• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የተዘጋውን የአረብ ሀገራት የኮንትራት ሰራተኛ አቅርቦትን ለመክፈት የወጣው ረቂቅ!

December 3, 2014 07:14 am by Editor Leave a Comment

* ስለ ሰራተኞች መብት ጥበቃ መነሳቱ አልተዘገበም
* በተወያይ ኤጀንሲዎች በኩል ግን ረቂቁ ውዝግብ አስነስቷል
* ከዚህ ቀደም ያለ በኮንትራት ለተበተኑትስ ዜጎችስ ምን ታስቧል?

አዲሱን መረጃ ያገኘሁት ሃገር ቤት ከሚታተመው ከአድማስ ጋዜጣ ላይ ነው፣ እንዲህ ይላል “ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግርና እንግልት ለማስቀረት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየውን አሰራር ለማስጀመርና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ውዝግብ አስነሳ፡፡”  … ወረድ ብለን ዝርዝር መረጃውን ስንቃኝ በዋናነት መታየት ያለበት አንኳሩ የሰራተኞች ይዞታና የመብት ጥበቃ ጉዳይ በዘገባው ላይ አልተካተተም። ይህም ይሁን ብለን ዝርዝሩን ስንቃኝ ከዚህ ቀደም በነጻ ያገኙትን ቪዛ በደላላ በየገጠር ከተሞች ሰብስበው እህቶቻችንን ከመላካቸው አስቀድሞ ፈቃድ ሲያወጡ ለመንግስት ያቀረቡት የገንዘብ መያዣ በደል ደርሶባቸው ለሚመለሱ ዜጎች ካሳ ሲከፈል አላየንም አልሰማንም። ከሁሉም የሚያመው ሰራተኞች ሲላኩ ለሚደርስባቸው አደጋ ኢንሹራንስ ሳይቀር ገንዘብ አስከፍለው የላኳቸው ቢሆንም በተበደሉበት በደል ተፈጽሞባቸው ሃገር ቤት ሲገቡ በከፈሉት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ አይደረጉም። የሰራተኞችን መብት አሟልተው ስራ ለማሰማራት እንግዲህ ውል ገብተው በወሰዱት ፈቃድ ልክ ውል ሲያፈርሱ ህግ አስፈጻሚ አካላት በኩል በዝምታ የታለፉት የእኛ ስራና ሰራተኛ አገናኝ ደላላ “ኤጀንሲዎች” በአዲሱ ረቂቅ ያነሱት ተቃውሞ “ቅድመ ሁኔታዎች አያሰሩንም” የሚል መሆኑን እያመመኝ አነበብኩት! እንቀጥል …

በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ሰራተኞችን የሚልኩ ኤጀንሲዎች ያሰሙት ቅሬታ የስራ ፈቃዱን ለማግኘት “ከአንድ ሚሊዮን እስከ አምስት ሚሊዮን ብር ካፒታል ሊኖረው ይገባል” መባሉና “ለሰራተኛው መብትና ደህንነት ዋስትና ማስከበሪያ የሚውል 100 ሺህ ዶላር ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ በዝግ ሂሳብ የማስቀመጥ ግዴታ አለበት” መባሉ ነው። ጋዜጣው ኤጀንሲዎች ለስራ ወደ ውጭ አገር የላኳቸውን ሰራተኞች በሚሔዱባቸው ሃገራት ላሉ ኢምባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቶች በ15 ቀናት እንደሚያስታውቁ ይጠቁማል።

የኤጀንሲዎች የአዞ እንባ

ኤጀንሲዎች ይህ መሰሉ ረቂቅ ህግ እንደማያሰራቸው እንዲያውም “በውጭ ሃገር ስራ ለማሰማራት የሚፈልጉትን ዜጎች እድል ያጠባል፣ ህገ ወጥነትን የሚያባብስ ነው” ሲሉ ህመሙን የመከረኞቹ ህመም በማድረግ የአዞ እንባ የማንባት አይነት ቅሬታ መሰማታቸውን በአድማስ ጋዜጣ ዘገባ ተጠቅሷል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ ኤጀንሲዎች ረቂቁን ህግ በወይይቱ የተቃወሙበትና ያልደገፉበት ዋንኛ ምክንያታቸው የተደነገገውን ቅድመ ሁኔታ ለማሟላት እንደሚከብድ መሆኑንም ጋዜጣው ያስረዳል።

ዳግም እንዳናነባ …!

ከወራት በፊት ጀምሮ “ወደ አረብ ሃገራት የተዘጋው የኮንትራት ቪዛ ይከፈታል!” የሚል መረጃ በሰፊው በመሰራጨት ላይ እንዳለ በሹክሹክታ ከሰማን ወዲህ ረቂቁ ለውይይት መቅረቡን ይህው ሰማን። ከዚሁ ጋር ባያያዝኩት የEBC TV ዘገባ እንደምትመለከቱት የዜና ዘገባ ከወራት በፊት የተባበሩት ኢምሬትን የጎበኙት ፕሬዘደንት ዶ/ር ሙላቱና የኢምሬት አምባሳደር አቶ አብድልቃድር የተዘጋውን የአረብ መንገድ መቸ እንደሚከፈት ተጠይቀው ሲመልሱ ህግ ሆነ መመሪያ እየወጣ መሆኑን ጠቁመው ነበር። ከዚህ ጋር በማያያዝ በሰጡት መግለጫም ከአሁን ቀደም ከአረብ ሃገራት ጋር ያልነበረው የሁለትዮሽ ስምምነት በቀጣይ መከወን እንዳለበት ገልጸውም ነበር። ይህ መግለጫ በተነገረ ማግስት በቪዛው ንግድ ተሰማርተው ከገጠር እስከ ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ እህቶቻችን ለሳውዲ “ገበያ” ያቀረቡት ባለ ኤጀንሲ ደላሎች ጅዳና ሪያድ መምጣት መጀመራቸው መረጃ ቢጤ አቅርቤም ነበር። አሁን በውስጥ አዋቂዎች የሰማነው፣ የተባለው ሁሉ እውን እየሆነ፣ እውነቱ እየጠራ የሄደ ይመስላል!

eth in the arabiaከዚህ ቀደም በሁለት ሃገራት መካከል ስምምነትና በቂ ዝግጅት ሳይደረግ በሳውዲ ብቻ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጥ ዜጋ  የህግ ሽፋን ህጋዊ ፈቃድ ባላቸው ኤጀንሲዎች በየገጠር ከተሞች ተግዘው በተለያዩ ከተሞች ተበትነዋል። ዛሬ በኮንትራት የመጡት “ያሉበትን ይዞታ እንዲህ ነው” ብሎ መረጃ መስጠት ቀርቶ፣ የትና በምን ሁኔታ እንደሚገኙ የሚያውቁ ኤጀንሲዎችም ሆነ የመንግስት ተወካዮች የሉንም የምለው በእርግጠኝነት ነው። በተደጋጋሚ ከሚደርሱኝ መረጃዎች መረዳት እንደቻልኩት በአሁኑ ሰዓት መግቢያ መውጫው ጠፍቶባቸው፣ በደልን እያስተናገዱ የሚንገላቱት በርካታ እህቶች በየቤቱ እንዳሉ አውቃለሁ። በዚህ መሰሉ የተወሳሰበ ችግር ዜጎች እየተሰቃዩ፣  መብታቸው የሚያስጠበቅ ስራ እየተሰራ በሌለበት ሁኔታ ሌላ እንባ ልናነባ የተቃረብን ይመስላል! የኮንትራት ሰራተኞችን አበሳ ብዙ ነው፣ የሚሰራው ታስቦና ተጠንቶ ስላልሆነ፣ መብታችን የሚያስጠበቅልን ስለጠፋ ተዋርደናል። አሁን ድረስ በዚህ ዙሪያ ያገባናል ብለን  ስንጽፍና ስንናገረው እንደ ተቃዋሚ እየታየንም ቢሆን ግፍ ሰቆቃና ስቃዩን ሊያሰለች በሚችል ስፋትና ጥልቀት ጽፈነዋል፣ ተናግረናል! ሰሚ ግን የለም!

በህግ መመሪያ የተቀመጠው የመንግስት ዲፕሎማቶች ቀዳሚ ስራ ባሉበት ሃገር የሚገኙ ህጋዊም ሆኑ ህገ ወጥ ዜጎችን ሰብአዊ መብት ረገጣ እንዳይደርስባቸው መከላከል ቢሆንም ይህ እየተሰራበት አይደለም። የህገ ወጦችን ቀርቶ በኮንትራት ሰራተኛና አሰሪ ስምምነት የመጡ ዜጎችን መብት ማስከበር አልቻሉም! የቪዛ ውል ማስፈጸሚያ ገንዘብ እየሰበሰቡ ባጸደቁት የኮንትራት የስራ ውል ላይ የተጻፉት ስምምነቶች የዜጎች ይዞታ የመከታተልና የማስፈጸም ሃላፊነትን ሲወጡ አላየንም! እውነቱ ይህ በመሆኑ ሰብዕናችን መርከስ ይዟል፣ ግፍ እየተፈጸብን ነው። በዚህ ሁኔታ ረቂቁ ጸድቆና በተግባር ውሎ ዳግም እንዳናነባ ያሰጋል!

ግልድ መሆን ያለበት ነባራዊው እውነታ

የረቂቁ ጉዳይ በእንዲህ እንዳለ ከኢትዮጵያ መንግስት አስቀድሞ ከኢትዮጵያ የኮንትራት ሰራተኞች እንዳይመጡ ያገደው የሳውዲ መንግስት እገዳውን እስካሁን አላነሳም። በዚህ ላይ መንግስት ከአረብ ሃገራት በኩል እግዱ ተነስቶ ሰራተኞች እንዲያቀርብ ጥያቄ እየቀረበለት መሆኑን ደጋግመን ሰምተናል። ከአረቦች በኩል ግን የምንሰማው ለየቅል ነው!

ወደ ረቂቁ ስንመለስ፣ ብዙዎቻችን የሚያሳስበን በማህበራዊና ሰራተኛ ሚኒስትር ለኤጀንሲዎች ውይይት የቀረበው ረቂቅ ህግ በሰራተኞች ይዞታና መብት ጥበቃ ዙሪያ የተነሳ ጉዳይ አለመኖሩም ነው። በአድማስ ጋዜጣ ዘገባ በማህበራዊና ሰራተኛ ሚኒስትር በቀረበው ረቂቅ ኤጀንሲዎች መወያየታቸውን ሲያስረዳ ፍቃድ ለመውሰድ የተጣለባቸውን ከፍተኛ ገንዘብ የማስያዝ፣ ሰለሰራተኞች እድሜ የትምህርት ደረጃ ገደብ እና ሰራተኞችን በሚሄዱበት ሃገር ኢምባሲና ቆንስል መ/ቤት በ15 ቀን ውስጥ ከማስመዝገብ ቅድመ ሁኔታ ያለፈ አለመወያየታቸውን የቀረበው ዘገባ ያስረዳል።

በረቂቁ ላይ ሰራተኞች ቢያንስ እስከ ስምንተኛ ክፍል በላይ የሆኑት ብቻ እንደሚያካትት ከመጠቆሙ ባለፈ ሰራተኞች ማግኘት ስላለባቸው በቂ ስልጠናና ተዛማጅ ቅድመ ዝግጅት በቀረበው ረቂቅ ቀርቦ ለውይይት አለመደረጉ ያሳስባል። ከዚህ ቀደም ድህነትና የኑሮ ውድነቱን ተከትሎ በልጆቻቸው ህይወታቸውን ለመለወጥ የቋመጡ ወላጆች በደላሎች ቀቢጸ ተስፋ ተታልለውና የተሳሳተ የእድሜና የትምህርት መረጃና የመጓጓዣ ሰነድ አቅርበው ከሃገር እንዳይወጡ የተሰራውን ስራ የሚከላከል ዘዴ በረቂቁ አልቀረበም። አለም አቀፍ የሰራተኛ ህግንና ሰብአዊ መብት ማስከበሪያ ድንጋጌዎችን ባገናዘበ መልኩ ሰራተኞች ስለሚከፈላቸው ክፍያ፣ ስለጤና፣ ስለ እረፍት ሰአታቸው እና ስለመሳሰሉት መሰረታዊ የኮንትራት ሰራተኞች አንገብጋቢ ጥያቄዎች  ውይይት ሳይደረግበት ስለኤጀንሲዎች ፈቃድ ማግኘት ቅድመ ሁኔታ ውይይት መቅረቡ ያሳስባል። በረቂቁ ውይይት ከመደረጉ አስቀድሞ ኤጀንሲዎች ከዚህ በፊት ስላነጋገሯቸው ዜጎች ነባራዊ ይዞታና ሁኔታ ፣ አድራሻና ያሉበትን ሁኔታ በዝርዝር መረጃ አላቀረቡም። በላኳቸው ሰራተኞች ላይ ለተፈመውና እየተፈጸመ ላለው በደል ተጠያቂው ሳይታወቅ ስለመጭው ፈቃድ አወጣጥ ከኤጀንሲዎች ጋር በረቂቁ ዙሪያና መስፈርት ዙሪያ  መወያየቱ ጠቃሚ አይመስለኝም።

የኮንትራት ሰራተኞች ጉዳይ ሲነሳ በየአረብ ሃገራት ያሉትን ኢምባሲና ቆንስል መስሪያ ቤቶች ለዜጎች በሚሰጡት ያልተሟላ ግልጋሎትና ያልሰመረ የመብት ማስጠበቅ ይጠቀሳል። ይህ ለምን ሆነ ሲባሉ የሰራተኛና በበጀት እጥረት እንዳለባቸው አዘውትረው ይናገራሉ። በዚህ  መንገድ አሁን ድረስ ስለሚንከላወሱት የኢምባሲና የቆንስል መ/ቤቶች ረቂቁ ምን ይላል? የሚለው እንዳለ ሆኖ በሃገር ቤት ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ዝግጅት፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነት በረቂቁ ውይይት አልተነሳም።

እልፍ አእላፍ የኮንትራት ሰራተኞች አሁን ያሉበት ይዞታ በውል ሳይመረመርና ሳይታወቅ እየተንገዋለለ ባለበት ሁኔታ የተዘጋውን ለመክፈት ሂደት ግልጥልጥ አለማለት ያስፈራል። ከዚህ በፊት በኮንትራት የገቡት ጉዳይ ገለል አድርጎ ስለ አዲሱ ህግና መመሪያ እንነጋገር መባል ችግሩን ያገዝፈዋል እንጅ አይቀርፈውም። ይፋ መውጣት የጀመረው ረቂቁ ህግና በዚህ ጫፍ ያለው ዝግጅት የተዳከመ አለያም የለም የሚባል አይነት መሆኑ አሁንም የዜጎችን አበሳ በቅርብ ለምንመለከተ ውን  ዜጎች ያሳስበናል። መፍትሄው በአረብ ሃገራት ያሉትን ዜጎች ጨምሮ የሁሉም ባለድርሻ አካላት በረቂቁ ህግ ተሳትፎ ሊያደርጉበት ይገባል። በፈለገው መንገድም ይሁን በረቂቁ ህግና መመሪያ ዙሪያ ግልጽና ጥልቅ ውይይት ካልተደረገ አሁንም ዳግም እንደምናነባ ልብ ያለው ልብ ይበል!

ጆሮ ያለው ይስማ!

ቸር ያሰማን!

ነቢዩ ሲራክ
ህዳር 24 ቀን 2007 ዓም

አዲስ አድማስ ላይ የወጣው መረጃ እንዲህ ይነበባል፡፡ ፎቶዉንም የወሰድነው ከዚሁ ጋዜጣ ነው፡፡

የውጭ አገር ሥራ ስምሪት ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው

* ፈቃድ ለማግኘት ከ1ሚ. ብር በላይ ካፒታልና 2 ሚ. ብር ዝግ ሂሳብ ያስፈልጋል
* ኤጀንሲዎች ከተጓዥ ክፍያ ሊጠይቁ አይችሉም
* 8ኛ ክፍል ያላጠናቀቀና የሙያ ማረጋገጫ የሌለው መሄድ አይችልም
* ባለፉት 7 ወራት 50ሺ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ ጉዞ የመን ገብተዋል፡፡

ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግርና እንግልት ለማስቀረት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየውን አሰራር ለማስጀመርና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ውዝግብ አስነሳ፡፡

በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ወደ ውጭ አገር ሰራተኞችን የሚልኩ ኤጀንሲዎች፣ የግለሰብ ድርጅት ከሆነ አንድ ሚሊዮን ብር የሽርክና ማህበር ከሆነ ደግሞ አምስት ሚሊዮን ብር ካፒታል ሊኖረው ይገባል ይላል፡፡ ኤጀንሲው ለሰራተኛው መብትና ደህንነት ዋስትና ማስከበሪያ የሚውል 100 ሺህ ዶላር (ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ) በዝግ ሂሳብ የማስቀመጥ ግዴታ አለበት፡፡

ኤጀንሲዎች ለስራ ወደ ውጭ አገር የላኳቸውን ሰራተኞች ለኢትዮጵያ ኤምባሲ በ15 ቀን ውስጥ ማስመዝገብና የስራ ፈቃድ ማግኘታቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ለሚኒስቴሩ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ኤጀንሲዎች ለሚሰጡት አገልግሎት ምንም ዓይነት ክፍያን መጠየቅ አይችሉም፡፡ ረቂቅ አዋጁ በውጭ አገር ስራ ለመሰማራት የሚፈልጉ ዜጎችን ዕድል የሚያጠብና ህገ ወጥነትን የሚያባብስ ነው ሉ በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ ኤጀንሲዎች በስራው ለመሰማራት የሚያስችሏቸውን መስፈርቶች በሙሉ አሟልተው ለመቅረብ በእጅጉ እንደሚቸገሩና ረቂቅ አዋጁ መሻሻልና መታረም እንደሚገባውም ተናግረዋል፡፡ የአረብ አገራት ጉዞ በመንግስት ከታገደ ወዲህ ባሉት ሰባት ወራት 50 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን የመን መግባታቸውንና ባለፈው ጥቅምት ወር ብቻ በህገወጥ መንገድ የመን የገቡ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ስምንት ሺህ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት አመልክቷል፡፡

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
Copyright © 2026 · Goolgule