ይህንን ዘገባ ሳሰናዳ በ1997 ምርጫ ወቅት አዲሱ ገበያ አካባቢ አልሞ ተኳሾች የገደሉባቸውን ልጃቸውን ስም እየጠሩ “ምን አደረካቸው? ምን አጠፋህ? አንተኮ ትንሽ ነህ? ማንን ልጠይቅ? ማንን ላናግር? ልጄ … የኔ ባለተስፋ፣ እኔ ልደፋ፣ እኔ መንገድ ላይ ልዘረር፣ ምነው ለኔ ባደረገው? የማን ያለህ ይባላል…” የሚሉ ልብን ዘልቆ የሚገባ ሃረግ እየደጋገሙ እብደት የተቀላቀለው ለቅሶ አልቅሰው ያስለቀሱን እናት ታወሱኝ፤ ብዙዎች በተመሳሳይ አንብተዋል።ደረታቸውን ደቅተዋል። አሁን ድረስ የልጅ፣ የአባት፣ የወንድም፣ የእህት፣ የዘመድና ወዳጅ ብሎም የአገር ልጅ ሃዘን የሚያቃጥላቸውን ቤታቸው ይቁጠራቸው። “ኢትዮጵያ ለእኛ አስፈላጊ አገር ናት። ኢትዮጵያዊ በመሆናችን ለአገራችን ትልቅ ቦታ መስጠት አለብን። ምክንያቱም አስፈላጊ ናትና። እዚያ እስከተወለድን ድረስ /መሰረታችን ኢትዮጵያ እስከሆነች … [Read more...] about “በአገራችን ባይተዋር ከመሆን በላይ ውርደት የለም”