* ውሳኔው የኢትዮጵያን የወደብ ፖለቲካ ስትራቴጂካዊ ኃይል ሰጥቶታል የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እሑድ ጥቅምት 8 ቀን 2019 ዓ.ም. ባቀረቡት አዲስ ብሔራዊ የደኅንነት ዶክትሪን መግለጫ ላይ፥ ሶማሊላንድን ከቀሪዋ ሶማሊያ ነጥሎ ሉዓላዊት ሀገር አድርጎ የሚያሳይ አዲስ ጂኦ-ፖለቲካዊ ካርታ ይፋ አድርገዋል። ይህ እርምጃ ቀጣናዊ የኃይል ሚዛኑን በእጅጉ የሚቀይር ሲሆን፥ በተለይም ኢትዮጵያ በሶማሊላንድ በኩል የባሕር በር ለማግኘት ለምታደርገው ብሔራዊ ጥረት ትልቅ ዲፕሎማሲያዊና ስትራቴጂካዊ ግፊት እንደሚፈጥር ተነግሯል። በእስራኤል መንግሥት የፕሬስ ቢሮ አርማ በታተመውና "በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ጂኦ-ፖለቲካዊ ጥምረቶች" በሚለው ካርታ ላይ ሶማሊላንድ ለእስራኤልና ለተባበሩት አረብ ኤምሬቶች (UAE) ስትራቴጂካዊ ምሕዋር “ወዳጅ” ተብላ በልዩ ቀለም ተለይታለች። … [Read more...] about ኔታንያሁ የሶማሊላንድን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ አዲስ ቀጣናዊ ካርታ ይፋ አደረጉ

