• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ

September 19, 2023 04:35 pm by Editor Leave a Comment

በቦሌ ክፍለ ከተማ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ በአማራ ክልል ለሚንቀሳቀሱ ጽንፈኛ ሀይሎች ሊተላለፉ የነበሩ የተለያዩ ወታደራዊ ቁሳቁሶች እና ሰነዶች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

ጌታሁን አስፋው ጌታሁን የተባለ እና በአማራ ክልል የህዝብ ሰላም እና ጸጥታን ለሚያውኩ ጽንፈኛ ሀይሎች የሎጀስቲክስ አቅራቢ እንደሆነ የተጠረጠረ ግለሰብ በክፍለ ከተማው ወረዳ ሁለት የሚገኝ ቤትን በመከራየት የተለያዩ ወታደራዊ ቁሰቁሶችን በማከማቸት ለጽንፈኛ ቡድኖቹ ለማቅረብ በመንቀሳቀስ ላይ እያለ በጸጥታ ሀይሎች ክትትል ሊደረስበት ችሏል፡፡

የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ፣ የአዲስ አበባ ከተማ የጸጥታ ዘርፍ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ባካሄዱት ኦፕሬሽን ግለሰቡ ከተከራየው ቤት የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች፣ የመካከለኛ እና የረጅም ርቀት ወታደራዊ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ልዩ ልዩ ትጥቆች እና ወታደራዊ አልባሳት፣ የተለያዩ ሰነዶች እና ጽንፈኛ ሀይሎቹ የሚጠቀሙባቸው ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ከመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የጸጥታ አካላት ውጭ በግለሰቦች እጅ ሊኖር የማይገባ የከፍተኛ ርቀት ወታደራዊ የመገናኛ መሳሪያም በቁጥጥር ስር ከዋሉ ቁሳቁሶች መካከል የሚገኝበት እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡

ተጠርጣሪው ግለሰብ የተለያዩ ስሞችን በመጠቀም መታወቂያዎችን በማውጣት ሲንቀሳቀስ የነበረ ሲሆን ከአማራ ክልል በመሰወር በአዲስ አበባ ከተማ የግለሰብ ቤት በመከራየት ለጽንፈኛ ሀይሎች ሎጀስቲክስ ሲያሰባስብ እና ስልጠናዎችንም ሲሰጥ እንደነበረ ለጸጥታ ሀይሎች የደረሰው መረጃ ያመለክታል፡፡ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተቀናጀ ክትትል እየተደረገ ሲሆን ተጨማሪ ምርመራም እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: amhara region, ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule