም ሽሮ የመሬት ባለቤትነትን በዜግነት ላይ ተከለ፤ የወያኔ ሥርዓት ሲመጣ የገጠር መሬትን በፖሊቲካ ታማኝነት ደለደለ፤ የከተማ ቦታን ደግሞ በአጼ ዘመን ሲሠራ እንደነበረው ለቅርብ ሎሌዎችና ታማኛ አገልጋዮች እንደማደሪያ ዓይነት እየሆነ ተሰጠና አዲስና በጣም ከፍተኛ የከተማ ባለሀብቶች መደብ ተፈጠረ፤ በገጠርም ለልዩ ሰዎችና ለስደተኞች፣ እንዲሁም ለውጭ አገር ባለሀብቶች (ቻይና፣ ህንድ፣ ሆላንድ … ) ተደለደለ፤ እንዲህ እንዲህ እያለ በወያኔ አገዛዝ በውጭ አገር ከበርቴዎችና በአገር ውስጥ የቢሮና የጠመንጃ ከበርቴዎች እየበረከቱ ደሀው ተደፈጠጠ፤ የወያኔ አገዛዝ የማርክስና የሌኒንን መፈክር አንግቦ ተነሣና ደሀን የጠላበት ደረጃ ላይ ደረሰ፤ እንደሚስለኝ የተለመደው የአስተሳሰብ ስሕተታቸው ነው፤ ደሀነትንና ደሀን አንድ አድርገዋቸዋል!

በወያኔ አገዛዝ በገጠሩም ሆነ በከተማው መሬት ላይ የተወሰደው በጣም ደፋር እርምጃ በጣም የሚያስደንቅና ገዢዎችንም ተገዢዎችንም ለታሪክ ትዝብት የሚዳርግ ነው፤ አንድ ኪሊሜትር መንገድ ለመሥራት ስንት ደሀ ቤተሰብ ይፈናቀላል? አንድ ትልቅ ሕንጻ ለመገንባት ስንት መድረሻ የሌላቸው ደሀዎች አውላላ ሜዳ ላይ ይወድቃሉ? ነገር ግን ጨቋኝና ተጨቋኝ በስምምነት ለሚቀጥለው የጥቃት ዙር ይዘጋጃሉ፤ ይህ የትም ሌላ አገር የሚሆን አይመስለኝም፤ የኢትዮጵያውያን ልዩ ችሎታ ነው፤ እዚህ ወደዝርዝር ምክንያቱ አልገባም፤ ግን ምክንያት አለው።

እንኳን ለቀለብ ማምረቻ የሚሆን መሬት፣ አንኳን የመኖሪያ ቤት የሚሠራበት መሬት ለመቃብርም የሚሆን ሁለት ክንድ መሬት በሊዝ ሆኖአል፤ ወደፊት ደሀ የሚጣልበት መሬት አይገኝም ይሆናል፤ እንግዲህ የሚሞቱበት መሬት ወደማይኖርበት ሁኔታ እየደረስን ነው ማለት ነው፤ ስለዚህም አስቀድመን ማሰብ የሚያስፈልገን ይመስለኛል፤ በራሴ በኩል አውጥቼ አውርጄ ውሳኔ ላይ ከደረስሁ ቆይቻለሁ፤ መቀበር አልፈልግም፤ ሕይወቴን በሙሉ ተቀብሬ ኖሬአለሁ! ወይም በመቃብር ውስጥ ኖሬአለሁ፤ ድንጋይ እየተደራረበ ተጭኖብኝ አምላክ ድንጋዩን አፈር አድርጎ እያቀለለልኝ ሳልጨፈለቅ ቆይቻለሁ።

ስሞት ደግሞ፣ ወይም አንዳንዶቻችሁ ቃልም እንደምትፈሩ ለማሳየት እንደምትሉት ለህልፈት ስበቃ የሬሳን ፈቃድ የሚፈጽም ከተገኘ መቀብር አልወርድም፤ ድንጋይ አይጫንብኝም፤ ይበቃኛል፤ ኑዛዜ– ከሚለው ግጥሜ ቀንጭቤ ፍላጎቴን ልግለጽላችሁ፡ –

የሕይወት ጽዋዬ ጥንፍፍ ብሎ ሲያበቃ፤

ሲቀር  ባዶውን፣ የቆየ ባዶ ዕቃ፤

ሲበቃኝ፤ በቃህ ስባል፣

ትንፋሼ ሲቆም በትግል፣

ስሸነፍ ተሟጦ ኃይል፣

ሰው መሆኔ ቀርቶ፣- አስከሬን ስባል፣

እወቁልኝ ይህን ብቻ፣- የገባኝን ያህል

ሞክሬ ነበር ሰው ለመሆን፤

ሰውነት በከፋበት ዘመን።

በቁማችን ስንቃጠል ስንቀጣጠል ኖረን ስንሞት እሳትን ለምን እንፈራለን? ጭቆናና መታፈን ለምደን መቃብር እንወዳለን፤ እንደአህያችን ጭነት ለምደን ድንጋይ ለመሸከም ቀባሪ አታሳጣን እንላለን፤ –

መሬት አልነበረኝም በሕይወቴ

መሬት አልፈልግም፤ አሁን በሞቴ

አቃጥሉልኝ ሬሣዬን፤

አመድ እስኪሆን፤

አዋሽ ውስጥ ጨምሩልኝ አመዴን፤

አመዴ

ከአዋሽ ይቀላቀል ከዘመዴ

ይቺን አትንፈጉኝ አደራ

አመዴ እንኳን እንዲኮራ

የወያኔ አገዛዝም ሬሳ አቃጣይ ድርጅት ቢከፍት ለመቃብር የሚውለውን መሬት ለቻይና በማከራየት ኪራይ ሰብሳቢነቱን ያጠናክር ነበር፤ ህንዶች ሬሳ በማቃጠል ልምድ ስላላቸው አንድ የህንድ ባለሀብት ሬሳ በማቃጠሉ ሥራ ቢሰማራ የኢኮኖሚውን እድገት በጣም ያፋጥንላቸው ነበር፤ ለአገዛዙም፣ ለባለሀብቱም አዲስ የሥራ መስክ ይፈጥራል፣ ሬሳ የማቃጠሉ ተግባር በቁሙ የተጎዳውን ደሀ ሲሞት ደግሞ መድረሻ እንዳያሳጣው የደሀ ሬሳ ለማቃጠል የሚያስፈልገው ወጪ ‹‹ድህነትን ለመቀነስ›› ከሚለው በጀት ወይም እርዳታ ቢወጣ ችግሩን ሁሉ ያቀላጥፈዋል፤ ደሀውም እየተደሰተ ይቃጠላል ወይም ችግሩ አብሮት እንደሚቃጠል እያወቀ ይደሰታል።

የወደፊቱ ኢትዮጵያዊ የሚወለድበት መሬት የለውም፤ የትም የሚወለድ ነው፣ ፍቅሩን ከመሬት ላይ አንሥቶ ጥሬ ገንዘብ ላይ በመካቡ የሚሞትለት መሬት የለውም፤ ከመሬት ጋር ያለው የዓጽመ-ርስት ቁርኝት ስለተበጠሰ የሚሞትበት መሬት የለውም፤ ‹‹አፈር ነህና ወደአፈር ትመለሳለህ፤›› የተባለው ቀርቶ ድንጋይ ነህና ወደ ድንጋይ ትመለሳለህ የሆነ ይመስላል፤ መሬት የሰውነት መለኪያ መሆኑ ቀርቶ የሀብት መለኪያ ሆኖአል።

(Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    July 18, 2013 02:10 pm at 2:10 pm

    >ተወልደው የሚሞቱላት ሞተው ለመቀበራቸው ዋስትና የሌለበት…ግን ብዙዎች የሚመኟት…የሚናገሩላት የማይናገሩባት
    ለዚች መሬት የሞቱላት በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖራቸውን አምነን በመቀበል…”አብዛኞቹ ለመቃብር ያህል ሁለት ክንድ መሬት አንኳን አላገኙም፤ በተሰለፉበት ወድቀው የአውሬና የአሞራ ምግብ ሆነው የቀሩ ናቸው፤ ለመሬት ፍቅር ሞተው ለመቃብር የሚሆናቸው መሬት እንኳን አላገኙም፤ ነገር ግን የሚደንቀው እነሱ ሞተው ለመቃብርም የሚሆን መሬት ሳያገኙ የሚቀጥለውን ትውልድ ባለመሬት አደረጉት።” ሻማ ትዝ አለችኝ!
    ___—————________
    አይ አንቺ ‘ሻማ’ እራስሽን መስዕዋት ያደረገሽ
    መብራት በጠፋ ቀን ሁሉ የሚያበሩሽ
    እነሱ ሲደሰቱ አንቺን እየለኮሱሽ
    ሀዘንም ሲገጥማቸው አንችው ተቃጥለሽ
    ከቶ ማነው አንቺ ቀልጠሽ! አንብተሽ!
    ለሌላውን ብርሃን ሁኚ ብሎ የፈረደብሽ ?
    የወደፊቱ ኢትዮጵያዊ የሚወለድበት መሬት የለውም፤ የትም የሚወለድ ነው፣ ፍቅሩን ከመሬት ላይ አንሥቶ ጥሬ ገንዘብ ላይ በመካቡ የሚሞትለት መሬት የለውም፤ ከመሬት ጋር ያለው የዓጽመ-ርስት ቁርኝት ስለተበጠሰ የሚሞትበት መሬት የለውም፤በቁማችን ስንቃጠል ስንቀጣጠል ኖረን ስንሞት እሳትን ለምን እንፈራለን? ጭቆናና መታፈን ለምደን መቃብር እንወዳለን፤ እንደ አህያችን ጭነት ለምደን ድንጋይ ለመሸከም ቀባሪ አታሳጣን እንላለን፤ –
    ***ሻማ !
    ምን ነበር ታዲያ ከአንቺ የሰው ልጅ ቢማር
    ውጭ ሄዶ ከሚቀልጥ ከሚያነባ ከሚማረር
    እንዳይሆን የጋን መብራት እንዳይጠፋ ሳያስተምር
    እንደሻማ ተለኩሶ በርቶ እየታየ ለህዝብ ቢናገር
    ስንት የጨለመባቸው ፍንትው ብሎ በታያቸው ነበር !!።
    ክቡር አባቴ ” ሰዎች ያገኘሁት ሥራ ቋሚ አደለም የኮንትራት ነው ሲሏቸው እንኳን ሥራችሁ ይች የምትኖሩባትም መሬት የኮንትራት ነች” ይሉ ነበር። ሠው በገዛ ፍቃዱ ሆ!ብሎ በሀገሩ ባዕድ ይሆናልን? ማንነቱን ሸጦ ያጨበጭባል? ጉድ ነሽ የአንኮበር ቅጠል አለ። ሊ/ጠ ስለሠጡን ትምህርት እንደወትሮው ከአድናቆትና ምስጋና ጋር በለው! ከሀገረ ካናዳ በቸር ይግጠመን

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule