• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ክፋት በዛ

November 17, 2015 12:17 am by Editor 1 Comment

ክፉ ቀን ብዙ ክፉ ምግባሮች ይዞ ይመጣል።

በቀይሽብር ወቅ በመቀሌ ከተማ ያጋጠመ አንድ የክፉ ምግባር ምሳሌ ነበር።

ዘስላሰ የተባለ ወጣት በፀረ ደርግነት ተጠርጥሮ የቀይ ሽብር ሰለባ በመሆን በባዛር እየተባለ የሚታወቀውና አሁን በስሙ ዘላሰ የተሰየመው የአፄ ዮሐንስ ቤተ መንግሥት ፊትለፊት የሚገኝ አደባባይ ይረሸናል። ወላጅ እናቱ በደርግ ወታደሮች ተገድደው እልልል እያሉ፣ እያጨበጨቡ ደስታቸው እንዲገልፁ ተደርገዋል።

ያ ቀይ ሽብር ክፉ ቀን የወለደው ጥቁር ጠባሳ ጥሎ አልፏል። አሁንም ይሄ ጥቁር ታሪክ ዳግማዊ ትንሳኤውን አግኝቷል።

የጥቁር ታሪክ ባለቤት የሆነችው የሰሜን ወሎ ዞን፣ ቆቦ ወረዳ 027 ቀበሌ ነዋሪ እናት ወይዘሮ ብርቱኳን ዓሊ ነች። የ5 ዓመት ልጇን በረሃብ አጥታ እያነባች ለቢቢሲ የሰጠችው ቃለ ምልልስ ኢህአዴግን አስቆጥቶ ልክ እንደ የዘስላሰ እናት አስገድደው እንድታስተባብል አድርጓታል።

የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ልክ እንደ የደርግ ወታደሮች ሁሉ ወይዘሮ ብርቱኳን የልጇን ሞት ሃዘን እንዳትችል እያዋከቡና እያስፈራሩ እንድታስተባብል አስገደዷት። ይባስ ብሎ የአሜሪካ ድምፅ VOA ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩም የወንጀሉ አካል መሆኑ እጅግ ያሳዝናል።

ግርማይ ገብሩ የህወሓትን ሴራ እያወቀው ልጇ በድንገተኛ ሞት እንዳጣች፣ በሬ፣ ላም፣ እህል ወዘተ እንዳገኘባት መዘገቡ ያስገምተዋል። እዚህ ላይ የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ያስተላለፉት በቀጣይ ልጆችዋ በረሃብ እንዳታጣ መስጋትዋ ገልፃለች። ግርማይ ግን ከነሱ ብሶ መዘገቡ ያሳዝናል።

ህወሃት “የትግራይ ገበሬ 100% ሞዴል፣ የአንድ ዓመት ምርት 113 ሚሊዮን ኩንታል አመረተ”፤ ብሎ የሚዋሽ ድርጅት መሆኑ እያወቀና ጋዜጠኞች እንደሚሄዱ አውቀው የጠቀሳቸው ከብቶችና እህል አስቀድመው በቤትዋ ማስቀመጥ እንዴት ያቅታቸዋል ብሎ ያስባል?

ቅለል ያለው … ሆነ እንጂ የቢቢሲ መግለጫዋ ያስኮነነው ህወሃት UN በየቀኑ ሁለት ሰዎች ድርቅ ባስከተለው ረሃብ እየሞቱ እንዳሉ ገልፀዋል።

የቀይ ሽብር ተግባር በድርቅ ሲደገም እጅጉን ያማል። (Amdom Gebreslasie)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    November 18, 2015 11:53 pm at 11:53 pm

    >>>በቅርቡ በተካሄደው የሕወሓት 12ኛ ጉባዔ ላይ በነባሩ መሥራች አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይ ስብሃት) ተጠቁመው የድርጅቱ ማዕክላዊ ኮሚቴ አባል ሆነው የተመረጡት የሕግ መምህሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ ‹‹እኔ የምለው በሙሉ የመንግሥት አቋም ነው፡፡ የተናገርኩት መንግሥት ማለት ስለፈለገው ነው፡፡ አትቆራርጡት፡፡ እንዳለ አስተላልፉት፤››ሲሉ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋዜጠኛ ነገሩት፡፡

    __ ይህንን እኛም በምርጫው ማግስት’እንደወረደ ከወርቃማ ህዝቦች ሳይበረዝ ሳይከለስና ሳይሸራረፍ ዜና እንደምንሰማ አውቀናል..የመንግስት ኮምንኬየሽንን ቦታ ከድምፅ ማጉሊያ ጋር በመፃ ይዘውት የነበሩት ሁሉ በህወአት ጥላ ሥር ሆነው የግልና ክልላዊ የበታችነት አመለካከታቸውን መቅረፊያ መዝለፊያና የመሳደቢያ መድረክ፣ ያለነጥብ ቃላት ሲደረድሩ (GOOD) ጉድ(ፅቡቅ) ብለናል::‹‹እንግዲህ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ አሉ የምትሉዋቸውን ጥያቄዎች ማንሳት ትችላላችሁ፤›› በማለት ነበር ግልፅና ተጠያቂነት ያለው ደፋር፣ብሔራዊ ቡድን የአምስት ዓመት ኮንትራቱን ለመጨረስ ‹‹አሁንም በመጥፎ ሥራው መጠየቅ ያለበት ኃላፊ ካለ ይጠየቅ!፡፡ መሰቀል ያለበትም እሱ ከሆነ የሚገባው ይሰቀል!፡፡ ሥርዓቱን ለማስተካከል ስንንቀሳቀስ ይህንን በማደናቀፍ በግልጽ ሚና ያላቸው ወገኖችና ተቋማትም ካሉ መፍረስ ያለበት ይፍረስ! መመታት ያለበት ይመታ! ›› ሲሉ መንግሥት የተግባር ዕርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ አቋም መያዙን ተናግረዋል፡፡

    **አሁን በድርቅና በርሃብ መካካል ያለው የርዮተዓለምና የአተረጓጘም ልዩነት በህወአት/ኢህአዴግ ምሁራን፣ በቢቢ ጋዜጠኞች፣ አስለማኝና አበዳሪ ወይም (partners) በእያሉ በሚያቀማጥሏቸው ኪራይ ሰብሳቢ የውጭ ሕዝቦች የርሃብተኛ ቁጥር፣ የዕርዳታው በገፍና በፍጥነት መድረስ ላይ ማን ነው በበለጠና በሰለጠነ መልኩ የዋሸው? የሚለው ፍትጊያው ቀጥሏል።
    “ርሃብተኞችም የእውነት ዝናብ እስኪመጣ የርሃብን ዕንባ ያዘንባሉ!።
    … “ቢቢሲ ስለተከሰተው ድርቅ ቢጽፍ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብን የማንቃት ዓላማ ይኖረዋል ከሚል ፍላጐት እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ‹‹የሄዱበት መንገድ ግን ሌላ ነው፡፡ ያቀረቡትም ውሸት ነው፡፡ ዘገባው የተሠራው ከቆቦ ነው የሚሉት፡፡ ልጇ የሞተባት እናት ግን ከመርሳ ናት፤›› በማለት በዘገባው ሐሰተኝነት ‹‹ያልተቀናጀ የሰነፍ ሥራ ነው የሠሩት፣ያሳዝናል፤›› ብለዋል፡፡… አቶ ጌታቸው ረዳ፡፡ ‹‹እስከ ዛሬ በረሃብ ምክንያት ለሞት የተዳረገ ሰው የለም፡፡ በድርቁ ምክንያት ለሕመም የተጋለጠ ሰው ካለ ግን የመዳን ያለመዳን ዕድሉ ከመንግሥት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው፤›› ብለዋል፡፡
    … መንግሥት በስድስት ቢሊዮን ብር ከውጭ የእህል ግዥ ማከናወኑን የገለጹት አቶ ጌታቸው፣ እስካሁን ፕሮጀክቶችን ለማጠፍ የሚያስችል አደጋ አለመድረሱን አስረድተዋል፡፡‹‹በእርግጥ አንዳንድ ወገኖች ችግሩ በዚሁ ደረጃ ግዙፍ ሆኖ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጪ ሆኖ ማየት ይፈልጋሉ፤›› በማለት፣ የአደጋው ደረጃ ግን ግዙፍ ግብረ ኃይል ለመመሥረትም እንዳልደረሰ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ምናልባት ፕሮጀክቶችን በሁለትና በሦስት ወራት ልናዘገይ እንችላለን፤›› በማለት፡፡ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ዕርዳታ እየቀረበ ስለመሆኑ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹እንደ ፀበል አንረጭም፡፡ ዜጐችን ከተከሰተው ድርቅ ሕይወታቸውን ለመታደግ በሚያስችል መንገድ ግን እያደረስን ነው፤›› ብለዋል፡፡ አሜሪካ በዚሁ የበጋ ወር ጀምሮ 246ሚሊዮን የምግብና የገንዘብ እርዳታ…በዚህ ሳምንት እንኳን የአሜሪካ መንግስት 97 ሚሊዮን ዶላር፣ የተባበሩት መንግስታት የስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ 17 ሚሊዮን ዶላር፣ ቻይና 8 ሚሊዮን ዶላር ፣ የአውሮፓ ህብረት (የጀርመን መንግስት) አንድ ሚሊዮን ዩሮ ሰጥተዋል።ጋዜጠኞቻችን ሆይ፣ በወቅታዊ ጉዳያዮች ላይ እንደፈለጋችሁ ጠይቁ ከተባላችሁ ታዲያ…አንድም ሰው ካልተራበ የቢቢሲና የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት ውሸት ከሆነ ይህ ሁሉ ርብርብ ለምን አስፈለገ? በእውነት በአሁኑ ሰዓት የተራበ ሰው ባይኖር ኖሮና መንግስት በቂ በጀት ከመደበ፣ ለለጋሽ ድርጅቶች ጥሪ ማቅረብ ለምን አስፈለገ? ብሎ የጠየቀ አለን ? ለሚሰቀል ገመድ ማቀበል ሳይሆን ተራው የማነው ብሎ መጠየቅ ጥሩ ነው ነግ በእኔ ነውና ። ሠላም በቸር ይግጠመን

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule