የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ሕወሃት) የፈጠረው የብአዴን ታጣቂዎች በመተማ ከተማ “በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች” በሚል ሁለት ነዋሪዎችን መግደላቸው፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸው እንዲሁም ከሃምሳ በላይ ማቁሰላቸው ተሰማ።
የብአዴን አባላት እና መሪዎች የዐማራን ሕዝብ እያሰቃዩ እና እያስፈጁ የሚያካብቱት ማንኛውም ሃብት በክህደትና በግፍ የተሰበሰበ በመሆኑ ለህዝብ የሚያስረክቡበት ግዜ ሩቅ አይደለም።
ለዚህ የክህደት ተግባራችው ተገቢውን ቅጣት ያገኛሉ፣ በባህርዳር እና በጎንደር በሰፊው እየተሳሳቡ አገር እየዘረፋ መሆኑን እያንዳንዷንም ተግባራቸውንም እየተከታተልን ዝርዝር ይፋ እናደርጋለን።
እነኝህ ስግብግቦች በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ከተማ፣ በሕግ ወጥ መንገድ የተሰሩ ቤቶች ናቸው ያሏቸውን ቤቶች ለማፍረስ በሚሞክሩበት ጊዜ፣ ከነዋሪው በተነሳዉ ተቃዉሞ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት፣ የሕወሃት ብአዴን ታጣቂዎች ሁለት ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሶስት ለሞት የሚያደርስ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከአምሳ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። (ምንጭ፦ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት Dr.Getachew Reda ጠቅሶ መስከረም ፱ ቀን ፪ሺህ፰ ዓም የላከው መረጃ)
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡
Leave a Reply