እኔ ምን አገባኝ እኔ ምን አገባኝ የምትሉት ሐረግ እሱ ነው ሀገሬን ያረዳት እንደ በግ የሚል ግጥም ልጽፍ ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና ምን አገባኝ ብየ ቁጭ አልኩ እንደገና:: ግጥሙ የተወሰደው ከኑረዲን ዒሳ ፌስቡክ ነው:: ባለፈው ሌባዬ በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ የተሳተፋችሁትን ሁሉ በተለይ ደግሞ Tsinat ፣ Gedion Adenew እና አበበ አዲስ ከልብ እናመሰግናለን:: እስቲ ለዚህኛውም አንድ ሁለት ሁላችንም እንበል!! እንደበፊቱ ሁሉ ምላሹ በግጥም ቢሆን ጨዋታዋን ሞቅ ያደርገዋል:: … [Read more...] about እኔ ምን አገባኝ?
Right Column - Primary Sidebar
ያልተመጣጠነ ግጥሚያ
ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ታመዋልም ሞተዋልም በሚማልበት ሰአት ሎጋው ሽቦ ተዘፈነ … የርዕሰ ብሄር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ በሆነበት ሰአት ደግሞ ብር አንባ ሰበርልዎ ተብሎ ሲዘፈን በሰፊው ተሰማ… ኃይለማርያም ደስ አለኝ ቦታው ተፈቅዶላቸው ሀገር ወከሉ ተብሎ ሲታወጅ አስገራሚው ዘፈን አላቆመም የቤተ ዘመዱ ይታያል ጉዱ ይባል ተገባ… ***************************************************************************************************** አጋጣሚ የፈጠረውን ፖለቲካዊ ግርግር በጥበብ ተጠቅሞ በፖለቲካው እንቅስቃሴ ውስጥ የመደራደሪያ አቅም በማበጀት ወይም አቅም በመገንባት አማራጭ ሀይል መሆንን ከማሳየት ፋንታ በቀረርቶና በሽለላ የጨዋታውን ህግ ለመቀየር መመኘት የምኞት ሁሉ መናኛ ቢባል ያስነውር ይሆን? በትግል … [Read more...] about ያልተመጣጠነ ግጥሚያ
ሌባዬ. . .
ሌባዬ. . . ድምጹ ሳይሰማ ኮቴውን አጠፍቶ በጠራራ ፀሐይ የደጄን በር ከፍቶ መዝለቅ የጀመረው ክርችም በሬን ከፍቶ ምን ሊዘርፈኝ ይሆን በምኔ ጎምጅቶ? በማለት ኖላዊት ሽመልስ ስትጠይቅ የሚከተሉት መልሶች ተሰጥተዋታል፡፡ (ምልልሱን ያገኘነው ከፌስቡከ ሲሆን እርስዎም የሃሳብ በመስጫውን በመጠቀም ምላሽዎን እንዲሰጡ እንጋብዝዎታለን፡፡) ************************************************************************************* ጠንቀቅ አለሽ ንብረት አለሽ አንቺዬ ሃብት አለሽ ገንዘብ የማይገዛው ለራስሽ ያልታየሽ እጅግ የበለጠ ከወርቅ፤ አልማዝ፤ ከእንቁ አድፍጦ ሊዘርፍሽ ያመጣው ከሩቁ እመኚኝ ሃብት አለሽ ዘብ የሚያስፈልገው ብቻ ችላ ብለሽ እንዳታሰርቂው፡፡ (ብሌን … [Read more...] about ሌባዬ. . .
“ግራውንድ ሲቀነስ አንድ”
(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ለአዲስ አበባ ከተማ ክብር ያላችሁ እንስማማለን። አዲስ አበባ አንጀቷ ርህሩህ ነው። ከገዢዎች ክፋት በተጨማሪ አዲስ አበባ ፊቷን ብታጠቁር ምን ይኮን ነበር? ሎሬት ጸጋ ስለ አዲስ አበባ ተቀኙት ወደው አይደለም። በውነት ላስተዋለው የአዲስ አበባ ቆዳና ያዲስ አበቤዎች ትከሻ “ላይችል አይሰጥም” የሚሉት አይነት ነው። በየቀኑ አዲስ አበባ በማለዳ በትና በምሽት የምትሰበስባቸው ልጆቿ ተቃምሰው ማደራቸው ባዲሳባ በረከት እንጂ በገዢዎች አቅርቦት አይመስልም። ከአራቱም ማዕዘን የሰው ደራሽ ወደ አዲስ አበባ ይንፎለፎላል። አዲስ አበባ ሞልታ የምትፈስ አትመስልም። እምዬ ምኒሊክ ሲቆረቁሯት ጀምሮ አዲስ አበባ ተቀባይ ነች። የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ መዲና፣ የሰው ልጅ እምብርት፣ አዲስ አበባ፣ ፊንፊኔ። ምንም ትባል ምን አዲስ አበባ ሁሉም ጓዳ የተባረከች ናት። … [Read more...] about “ግራውንድ ሲቀነስ አንድ”
የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች
(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) “በሬ ለምኔ” የፍየል ቁርጥና ጥብስ መለያ ማስታወቂያ ነው። ከኦሎምፒያ ወደ መስቀልፍላወር በሚወስደው መንገድ ላፓሬዚን አለፍ እንዳሉ ወደ ግራ ሲታጠፉ ያገኙታል። ለጉዳዬ የሚመቸኝን በሬ ለምኔ ላመላክት እንጂ ብዙ “በሬ ለምኔ” ቤቶች አዲስ አበባ ተከፍተዋል። ያዲሳባ ቀምጣላ ካድሬዎች፣ ልማታዊ ባለሀብቶች፣ አቀባባዮችና ባለጊዜዎችና አጫፋሪዎቻቸው እድሜ ለማራዘም ፍየል ይመገቡና ማታ ልቅ የግብረ ስጋ ለማድራት አይጨነቁም። እጠቆምኩት ቤት ስትገቡ ፍየል የሚያገላብጡት የሚታወቁ ባለሥልጣናትና ታዋቂ ካድሬዎች ናቸው። ፍየል ከገባ በኋላ መኪና ተረክ እያደረጉ እዛው ሰፈር፣ ብዙም ሳይርቅ ወይም ቦሌ መሃል፣ ዝግ ቤቶች ይሰየማሉ። አንዱን “ሮዚና” ዝግ ቤት ላስተዋውቃችሁ። ሮዚና ዝግ ቤት ማንም ዘው ብሎ አይገባም። ሮዚና ሲደርሱ እንደ መኖሪያ ቤት ጥሩምባ አሰምተው … [Read more...] about የሚዘጋባቸው ህጻናት – ዝግ ቤቶች
“ጣጣ የለውም!” ሌላው ግሽበት
(ቀጭኑ ዘ-ቄራ ) ዛሬ ዛሬ ባገራችን በተለይም አዲስ አበባ በየቀኑ የሚመረቱት ቃላቶች የሚሰበስባቸው ቢገኝ አንድ ራሱን የቻለ ቋንቋ ይመሰርታሉ። ለተረብ የሚወረወሩት ቃላቶች ደግሞ ፈጠራቸው እስኪገርም ድረስ ያንተከትካሉ፤ ያስቃሉ። ወሬ ከሚፈላባቸው ቦታዎች መካከል ጫት ቤቶች ይጠቀሳሉ። በጫት ቤት ወሬ ይበለታል፤ መንግስት ይገሸለጣል። ጫት ቤት ሆነው ከፍተኛ መመሪያ የሚያስተላልፉ ጥቂት አይደሉም። ጫት ቤት ቁጭ ብለው መንገድ እንዲወጠር የሚያዙ የፌደራል ፖሊስ ሃላፊዎች አሉ። ከአቶ መለስ ጠባቂዎችም መካከል መርቃኞች የነበሩ፣ ለስራ ሲፈለጉ ሸሚዝ ቀይረው በኮብራ የሚበሩ አሉ። ጫት ቤት የማይሰበስበው ሰው የለም። ዶክተሮች፣ የህግ ሰዎች፣ ሚኒስትሮች፣ ልማታዊ የህዝብ ግንኙነቶች፣ ከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች፣ የደህንነት ሰዎች፣ የፓርላማ አባላት፣ ከንቲባዎች፣ ዞንና የቀበሌ ሰራተኞች… … [Read more...] about “ጣጣ የለውም!” ሌላው ግሽበት
የኔ ውብ ከተማ
የኔ ውብ ከተማ ከጎራው ዘልቄ እስኪ ልነጋገር ካለሰው ቢወዱት ምን ያደርጋል አገር? የኔ ውብ ከተማ ሕንፃ መች ሆነና የድንጋይ ክምር የኔ ውብ ከተማ መንገድ መች ሆነና የድንጋይ አጥር የኔ ውብ ከተማ የኔ ውብ አገር የሰው ልጅ ልብ ነው የሌለው ዳርቻ የሌለው ድንበር፡፡ ሕንፃው ምን ቢረዝም ምን ቢፀዳ ቤቱ መንገዱ ቢሰፋ ቢንጣለል አስፋልቱ ሰው ሰው ካልሸተተ ምንድነው ውበቱ? የሰውን ልብ ነው፡፡ ምን ቢነድ ከተማው ተንቦግቡጎ ቢጦፍ ቢሞላ መንገዱ በሺ ብርሃን ኩሬ በሺ ብርሃን ጎርፍ ምን ያደርጋል? ምን ያሳያል? ካለሰው ልብ ብርሃን ያ ዘላለማዊ ነበልባል ያ ተስፋ ሻማ ጨለማ ነው ሁሉም ጨለማ፡፡ በዓሉ ግርማ … [Read more...] about የኔ ውብ ከተማ
“ሰለባው” ማን ነው?
አቶ መለስ መሞታቸውን መንግስት አላምንም ማለቱ ጉጉት ፈጠረ። መለስ ታመዋል የሚለው ወሬ ሹክ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ የሁሉም ጆሮ በመለስ እስትንፋስ ማለፍና አለማለፍ ዙሪያ የሚሰጡትን መግለጫዎችና ዜናዎች ማሳደድ ላይ ተጠመዱ። እስካሁን ለንባብ ባይበቃም አቶ መለስ ረጅም ሰዓት የፈጀ የአእምሮ ቀዶ ጥገና ካደረጉ በኋላ መንቃት በሚገባቸው ሰዓት ውስጥ ባለመንቃታቸውና ምንም ዓይነት የመንቃት ምልክት ማሳየት ባለመቻላቸው ሃኪማቸው “clinically dead” በማለት በህክምናው ረገድ ማረፋቸውን ተናግረው ነበር፡፡ ግን ህይወታቸው አላለፈችም የሚል ሪፖርት ማቅረባቸውን የቅርብ ምንጮች ከነገሩኝ ቆይቷል። ሃኪማቸው እጃቸውን አጥብቆ ሲይዝ ምንም ምላሽ ባለመስጠታቸው በሙያው ቋንቋ የተስፋ መቁረጥ ሪፖርት ያቀረቡት ሃኪማቸው ከቀናት በኋላ በተመሳሳይ እጃቸውን ሲጨብጥ መለስም ያዝ በማድረግ ምላሽ … [Read more...] about “ሰለባው” ማን ነው?