• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በአዲስ አበባ መብራት እንዳይቋረጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል

June 14, 2015 10:41 pm by Editor Leave a Comment

* የከተማዋ መብራት መቋረጥ ችግር የከተማዋ ዕድገት ነው

* የችግሩ ምክንያት የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ነው

* የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡና ግድቦች አለመሙላታቸው ነው ችግሩ

* ለጥናቱ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ተደርጓል

* ዕቅዱ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት ተግባራዊ ይሆናል

በአዲስ አበባና በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እያጋጠመ ያለው የኃይል መቆራረጥ፣ በዋናነት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ምክንያት ነው ሲባል ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ ለኃይል መቆራረጡ የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ግድቦች በቂ ውኃ ባለመያዛቸው እንደሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡

በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ 12 የኦሮሚያ ክልል ልዩ ዞን ከተሞች በየጊዜው የሚገጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ለማስቀረት ማስተር ፕላን ተነደፈ፡፡ አዲሱን ማስተር ፕላን ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ቢሊዮን ዶላር ያስፈልጋል፡፡

“አዲስ አበባና ዙሪያዋ የኤሌክትሪክ ዲስትሪቢውሽን ማስተር ፕላን ጥናት ፕሮጀክት” በሚል ስያሜ የተነደፈው ማስተር ፕላን፣ በሚቀጥሉት 20 ዓመታት በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡

ባለፈው ሐሙስ ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. በማስተር ፕላኑ ላይ ውይይት በተደረገበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ እንደተናገሩት፣ እ.ኤ.አ. እስከ 2017 ድረስ ተግባራዊ በሚደረገው የአጭር ጊዜ ዕቅድ አሮጌ ኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ይለወጣሉ፡፡

በአጠቃላይ ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ አንድ ቢሊዮን ዶላር በጀት መያዙ ተገልጿል፡፡ ከዚህ ውስጥ እ.ኤ.አ. እስከ 2017 ለሚተገበረው የአጭር ጊዜ ዕቅድ ማስፈጸሚያ 285 ሚሊዮን ዶላር፣ እ.ኤ.አ. ከ2018 እስከ 2022 ተግባራዊ ለሚሆነው መካከለኛ ዘመን ዕቅድ ማስፈጸሚያ 37 ሚሊዮን ዶላር፣ ለረዥም ጊዜ ዕቅድ ማስፈጸሚያ (እ.ኤ.አ. ከ2023 እስከ 2034) 745 ሚሊዮን ዶላር መበጀቱ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ በአዲስ አበባና አካባቢው የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎትና ዕድገት ለማጣጣም የተያዘውን ዕቅድ ለማስፈጸም፣ 1,067 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ ተገምቷል፡፡

ፕሮጀክቱ ተግባራዊ የሚደረገው በአዲስ አበባ በሚገኙት አሥር ክፍላተ ከተሞችና በኦሮሚያ ልዩ ዞን በሚገኙት አዲስ ዓለም፣ ኢሉ፣ ወልመራ፣ ሙሎ፣ ሱሉልታ፣ በረህ፣ አሌልቱ፣ ጊምቢቹ፣ አደአ፣ አቃቂ፣ ዓለም ገና፣ ቀርሳና ማሊሞ ወረዳዎች ናቸው፡፡

አዲስ አበባና ዙሪያዋ አገሪቱ ከምታመነጨው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 60 በመቶውን እንደሚጠቀሙ ኢንጂነር አዜብ ገልጸው፣ አካባቢዎቹ የሚያጋጥማቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል ሥርጭት መቆራረጥ ለማስቀረት የፕሮጀክቱ ተግባራዊ መሆን ወሳኝ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

ይህንን ማስተር ፕላን ከአፍሪካ ልማት ባንክ በተገኘ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ያጠናው የእንግሊዝ ኩባንያ የሆነው ፓርሳን ብሪንኤርሆፍ ሊሚትድ ነው፡፡ የኩባንያው ተወካይ ናንካ ብሩስ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት፣ አዲስ አበባ በፍጥነት እያደገች በመሆኑ እያጋጠማት ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ወጥታ፣ ለዕድገቷ የሚያስፈልጋትን ኃይል ለማግኘት ማስተር ፕላኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው፡፡

ይህ ፕሮጀክት ተግባራዊ ሲሆን፣ በከተማው የሚገኙ አሮጌ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያዎች በአዲስ ይተካሉ፡፡ መሻሻል ያለባቸውም እንዲሻሻሉ ይደረጋል በማለት ኢንጂነር አዜብ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይነት ይህ ፕሮጀክት በሐዋሳ፣ በመቀሌ፣ በባህር ዳርና በሌሎች ትልልቅ የክልል ከተሞች ተግባራዊ እንደሚሆን ኢንጂነር አዜብ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባና በአካባቢው ለረጅም ጊዜ እያጋጠመ ያለው የኃይል መቆራረጥ፣ በዋናነት በኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ ጣቢያዎች እርጅና ምክንያት ነው ሲባል ቆይቷል፡፡ ነገር ግን ከቅርብ ወራት ወዲህ ለኃይል መቆራረጡ የበልግ ዝናብ በተፈለገው መጠን ባለመዝነቡ ምክንያት፣ ግድቦች በቂ ውኃ ባለመያዛቸው እንደሆነ ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው፡፡(ምንጭ: ውድነህ ዘነበ፣ ሪፖርተር)

ሥልጣን በተቆጣጠሩ ወቅት በቀጣይ 10 ዓመታት ለኢትዮጵያ ያላቸው ህልም ምን እንደሆነ ተጠይቀው ህዝቡን በቀን ሦስት ጊዜ መመገብ እንደሆነ የተናገሩት “ባለራዕዩ” መሪ መለስ ግልገል ጊቤ በተመረቀ ሰሞን ከአሁን በኋላ ሻማ የሚበራው በኤሌክትሪክ መቋረጥ ለሚከሰት ችግር ሳይሆን ለልደት ብቻ እንደሚሆን በመግለጽ “ውርሳቸውን (ሌጋሲያቸውን)” ትተው ማለፋቸው አይዘነጋም፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule