• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቴዲ በድጋሚ ፓስፖርቱን ተቀምቶ ነበር

July 19, 2015 12:48 am by Editor 1 Comment

ባለፈው ሳምንት ወደ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉን የአየር መንገዱ ምንጮች አስታወቁ።  በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮቹ ጠቁመዋል። በተሳፋሪዎች ላይም ከፍተኛ መጉላላት ደርስዋል።

አውሮፕላኑ ካኮበኮበ በኋላ እንዲመለስ የተደረገበት ምክንያት ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ከአለምሰት ሙጬ ጋር በአውሮፕላኑ በመሳፈሩ ምክንያት መሆኑ ተረጋግጧል። ይህ አስደንጋጭ ክስተት የተፈጸመው አለምሰት ሙጬ በደረሰባት ድንገተኛ ህመም ለህክምና ወደ ኬንያ እየተጓዘች ባለችበት አውሮፕላን ነው።

አውሮፕላኑ ዞሮ ከተመለሰ በኋላም ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ በደህንነቶች ተይዞ ከአውሮፕላኑ እንዲወጣ ተደርጓል።  የህወሃት የደህንነት አባላት የቴዲ አፍሮን ፓስፖርት ቀምተው አሰናብተውት ነበር።

ቴዲ አፍሮ በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ላይ ድምጻዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ጋር መጋበዙ የሚታወስ ሲሆን ይህንን በመቃወም ሚሚ ስብሃቱ እና ባለቤትዋ ዘሪሁን ተሾመ ዘመቻ ከፍተው እንደነበር የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 33ኛ ዓመት በዓል ላይ እነዚህ ድምጻውያን አልተገኙም። ድምጻውያኑ በበዓሉ ያልተገኙበት ምክንያት የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ በደረሰው የኮምፒውተር ሽብር ጥቃት የቪዛ ችግር ያጋጠማቸው መሆኑ ቢገለጽም፤ ቪዛ ቢያገኙ ኖሮ እንኳ በደህንነቶች  አፈና ከሃገር ሊወጡ እንደማይችሉ ግልጽ ነበር።

የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌዴሬሽን አሸባሪ ተብሎ በነሚሚ ስብሃቱ መፈረጁን ህወህት ተቀብሎ በውስጥ አጽድቆታል። ቴዲ አፍሮ ባለቤቱን ለማሳከም ወደ ኬንያ በመጓዝ ላይ እንዳለ በኬንያ በኩል ወደ አሜሪካ ሊጓዝ ነው ተብሎ በነ ሚሚ ስብሃቱ በደረሰው ጥቆማ ነው አውሮፕላኑ እንዲመለስ የታዘዘው። በዚህ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት በተሳፋሪው ላይም ከፍተኛ መጉላላት የደረሰ ሲሆን አየር መንገዱም ለከፋ ኪሳራ ተዳርጓል ሲሉ የአየር መንገዱ ምንጮች ተናግረዋል። ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ከባለቤቱ ጋር ወደ ኬንያ ይጓዝ የነበረው የሰሜን አሜሪካው የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ከተጠናቀቀ በኋላ ነበር። የህወሃት ደህንነት አባላት ይህንን እንኳን ማገናዘብ የማይችሉ ደካሞች እንደሆኑ ምንጮቹ ተቁመዋል።

ከብዙ መጉላላት በኋላ ቴዲ አፍሮ ፓስፖርቱን አስመልሶ ወደ ጀርመን – ፍራንክፈርት የበረረ ሲሆን በቅዳሜ ምሽት የአውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ላይ ዝግጅቱን አቅርቦዋል። ከዚያም የጄኔቭ ስዊዘርላንድ ማዘጋጃ ባሰናዳው ዝግጅት ላይ ልዩ ተጋባዥ በመሆን በመጭው ሳምንት ስራውን ለህዝብ በነጻ ያሳያል።

የቴዲ አፍሮ ባለቤት አለምሸት ሙጬ በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ-ቨርጂንያ ህክምናዋን እየተከታተለች ትገኛለች።

ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን በአካል አግኝቼ ባነጋገርኩበት ግዜ የዚህን ዘገባ ትክክለኝነት አረጋግጫለሁ። ይህንን እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ወደፊት በስፋት እመለስበታለሁ።

(ክንፉ አሰፋ፣ ፍራንክፈርት)

Filed Under: News, Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. ህሉፍ says

    August 8, 2015 04:31 pm at 4:31 pm

    ሞት ለወያኔ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule