• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ላይ ያለው እምነት ተሟጥጧል”

April 25, 2014 01:56 am by Editor Leave a Comment

የህዝበ ሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ወደ አፍሪካ የሰብዓዊ መብቶችና ህዝቦች ኮሚሽን ሂደው በመንግስት ላይ ክስ መመስረታቸው ይታወቃል። ይህንን በማስመልከትም በድር ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (ቢቢኤን) የኮሚቴውን የክስ ሂደት በቅርበት ከሚከታተለው ዶ/ር አወል ቃሲም አሎ ጋር በዚሁ ጉዳይ ቆይታ አድርጓል። ዶ/ር አወል የአለም ዓቀፍ ህግ ምሁር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በLondon School of Economics የሰብዓዊ መብት Fellow ነው።

ቢቢኤን፡- የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጉዳያቸውን ወደ አፍሪካ ኮሚሽን ለመውሰድና ለመክሰስ ያሰቡት ለምንድን ነው? ጉዳያቸውን በኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች መጨረስ አይችሉም ነበር?
ዶክተር አወል፡- አመሰግናለሁ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ጉዳዩን ወደ አፍሪካ ኮሚሽን ለመውሰድ የተገደደበት ምክንያት በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ላይ ያለው እምነት በመሟጠጡ ነው። እነዚህ ፍ/ቤቶች እንደዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ የህግ የበላይነትን፣ ህገ መንግስቱን እና የራሳቸውን ህሊና መሰረት በማድረግ ሊወስኑ ይችላሉ የሚለው ተስፋ በመሟጠጡ ነው። ይህ ክርክር ደግሞ በዋናነት የእውነት ጉዳይ ስለሆነ መንግስት ከዚህ በፊት ሚዲያውን እና የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን በአጠቃላይ እንደ መንግስት ያለውን ሙሉ ሀይል በመጠቀም መሬት ላይ ሲፈጥራቸው የነበሩ እውነታዎች እውነት እንዳልሆኑና ከዚያ በስተጀርባ ሌላ ነገር እንዳለ ይህም የተፈበረከ ነገር እንደሆነ ማሳየት የሚችሉት ገለልተኛና ዓለም አቀፍ የሆነ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ ሌላ መንግስት ጫና ሊያሳድርበት የማይችልበት ተቋም ላይ በመሄድ ጉዳያቸውን አቤት ለማለት ነው ተከሳሾቹ ወደ አፍሪካ ኮሚሽን ሊሄዱ የቻሉት።

ቢቢኤን፡- እንግዲህ ይህን ጉዳይ ከመጀመሪያው ጀምረህ ስትከታተለው ነበርና የአፍሪካ ኮሚሽን ምን አይነት ድርጅት ነው? ምን ምን ጉዳዮችንስ ያያል?
ዶክተር አወል፡- በመጀመሪያ እኔ ጉዳዩን ከያዙት ጠበቆች አንዱ አይደለሁም። ለጠበቆቹ በተወሰነ ደረጃ የሰጠሁት እገዛ አለ፤ ጉዳዩን በቅርበት አውቀዋለሁ ነገር ግን ጉዳዩን ከያዙት ግለሰቦች አንዱ አይደለሁም። ወደ ጥያቄው ስንመለስ ኮሚሽኑ ምን ዓይነት ተቋም ነው ለሚለው የአፍሪካ ህብረት በውስጡ የተለያዩ ተቋማት አሉት ከነዛ ውስጥም አንዱ ይህ የአፍሪካ ህብረት የሰብዓዊና የህዝቦች መብት ኮሚሽን ነው። ይህ ኮሚሽን በ1987 በተፈረመው የአፍሪካ የሰብዓዊና የህዝቦች ቻርተር በሚል ሰነድ መሰረት የተቋቋመ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ወይም ተቋሙ ሁለት መሰረታዊ ኋላፊነቶች አሉበት። የመጀመሪያው ይህን ሰነድ ፈርመው አባል የሆኑ አገሮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ማለት ነው በምን ዓይነት መልኩ የተጣለባቸውን የሰብዓዊ መብት ግዴታቸውን እየተወጡ እንደሆነ፣ ምን ዓይነት የህግ ማውጣት፣ የዳኝነትና የአስፈፃሚ ተቋማትን እንደገነቡ መገምገም ነው። ስለዚህ ማንኛውም ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነድ መንግስታት በዚያ ሰነድ ውስጥ የተቀመጡ ሰብአዊ መብቶችን ለማሟላት ይቻል ዘንድ አስተዳደራዊ የህግ ማውጣት እንዲሁም የዳኝነት እርምጃዎችን እንዲወስዱ ይጠበቃል። ስለሆነም ኮሚሽኑ በዚህ በኩል የሚሰረው ስራ አገሮች ቻርተሩን ከፈረሙ በኋላ በዛ ቻርተር ውስጥ የተረጋገጡ መብቶችን በምን ዓይነት መልኩ ተግባራዊ እያደረጉ መሆኑንና ምን ዓይነት እርምጃዎችንስ እየወሰዱ ነው የሚለውን ነገር ከአገሮች ሪፖርት እየተቀበሉ ያንን መመርመር ነው።

ሁለተኛው የተቋሙ ስራ ግለሰቦች የሚያቀርቡትን አቤቱታ ተቀብሎ ማየት ነው። በዚህ ሰነድ መሰረት መብት የተሰጣቸው ግለሰቦች መንግስቶቻቸው እዚያ ሰነድ ላይ የተረጋገጡ መብቶቻቸውን የሚጥሱ ከሆነ ለኮሚሽኑ አቤት ማለት ይችላሉ። ኮሚሽኑ አቤቱታቸውን ተቀብሎ የማየት ስልጣን አለው። በአጠቃላይ የኮሚሽኑ ስራ ይሄ ነው።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ እንደዚህ አይነት ጉዳዮችን በሚቀበልበት ጊዜ የሚያያቸው ነገሮች አሉ። እነዚህ የሚቀርቡ አቤቱታዎች ሊያሟሉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች አሉ። ከነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ ዋናው ግዴታ ምንድን ነው ከሳሾች ወደ ኮሚሽኑ ከመሄዳቸው በፊት ሀገሮቻቸው ውስጥ ያሉ የዳኝነት መፍትሄዎችን መጀመሪያ አሟጠው መጠቀም ይኖርባቸዋል። ነገር ግን ይህ በ‘ሀገር ውስጥ ያሉ የዳኝነት መፍትሄዎች ከተሟጠጡ ብቻ ነው አቤቱታ የሚቀበለው’ የሚለው መርህ የሚሰራው እዚያ ሀገር ውስጥ ቀድሞውኑ መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል የፍትህ ስርዓት ያለ እንደሆነ ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው እርከን /stage/ ይሄ admissibility የሚባለው ማለት የክሱ የተቀባይነት ሂደት /process/ ሲያልፍ ነው። ከነዚህ ውስጥ አሁን እንዳልኩህ ዋናው መስፈርት አገር ውስጥ ያሉ መፍትሄዎችን ማሟጠጥ መቻል ነው።

የኮሚቴዎቻችንን ጉዳይ /case/ ስንመለከት አገር ውስጥ ያሉ መፍትሄዎችን አሟጠዋል ማለት አይቻልም። ምክንያቱም የክስ ሂደቱ እስካሁንም እንደቀጠለ ስለሆነ ማለት ነው። የክስ ሂደቱ ቢጠናቀቅና ቢፈረድባቸው እንኳ ተጠናቀቀ ማለት አንችልም። ምክንያቱም ለበላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማለት መቻል አለባቸው። ስለዚህ መደበኛ በሆነው አካሄድ መፍትሄ ያለበት ሀገር ውስጥ ከሆነ ከሳሾች ወደ ኮሚሽኑ የሚሄዱት አገር ውስጥ ያለውን የይግባኝ እድሎች ካሟጠጡ በኋላ ነው። እዚህ አቤቱታ ላይ የቀረበው መከራከሪያ ምንድን ነው ኢትዮጵያ ውስጥ effective እና practical የሆነ የሚሰራ መፍትሄ አካል ስለሌለ ኮሚሽኑ ሀገር ውስጥ ያሉ መፍትሄዎችን እንድናሟጥጥ መጠበቅ አይኖርበትም የሚል ክርክር ነው የቀረበው። ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት ያለው jurisprudence ምንድን ነው አንድ ሀገር የዳኝነት አካሏ ለተከሳሾች፣ ለሰብአዊ መብት ጉዳተኞች መፍትሄ መስጠት የማትችል ከሆነ እነዚያ ግለሰቦች ሀገር ውስጥ ያለውን መፍትሄ እንዲያሟጥጡ አይጠበቅም ብሏል።

በዚህ የኮሚሽኑ jurisprudence መሰረትም ኮሚቴዎቹ እየተከራከሩ ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የዳኝነት አካል ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ስለሆነና ምንም አይነት ተቋማዊ (institutional) አሰራርና ገለልተኝነት /functional independence/ ስለሌለው፣ የመንግስት ተለጣፊ ስለሆነ ባጠቃላይ ሀገር ውስጥ ልናገኘው የምንችለው ምንም አይነት መፍትሄ ስለሌለ ኮሚሽኑ ጉዳዩን ማየት መቻል አለበት የሚል ክርክር ነው ያቀረቡት። ኮሚሽኑ እዚህ ላይ በቅርብ ጊዜ ይወስናል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጲያ መንግስትም የኮሚቴዎቹ አቤቱታ ደርሶታል። መልስ እንዲሰጥ እየተጠበቀ ነው። በእርግጥ መልስ ይመልስ አይመልስ በአሁኑ ሰዓት እኔ መረጃ የለኝም። ነገር ግን እዚህ የመጀመሪያው step ላይ ኮሚሽኑ በቅርብ ጊዜ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። ከዚያ በኋላ ነው ወደ merit ማለትም ወደ ዋናው case የሚኬደው ማለት ነው።

ቢቢኤን፡- ኮሚሽኑ በአሁኑ ሰዓት ጉዳዩን አይቶ ለኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርቦለታል ማለት ነው?
ዶ/ር አወል፡- ምንድን ነው እያልኩ ያለሁት ኮሚሽኑ አቤቱታውን ከተቀበለ በኋላ ያንን አቤቱታ ለተከሰሰችዋ አገር ይልካል። በእኛ ኬዝ ለኢትዮጵያ ማለት ነው። ከዚያም የኢትዮጵያ መንግስት ከሳሾች ላቀረቡት አቤቱታ መልስ ይሰጣል። መልስ የሚሰጠው እንዴት ነው? በአሁኑ ሰዓት ተከሳሾች ለምን ኢትዮጵያ ውስጥ መከራከርና ያለውን የፍትህ ስርዓት አሟጠው መጠቀም እንዳለባቸው፣ ለምን ኮሚሽኑ ይህንን ኬዝ ተቀብሎ ማየት እንደሌለበት ነው። ስለዚህ የመጀመሪያው ስቴጅ እንዳልኩህ ክሱ ተቀባይነት ይኑረው ወይስ አይኑረው የሚል ክርክር የሚደረግበት stage ነው። ክሱ ተቀባይነት አለው የሚል ውሳኔ ኮሚሽኑ ከወሰነ የሁለተኛው stage የሚሆነው የኢትዮጵያ መንግስት የሙስሊሙን ህብረተሰብና ኮሚቴ መብቱን ጥሷል ወይስ አልጣሰም ከተጣሰስ የትኞቹ መብቶች ናቸው የተጣሱት ወደሚለው ክርክር ይኬዳል ማለት ነው። ስለዚህ አሁን ያለነው የመጀመሪያው ስታጅ ላይ ነው። የኢትዮጽያ መንግስት ለኮሚሽኑ የገባው የከሳሾቹ አቤቱታ ግልባጭ ደርሶታል። መልስ እንዲሰጥም ይጠበቃል። በአሁኑ ጊዜ መንግስት መልስ ይስጥ አይስጥ እስካሁን የማውቀው ነገር የለም ግን አሁን ያለነው እዚህኛው stage ላይ ነው።

ቢቢኤን፡- በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ነፃ አለመሆኑን፤ ገለልተኛ አለመሆኑን ነው አቤቱታ እየቀረበበት ያለው። ስለዚህ ኮሚቴዎቹ በዚህ ፍርድ ቤት የማይተማመኑ ከሆነ ለምን አድማ በማድረግ በአፍሪካ ኮሚሽን ክስ ላይ ብቻ ትኩረት አልተደረገም? በሌላ በኩል በሀገሪቱ የፍትህ ስርዓት ፍትህ እናገኛለን ብለው የማያስቡ ከሆነ መጀመሪያውኑ እዚህ ክርክር ውስጥ በተለይ ከመንግስት ጋር በሚደረገው ክርክር ውስጥ ለምን ገቡ?
ዶ/ር አወል፡- እንደዚህ ዓይነት የመንግስት ፍላጎት ያለበት፣ አለመግባባቱ ቀጥታ በመንግስትና በተከሳሽ መሀከል በሚሆንበት የክስ ሂደት አንደኛው ፍርድ ቤቱ ነፃ አይደለም ስለዚህ የሚደረገውን የፍርድ ሂደት ክብር አለሰጠውም፣ legitimize አላደርገውም የሚባልበት አንዱ ሰትራቴጂ ከፍርድ ቤቱ ጋር ምንም አለመተባበር ነው፣ በክስ ሂደቱ ላይ አለመሳተፍ ነው፣ መከላለያ አለማቅረብ ነው. . . ወዘተ። ለምሳሌ ከ1997 ምርጫ በኋላ የቅንጅት መሪዎች በክስ ሂደቱ እራሳቸውን ለመከላከል የተጠቀሙት ስትራቴጂ ይሄ ነበር። ፍርድ ቤቱ ነፃነት ስለሌለው እንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ላይ ነፃ ሁኖ በህግና በህገ መንግስቱ መሰረት ሊወስን ስለማይችል ውሳኔውም መጨረሻ ላይ የሚመጣው ከመንግስት ስለሆነ የፍርድ ቤት ሂደቱ ላይ መሳተፍ የለብንም የሚል ውሳኔ ነበር እነሱ የወሰኑት። ኮሚቴዎቹ የወሰኑት ውሳኔ ግን ለየት ያለነው።awol

የዳኝነት ስራ ፍርድ ቤት ግለሰቦች ስለሄዱ ብቻ የሚሟላ አይደለም። የዳኝነት ስራ መሰረት የሚያደርጋቸው መሰረታዊ ነገሮች አሉ። አንደኛው ፍርድ ቤቱ በተከሳሽና ከሳሽ በሆነው መንግስት መሀከል ያለውን ሚዛን መጠበቅ መቻል አለበት። ተከሳሽ ማንኛውንም ነፃ መሆኑን ሊያሳዩ የሚችሉ መረጃዎችን የማቅረብ፣ የመከራከር፣ ዐቃቤ ህግ የሚያቀርባቸውን ማስረጃዎችና ምስክሮች ጥየቄ የመጠየቅና የመፈተሽ መብት አለው። እነዚህ መብቶች ሊጠብቅለት ይገባል። መንግስት ስንል በአንድ አገር ውስጥ ያለ መንግስት almost ማንኛውንም ነገር ማድረግ ይችላል ማለት እንችላለን። በጣም አቅም ያለው ትልቅ (ኋይል ነው)። ግለሰብ ግን በየትኛው ዓይነት መልኩ በመንግስት በቀላሉ ሊጨፈለቅ የሚችል አካል ነው። ዳኝነትን ዳኝነት የሚያስብለው ዋናው ነገር፤ ፍርድ ቤትን ፍርድ ቤት የሚያስብለው፤ የእውነት መድረክ የሚያስብለው፤ የፍትህ መድረክ የሚያስብለው መንግስትን የሚያክል ትልቅ ነገርና ግለሰብን የሚያክል በጣም ትንሽ ነገር ሚዛናዊነታቸውን ጠብቆ ሁለቱንም በህግ መሰረት በሰብዓዊ መብት ድንጋጌች መሰረት፣ በህገ መንግስቱ ድንጋጌዎች መሰረት እንዲከራከሩ እድል መስጠት ነው። በዛ ክርክር ሂደት እውነት እንድትወጣና በዛ እውነት መሰረት ፍርድ እንዲሰጥ ነው የክስ ሂደቱ ያለው። የዳኝነት ስራ ማለት ያ ነው። በርግጥ ፍርድ ቤት እነዚህን ግለሰቦች ምንም ዓይነት እራሳቸውን የመከላከል ዕድል ሳይሰጣቸው ዝም ብሎ ሊወሰን አይችልም። የሚወስን ከሆነ እራሱን ችግር ውስጥ ያስገባል ማለት ነው። እራሱን ችግር ውስጥ የሚያስገባው እንዴት ነው መጨረሻ ላይ ሂዶ ሂዶ ውሳኔው ከተወሰነ በኋላ ያ የወሰኑበት አካሄድ፣ የከለከሏቸውን መብት ምናልበት የህግ ስርዓቱ ዛሬ ተጠያቂ ላያደርጋቸው ይችል ይሆናል ነገር ግን በታሪክ ተጠያቂ ይሆናሉ፣ ይወቀሳሉ።

ቢቢኤን፡- ከኮሚሽኑ የፍርድ ሂደት በኋላ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀው ውሳኔ ምንድን ነው? ውሳኔውን እንዴት ነው ሊተገብር የሚችለው? ኮሚቴዎችን ከእስር ሊያስለቅቅ የሚያስችል የፖሊስ ኋይል አለው?

የዚህን ምላሽ በቀጣዩ ክፍል ይዘን እንቀርባለን። (ሰላም አብዱላሂ በፌስቡክ በኩል ለጎልጉል የላኩት)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Interviews Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm
  • በዓባይ ግድብ ምረቃ፡ የሕዝብ ደስታ፣ የቴድሮስ ካሳሁን ዝምታ September 14, 2025 04:27 am
  • ኢትዮጵያ የውኃ ኑክሊየር ማብላያዋን ልታስመርቅ ነው  August 29, 2025 11:46 pm
  • መከላከያ በፋኖ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ፤ ዘመነ በ“አንድ ማንኪያ ቅንነት” አንድ እንሁን አለ August 23, 2025 12:35 am
  • ፋኖን በፋይናንስና በሎጂስቲክስ የሚደግፉ የጎጃም ባለሃብቶች ከስደት ሊመለሱ ነው August 14, 2025 12:42 am
  • የበቀለ ገርባ የአሜሪካ ጥገኝነት ማመልከቻ ውድቅ ተደረገ August 13, 2025 12:16 pm
  • ሞዐ ተዋሕዶ “ነጻ አውጪ ግምባር” – ሞነግ August 13, 2025 12:58 am
  • የሃይማኖትና የመንግሥት ጥምረት በረከት ወይስ መርገም?  August 5, 2025 09:18 pm
  • የባከነ የስደት ሕይወት ከደባርቅ እስከ ኖርዌይ July 29, 2025 05:44 pm
  • “በዚህ ዓመት መጨረሻ ትግራይን እንቆጣጠራለን”፤ ቲፒኤፍ July 22, 2025 01:28 am
  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule