ሱስ አስያዥ ለሆኑ የተለያዩ ነገሮችና እፆች ተጋላጭ የሆኑ ህፃናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱንና፤ ጉዳዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አንድ ጥናት አሳሰበ፡፡
“ፊዩቸር ኬር” በተሰኘ ድርጅት የተሰራውና ሰሞኑን ይፋ የተደረገ ጥናት እንዳመለከተው፤ በአሁኑ ወቅት ዕድሜያቸው ለአቅመ አዳም ያልደረሱ በርካታ ህፃናት የተለያዩ ሱሶች ተገዥ እየሆኑ ነው፡፡ እነዚህ ሱሰኛ ህፃናት እስከ እብደት ሊያደርሱ በሚችሉ የአዕምሮ ጤና ችግር ሊጠቁ የሚችሉ ሲሆን ለተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችም የተጋለጡ ናቸው፡፡ ከሱሰኛ ህፃናቱ መካከል በተለያዩ መንገዶች ራሳቸውን የሚያጠፉ ህፃናት ቁጥርም እየተበራከተ መምጣቱን ጥናቱ አመልክቷል፡፡
እ.ኤ.አ ከ2015 ጀምሮ በተደረገው በዚሁ ጥናት መሰረት፤ በአገሪቱ ያሉ ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ ህፃናት እጅግ አደገኛ ለሆኑ ሱሶች ተጋልጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ45 ሺ በላይ ዕድሜያቸው ከ4-15 ዓመት የሆናቸው ህፃናት፣ ለአደገኛ ሱሶች የተጋለጡ ናቸው ብሏል ጥናቱ፡፡
የህፃናቱ የአደንዛዥ እፆች ሱሰኝነት መበራከት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያመለከተው ጥናቱ፤ ከሱሰኛ ህፃናቱ መካከል ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፈልባቸው የግል አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎችና የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙ ጠቁሟል፡፡
ከዓመታት በፊት በግዮን ሆቴል ተካሂዶ የነበረውንና በአፍሪካ የህፃናት ፖሊሲ መድረክ የህፃናት ህጋዊ ከለላ ማዕከል ተዘጋጅቶ የነበረውን ጉባዔ መነሻ ማድረጉን የገለፀው ይኸው ጥናታዊ መረጃ፤ የህፃናቱ የአደንዛዥና አፍዛዥ ነገሮችና እፆች ሱሰኝነት ችግር ከመቼውም ጊዜ በላይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ብሏል፡፡
ወላጆች ከፍተኛ ገንዘብ እየከፈሉ ልጆቻቸውን የተሻለ ትምህርት ለማስተማርና ብቁ ዜጋ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉበት ሁኔታ እየተበራከተ መምጣቱን የጠቆመው መረጃው፤ በዛው መጠን ከየት/ቤቶቹ ደጃፍ ላይ እንደ አሸን በፈሉት የሱስ መለከፊያ ጎተራዎች ውስጥ እየገቡ በአደንዛዥ እፅ ሱሰኝነት እየተመረቁ የሚወጡ ህፃናት ቁጥር ተበራክቷል ብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ባሉና ስማቸው ባልተገለፀ አምስት ስመ-ጥር ት/ቤቶች ውስጥ በሚማሩ እድሜያቸው ከ7-15 ዓመት በሆናቸው ተማሪዎች ላይ ጥናት መደረጉን ያመለከተው መረጃው ጥናት ከተደረገባቸው 283 ተማሪዎች መካከል ግማሽ ያህሉ በት/ቤቶቻቸው አካባቢ በሚገኙ እንደጫት ቤትና ሺሻ ቤቶች ያሉ የሱስ መሸመቻ ጎተራዎች ደንበኞች ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች እነዚህን ቤቶች በየዕለቱ ይጎበኙዋቸዋል፡፡
ሱስ አስያዥ አደንዛዥ እፆች የተለያየ የዓይነትና መጠን እንዳላቸው ያመለከተው ጥናቱ፤ በት/ቤቶች አካባቢ በሚገኙ ህፃናት ሱሰኞች የሚዘወተሩት በቁም ቅዥት ዓለም ውስጥ የሚከቱ፣ የሚሸተቱና በያዙት ሱስ አስያዥ ሽታ ሳቢያ ሱሰኛ የሚያደርጉ የእፅ አይነቶች ናቸው፡፡ ለእነዚህ ተማሪ ህፃናት ሱሰኝነት መጋለጥ ዋነኛ ምክንያት ተደርጎ በጥናቱ የተጠቀሰው በት/ቤቶቹ አካባቢ ሆን ተብለው የሚከፈቱ ሺሻ ቤቶች፤ ጫት ቤቶች፣ ከረንቦላ ቤቶችና በአሁን ወቅት እየተላመዱ የመጡት የቀን ጭፈራ ቤቶች ናቸው፡፡ በከተማዋ በሚገኙ እንደ ቦሌ፣ መገናኛ ሲኤምሲ አካባቢ ባሉ የግል ት/ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ህጻናት፤ በተለያዩ ሱሶች በከፍተኛ መጠን እየተያዙ መሆናቸውን የጠቆመው መረጃው፤ በት/ቤቶቹ አቅራቢያ በሚገኙ መጠጥ ቤቶች ውስጥ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት ቦታች የሆኑ ህፃናት ሲጋራና በሲጋራ መልክ ተጠቅልሎ የተዘጋጀ ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ እፅ እንደሚያጨሱም በጥናቱ መረጋገጡን አመልክቷል፡፡ በአንዳንድ የሱስ መለከፊያ ሺሻ ቤቶችና ጫት መቃሚያዎች ላይ ተማሪዎች ከነዩኒፎርማቸው ማየት የተለመደ መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ፤ በየመጠጥ ቤቶቹ ጎራ ለይተው እያውካኩ መጠጣት፣ በቂማ ቤቶቹ ፈርሸው ሲቅሙ መዋል፣ የሺሻ ፓይፓችን እየሳቡ በጭሱ መዝናናት፣ አለፍ ሲልም በሲጋራ ወረቀቶች እየተጠቀለሉ በሚሸጥላቸው ካናቢስ መጦዝ … ቦሌ አካባቢ በሚገኙ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ በሚማሩ ህፃናት እየተለመደ መጥቷል፡፡ ህፃናቱ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የሚከለከል አሊያም የሚፈፀሙት ድርጊት እጅግ ለከፋ አደጋ የሚያጋልጣቸው መሆኑን አበክሮ የሚያስተምር አካል ባለመኖሩ ምክንያት ህፃናቱ አሁንም ወደ ጥፋት ጎዳናው ከማምራት አልተቆጠቡም፡፡
ለሱሰኛ ህፃናት ቁጥር መበራከት ዋንኛ ምክንያቶች ተደርገው ከተገለፁት ጉዳዮች መካከል የአቻ ግፊት፣ ተቆጣጣሪ ማጣት፣ ከጓደኛ ያለመለየት ፍላጎት፣ የቤተሰብ መፈናቀልና የጎዳና ህይወት መሆናቸውን ይኸው ጥናት አመላክቷል፡፡ አብዛኛዎቹ የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት፤ ኑሮአቸውን በጎዳና ላይ ካደረጉበት ጊዜ ጀምሮ ከእነሱ ቀድመው የጎዳናውን ህይወት የጀመሩ ጓደኞቻቸው የሚያደርጉት ነገር ሁሉ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ ቀድመው በሱስ የተያዙት ጓደኞቻቸው ደግሞ ሕፃናቱን ወደ ሱስ ገደል ጫፍ ይመሯቸዋል፡፡
ጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት ከሚያዘወትሩአቸው ሱስ አስያዥ አደንዛዥ ነገሮች መካከል እነሱ “ጡጦ” እያሉ የሚጠሩት፣ በአፍና በአፍንጫ የሚሳበውና ህሊናን የማሳትና የማደንዘዝ ባህርይ ያለው ነገር ዋነኛው ነው፡፡ አብዛኛዎቹ የጎዳና ተዳዳሪ ህፃናት፤ ከቫርኒሽ ቀለሞች፣ ከጫማ ማጣበቂያ ማስቲሽና “ቺፍቼ” እያሉ በሚጠሩት የናፍታ ፍሳሽ በሚያዘጋጇቸው (በአፍና በአፍንጫ የሚወሰዱ) አደገኛ አደንዛዥ ነገሮች አእምሮአቸውን ያደነዝዛሉ፤ ረሃብ፣ ብርድ፣ ውሃ ጥም፣ ድካምና ህመምን ያስረሳል በሚሉት በነዚህ ለጤና እጅግ አደገኛ በሆኑ ነገሮች እስከ እብደት ሊያደርሱ ለሚችሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡
የምግብ ፍላጎት ስለማይኖራቸውና ምግብ ሰለማይመገቡ በቀላሉ ለተለያዩ የጤና ችገሮች ይጋለጣሉ፡፡ አብዛኞዎቹ የጎዳና ተዳዳሪዎች እራሳቸውን እንዲያጠፉ ከሚያደርጓቸው ጉዳዮች መካከል ዋንኛውም የሱስ ተገዥነታቸው ነው፡፡ ራሳቸውን በተለያዩ መንገዶች ያጠፉ ሱሰኛ የጎዳና ህፃናት መኖራቸውንም ጥናቱ አረጋግጧል፡፡
እነዚህ የዚች አገር ተረካቢ ይሆናሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው ለጋ ህጻናት፣ ያለ ዕድሜያቸው የሱስ ተገዥ ሆነው ሲሰናከሉ ማየት ለማንኛውም ዜጋ ከባድ ራስምታትና የጊዜው የአደጋ ጥሪ ደወል መሆኑን የጠቆመው ጥናቱ፤ ይህንን ሁኔታ ለመቀየርና ህፃናቱን ከአደገኛ እፆች ሱሰኝነት ለመታደግ አሁንም አልረፈደም ይላል፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ እና በአማኑኤል ሆስፒታሎች ውስጥ እንዳሉት የሱስ መላቀቂያና ማገገሚያ ማዕከላት ሁሉ፤ ህፃናቱን ከአደገኛ ሱሰኝነታቸው ሊያላቅቁ የሚችሉ ማዕከላት በመገንባትና በህፃናቱ ህክምናና እንክብካቤ በመስጠት ከችግራቸው ማለቀቅ እንደሚገባም ጥናቱ በማጠቃለያው ላይ አስገንዝቧል፡፡ የህፃናትን ሱሰኝነት ለመከላከል ቤተሰብ፣ ትምህርት ቤቶች፣ መንግስትና ሁሉም ዜጎች ኃላፊነት እንዳለባቸው በጥናት ውጤቱ ላይ ተገልጿል፡፡ [ፎቶው ለማሳያ የቀረበ እንጂ አጫሾች ናቸው ለማለት እንዳልሆነ ይታወቅልን – የቅዱስ ዮሴፍ ተማሪዎች](መታሰቢያ ካሳዬ)
Lusif says
It is really sad. The cost of living is beyond the reach of large number of households and can afford. These group of households have no other alternative except allowing their child to toil on the street to feed himself and to bring some left over if that child can.
Others are well off who wanted to bring up their kids in ” best ” environment where everything is available and within reach. We often hear parents boast that their kid goes to such and such school, where the big guys’ kids attained. If one ask about the environmental quality and safety of the school, the automatic answer is ” ho, Ya. Such and such kids also attained there.” Even other would dare to say that someone’s ( high profile name ) kid is my son / daughter best friend and class mate. That means if someone’s son attained in that school, charges high fee the school is best and the parent need no to bother offering help to to his kid. The other is an attempt of creating safety cocoon around. The whole thing is about displaying status and competion among parents. The wellbeing, safety and quality of education of the child is secondary to none.
There are honest and innocent parents who invest everything they get on their children education. These parents are there whenever the child needs protection and help. At their spare and conducive time, they help their kids know how to become strong and humble human being.
There also other parents who have no time for their kids because of chaotic life demands and field work.
Kids are the responsibility of parents. A cohesive and harmonious community is a great help. In the well off neighbour hood individualism is getting foot hold. Nobody cares for anybody’s child.
These days the government seems has no any help. If one raise the issue with government official/cadre the response is denial or lack of foresight and commitment.
Have we often hear from seasoned political cadres that all social problems are the result of the fast moving and growing economic development. When the economic growth and development reach its pick and leveled down all these problems will vanish by themselves. So let us concentrate on building the economy. Do not wary we are on right track. Well, it looks consoling. However, how many kids we have to sacrifices until that period arrives.
I am a mother of two kids. I do not want anything undesirable to happen to my children, so other kids.
Every comes and go. Once kids go, it is almost impossible to bring back. I know every parent takes care his own kids, I want them to be more vigilant. That is all I have.
Goota says
The Tigre apartheid regime does this horrific crime on purpose. It wants to ensure that the next generation of Ethiopians become mindless addicts.
The South African apartheid regime was viciously promoting the sale of poisoned tobacco that was frequented by blacks. Woyanes in their own small ways are doing the same thing. Chat use is illegal in their Tigrai while it is promoted nation-wide.
Has Ethiopia ever encountered an enemy as evil as these Tigres?