“ኢሕአዴግ በጣም አምባገነን ፓርቲ እንዲያውም ጥንት ከነበሩ መንግስታት በተለየ ነው” “ዲፋክቶ መንግስት ያዋጣል ብሎ የሚያስብ ፓርቲና ፖለቲከኛ እጅግ በጣም ለትግራይ ሕዝብ ጥፋት እየደገሰ ያለ ነው” አቶ ገብሩ አስራት የአረና ትግራይና የመድረክ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። የንግግራቸው አንኳር ሃሳቦች ከዚህ በታች በሚከተለው መልኩ ቀርቧል፤ • ሕወሓት ይፋዊ በሆነው ልሳኑ ወይን ጋዜጣ ላይ ዲፋክቶ መንግስት እንመሰርታለን ነው ያሉት። • የሕወሓት አመራር ስለተቸገረና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ስለተበላሸ እንገነጠላለን የሚለው ነገር የማያዋጣ ለሕዝብ የማይበጅ፤ ጥፋትን የሚያስከትል ነው ብዬ አምናለሁ። • ዲፋክቶ መንግስት ማለት ሕገወጥ መንግስት ማለት ነው። ለሕወሓት አመራር ፤ ለአንዳንድ አክቲቪስቶች … [Read more...] about “በትግራይ ያለው ገጽታ ከድሮውም የባሰበት አፈና ነው” ገብሩ አሥራት