
በወልዲያ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ከሶስት ሺህ በላይ የተለያዩ አይነት ተተኳሽ ጥይቶችን ሲያጓጉዙ የነበሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ማታወቁን ኢዜአ ዘገበ።
ተጠርጣሪዎቹ ኮድ 3-01470 አፋ በሆነ አነስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ጭነው ከቆቦ መስመር ወደ አፋር ክልል ሲጓዙ ህዳር 27/2013 ዓ.ም ሌሊት በጣቢያው ተቆጣጣሪዎች መያዛቸው ተገልጿል።

በተደረገው ፍተሻ 1 ሺህ 941 የብሬን ፣ 1 ሺህ 132 የክላሽ፤ 5 የብሬን ሽንሽን ጥይቶችና 3 የክላሽ ካዝና ተገኝቷል።
እንደ ኢዜአ ዘገባ ከሆነ አሽከርካሪውን ጨምሮ በዚሁ ወንጀል የተጠረጠሩ ሁለት ወንዶች እና ሁለት ሴቶች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ መታየት ጀምሯል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply