• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በሳውዲ አፈሳው ተጠናቅሮ ቀጥሏል

August 22, 2014 12:39 am by Editor Leave a Comment

ማለዳ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ አፈሳ ማድረጋቸውን የሪያድ ምንጮች ገለጹ። የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ህገወጥ የውጭ ሃገር ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚገልጸውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የፀጥታ ሃይሉ በወሰዱት እርምጃ ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ እትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሳውዲን ምድረ ለቀው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወሳል።

eth saudi 1ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ ከስደት ተመላሽ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በወቅቱ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ እስኪረጋጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም ከስደተኛው ጋር ፎቶ በመነሳት በኢቲቪ ሲሰራጭ ከነበረው ሰፊ የዜና ሽፋን ባሻገር ስደተኛው ምንም አይነት ማቋቋሚያም ሆነ ድጋፍ እንዳልተደረገለት ይነገራል።

በተለይ የስደት አለም ህጻናት ልጆቻቸውን ታቀፈው ለሃገር የበቁ እናቶች ለጎዳና ተዳዳሪነት የተዳረጉበት አስዛኝ ታሪክ የአብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ሆድ አላውሷል።

መንግስት በወቅቱ አዲስ አበባ በስደተኞቹ እንዳትጨናነቅ የስደተኞቹ ጉዳይ በየክልሉ ባለስልጣናት ይታያል በሚል ሽፋን በመቶሺህ የሚቆጠረውን ስደተኛ በየጉራጉሩ ወሽቆ ነገሮቹን ለማድበስበስ ቢሞክረም አብዛኛው ወገኖች በቋፍ ላይ ያለችውን ህይወታቸውን ለመታደግ አቅም ያለው አይቀሬውን ሞት በመጋፈጥ፤ በህይወቱ ቆርጦ ሳውዲ አረቢያ ለመግባት ቀይ ባሀርን በጀልባ አቋርጧ ለዳገም ስደት ተዳርጓል።eth saudi2

በአንጻሩ በሰው ሃገር ወልዶ ከብዶ በወቅቱ ያገኛት በነበረች የዕለት ገቢው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ የስደት አለም ጎጆውን አሙቆ ያለጥሪት ይኖር የነበረው አባወራ ያቺን ቀውጢ ወቅት መቋቋም ተስኖት የቤተሰቦቹን ህይወት ከወረበሎች ለማዳን ወደ ሃገሩ እግሬ አውጪኝ ቢልም ያልጠበቀው ገጥሞት የሞቀ የስደት ዓለም ትዳሩን መቅኔ ያሳጣውን የመንፉሃው ሁከት እየረገመ በገዛ ሃገሩ ሰማይ ተድፍቶበት ለልጆቹ የዕለት ጉርስ ዳቦ መግዣ አጥቶ የህጻናቱን ስቃይ እና መከራ ላለማየት እግር ወዳመራው ሲኳተን በረሃ በልቶት እንደወጣ የቀረውን ከሳውዲ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያዊ ቤት ይቁጠረው።

ይህ ባለበት ሁኔታ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ሐሙስ ዕለት ሐሙስ ባደረጉት የተጠናከረ የቤት ለቤት ፍተሻ ከ1 ሺሕ በላይ ህገ ወጥ ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የሚናገሩ ምንጮች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን መሆናቸው ጉዳዩን የበለጠ አሰደንጋጭ ያደርገዋል። የፀጥታ ሃይሉ ከህብረተሰቡ በሚቀርብላቸው መረጃ መሠረት ዘመቻውን በቀጣይነት በሪያድ ከተማ በተለምዶ ነሲም አል ሃማም እና ጉቤራ እየተባሉ የሚጠሩ መንደሮችን በማማከል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከውስጥ አዋቂ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል።

ከአንድ ወር በፊት በሪያድ ከተማ የአንድ ወህኒ ቤት ግርግዳ ደምርሰው ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ቁጥሩ በውል የማይታወቅ እስረኞች ማምለጣቸው ይታወሳል። ሐሙስ መንፉሃ ውስጥ በተካሄደው የቤት ለቤት ፍተሻ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለደረሰው እንግልት ወደ ሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ባደረኩት ጥረት አንድ ስሜ እንዳይገለጽ ያሉ ዲፕሎማት የቤት ለቤት ፍተሻው በኢትዮጵያውያኖች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እንዳልነበረ ገልጸው በዘመቻው ወቀት ከፍተኛ የሳውዲ ፀጥታ ሃይል መኮንኖች እና የመዲናይቱ ባለስልጣናት የቅርብ ክትትል እና ቁጥጥር ያደርጉ እንደነበር ተናግረዋል።eth saudi 5

ሲቀጥሉም እርምጃው በባህር የመጡ የመኖሪያ ፈቃድ በሌላቸው ህገወጥ የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ብቻ ያነጣጠረ እና በየትኛውም ዜጋ ላይ ምንም አይነት እንግልት ያለተፈፀመ ጥንቃቄ የተሞላበት ዘመቻ እንደነበር አረጋግጠናል ብለዋል። በማስከተል “ትላንት የሸኛችኋቸውን ኢትዮጵያውያን ደግማችሁ ዛሬ ስትሸኙ ምን ይሰማችኋል?” ላልኳቸው ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡኝ ተሰናብተውኛል።

ዛሬ ማለዳ መንፉሃ ውስጥ በሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ተካሄደ በተባለው የቤት ለበቤት አፈሳ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ወህኒ ከሚገኙ ወገኖች መረጃ በማሰባሰብ በሰፊው ለመዘገብ የማደርገው ጥረት ይቀጥላል።

Ethiopian Hagere Jed Bewadi በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የላኩት

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule