* “አሸባሪዎችን” ለይቶ የመያዝ “ልዩ ችሎታና ብቃት” ያለው ፖሊስ ያልያዘው ተጠርጣሪ አለ ሃና ላላንጎ የተባለችውን ተማሪ በሚኒባስ ታክሲ አፍነው በመውሰድ፣ በቡድን በመድፈርና ሕይወቷ እንዲያልፍ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙትን አምስት ተጠርጣሪዎች የፍርድ ቤት ጉዳይ በዝግ ችሎት መታየት ጀመረ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ለሦስተኛ ጊዜ ኅዳር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍርድ ቤት፣ ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ ፖሊስ ቀደም ባለው ቀጠሮ እንደሚሠራቸው ያስመዘገበውን ቀሪ የምርመራ ሒደት፣ ለችሎቱ ያስረዳበትና ተጠርጣሪዎቹን ያቀረበበት ሰዓት፣ ከሌሎች ቀናት የተለየ ነበር፡፡ ሟች ሃና ላላንጎ በቡድን ተደፍራ ሕይወቷ ማለፉ በመገናኛ ብዙኃን ከተሰራጨበት ጊዜ አንስቶ እያነጋገረ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ በየቀጠሮው ፍርድ ቤት የሚገኘው ታዳሚ ቁጥር … [Read more...] about የሃና ላላንጎ ጉዳይ በዝግ ችሎት ታየ
Archives for December 2014
“ሙሽራን ያላችሁ እስቲ እንያችሁ…”፤ [“የቲፎዞነት” ዘመን]
እንዴት ሰነበታችሁሳ! ሀሳብ አለን … ስብስባዎች ሁሉ … አለ አይደል… “እንዴት ሰነበታችሁ…” በሚል ብቻ ይከፈትና ወደ ጉዳዩ ይገባ! አሀ … “ክቡር እከሌ እከሌ፣” “ክብርት እከሊት እከሌ፣” “የተከበሩ እከሌ እከሌ” … ምናምን ሲባል የስብሰባው ሲሦ እያለቀ ነዋ! ለነገሩ … (“ለምን ይዋሻል!” የሚሉት ነገር ነበረ አይደል!) ብዙ ስብሰባዎች ላይ “እንትንህን እንደ ዳናኪል እንፋሎት እንዳላቦንልህ!” አይነት “የጉልበት ግማሹ ምላስ ነው…” ነገር በዝቷላ! (እኔ የምለው … አንዳንዱ መድረክ ላይ ወጥቶ እንዴት ነው እንዲህ ‘ልክ ልክ ማጠጣት’ የሚዋጣለት!) አንድ ወዳጃችን ሲነግረን አለቅየው ‘መጠመቁን’ ለበላዮቹ ለማስመስከር የማይሞክረው ነገር የለም፡፡ በተለይ ስብሰባዎች ላይ የሚናገረው ‘ቦተሊካ’ ነክ ንግግር ካርል ማርክስን ጢሙንና ጸጉሩን አርግፎለት ‘አይ ሮቦት’ ነገር … [Read more...] about “ሙሽራን ያላችሁ እስቲ እንያችሁ…”፤ [“የቲፎዞነት” ዘመን]
የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር
ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ - በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል። "እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል... ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።" እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም... ይመስላል። የዚህ ምስኪን ሰው ገጽታ … [Read more...] about የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር
የተዘጋውን የአረብ ሀገራት የኮንትራት ሰራተኛ አቅርቦትን ለመክፈት የወጣው ረቂቅ!
* ስለ ሰራተኞች መብት ጥበቃ መነሳቱ አልተዘገበም * በተወያይ ኤጀንሲዎች በኩል ግን ረቂቁ ውዝግብ አስነስቷል * ከዚህ ቀደም ያለ በኮንትራት ለተበተኑትስ ዜጎችስ ምን ታስቧል? አዲሱን መረጃ ያገኘሁት ሃገር ቤት ከሚታተመው ከአድማስ ጋዜጣ ላይ ነው፣ እንዲህ ይላል "ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግርና እንግልት ለማስቀረት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየውን አሰራር ለማስጀመርና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ውዝግብ አስነሳ፡፡" ... ወረድ ብለን ዝርዝር መረጃውን ስንቃኝ በዋናነት መታየት ያለበት አንኳሩ የሰራተኞች ይዞታና የመብት ጥበቃ ጉዳይ በዘገባው ላይ አልተካተተም። ይህም ይሁን ብለን ዝርዝሩን ስንቃኝ ከዚህ ቀደም በነጻ ያገኙትን ቪዛ በደላላ በየገጠር ከተሞች ሰብስበው እህቶቻችንን ከመላካቸው አስቀድሞ ፈቃድ ሲያወጡ ለመንግስት … [Read more...] about የተዘጋውን የአረብ ሀገራት የኮንትራት ሰራተኛ አቅርቦትን ለመክፈት የወጣው ረቂቅ!
የድል ፍሬ ፀሐይ
የሕይዎት ዋስትና ፤ የፍጥረቱ ሲሳይ ሃሌታዊ ጀምበር ፤ ለዚህች ማሕሌታይ የተስፋ ብርሃን ፤ የማለዳ ፀሐይ የድል በረከቱ ፤ መከራን ገላጋይ እፎይታን አስኮምኳኝ ፤ ሁሉንም አማላይ ኧረ ምን ነው ቀረሽ ፤ እባክሽ ቶሎ ነይ፡፡ አዝርቱን ውርጭ መታው ፤ ቀረ እንደ ጫጨ አውድማው ነጠፈ ፤ ዘር መክለፍት ተፈጨ ሁሉም በቁር ጠፋ ፤ ውሽንፍሩ አፋጨ ሕይዎት ያለው ፍጥረት ፤ በአጭሩ ተቀጨ የማለዳ ፀሐይ ፤ ሕይዎት መታደያ ምን ነው በአፍሪካ ፤ ምን ነው በኢትዮጵያ ሌሊቱ ረዘመ ፤ ምንድነው ምክንያቱ አትወጭም እንዴ! ፤ ገደለን ምኞቱ የድል ፍሬ ፀሐይ ፤ የፍጥረት ሕይዎቱ በነፍስ ድረሽልን ፤ ይንጋልን ሌሊቱ፡፡ ቁር የቀፈደደው ፤ ያስቀመጠው አስሮ ልሳኑ የተያዘ ፤ የደረቀው ከሮ በሙቀትሽ ይንቃ ፤ ይፈታ ሞት … [Read more...] about የድል ፍሬ ፀሐይ