• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ጃዋር፦ ያልተናገረውን በተናገረው ውስጥ መስማት”

November 6, 2016 12:21 am by Editor 1 Comment

“ወያኔ አንድ ታንክ ከመግዛት፣ በ10 ሚሊዩን ዶላር አንድ ከፋፋይ አክቲቪስት መግዛት ትመርጣለች” መስፍን ፈይሳ ሮቢ

ጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው በ“አፈርሳታ” ዝግጅቱ ጃዋርን አቅርቦ አነጋግሮት ነበር። ለጃዋር የቀረበለት አንዱ ጥይቄ “. . . የግንቦት ሰባት እና የኦሮሞ ደሞክራሲያዊ ግንባርን ጥምረት እንዴት አየኸው?” የሚል ነበር።  ጃዋር “. . . ቅን አመለካከት ነው ያላቸው. . .ጥሩ ሙከራ እያደረጉ ነው. . . ኢንቴንሽናቸው  ቅን ነው. . .” ብሎ በተናገረው ውስጥ  “. . . በትክክል የተሰራ ግን አይደለም፣ የፖለቲካ ብስለት ያለበት ግን አይደለም” የሚል እና ያልተናገረውንም ነገር (between the lines) ትሰማለህ።  ነገሩ “ከኛ ወዲያ ፉጭት አፍ ሟሞጥሞጥ ነው. . .” ወይም  “. . . ፖለቲካ ከኔ ወዲያ ላሳር ነው” የሚል ድምጸት አለው።

ጃዋር ሌላም ጥይቄ ቀርቦለት ነበር፡- “. . . አሁን በዚህ ወቅት በብሄረሰቦች መሃከል . . .ችግሩን የጋራ አድርጎ የማየት ነገር ይታያል። ነገር ግን ቀደም ብሎ አንተ. . . ለኦሮሞ ህዝብ ችግር በደል ጭቆና . . . ትኩረት አድርገህ ነው ስትታገል የነበረው እና ለምን ከሰብዓዊነት አንጻር . . . ለምን ጠበብ አድርገህ አየኸው፣ ለምን ከማንነት፣ ከኦሮሞነት መነሳት ፈለግህ . . . አሁን ራስህ ብለኸኛል . . . ኮንሶ፣ ጋምቤላ . . . ተመሳሳይ ጭቆና እየደረሰባቸው ነው፣ . . . የኦሮሞን ህዝብ ብቻ “ኮዝ” (cause/ምክንያት) አድርገህ የተነሳሃው ለምንድን ነው?”

ሰብዓዊነትን የሚፈትን ጥያቄ ነው (በሜጫ አንገት ለሚቆርጥ ሰው የሚመጥን ባይሆንም)።

የጃዋር መልስ “. . . ብዙ ቤቶች በመደዳ አሉ ልበል፣ እና እሳት ተለኮሰ፣ መጀመሪያ የራስህን ቤት እሳት ማጥፋት የመጀመሪያ የሰዎች ሰብዕና ተፈጥሮ ነው. . .” ሲል ነበር የመለሰው። ይኼ መልሱ፣ ህወሃት አ.አ. ገብቶ መንግስት ከመሆኑ አንድ አመት በፊት፣ ጎጃም ውስጥ ያገኘሁት አንድ የህወሃት ነፍጥ አንጋች የሰጠኝን መልስ ነበር ያስታወሰኝ።

ጠየቅሁት፦ “ለመሆኑ በኤርትራ ጉዳይ ላይ ያላችሁ አቋም ምንድን ነው?”

የህወሃቱ ነፍጥ አንጋች፦ “. . .ባልና ሚስት አብረው የሚኖሩት እስከተስማሙ ድረስ ብቻ ነው፣ ካልተስማሙ መፋታት ነው ያለባቸው. . .” ነበር ያለኝ (በዚህ አጋጣሚ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ ጉዳይ ቁጥር አንድ ተጠያቂው ህወሃት ነው)።

የሃገርን ጉዳይ ከባልና ሚስት ፍቺ ጉዳይ ጋር እኩል የሚያነጻጽር የፖለቲካ ትንተና ከአንድ የህወሃት ነፍጥ አንጋች መስማት አይገርምም፣ ፖለቲካል ሳይንስ ካጠናው ጃዋር፣ የፖለቲካ ተንታኝ ከሆነው ጃዋር፣ የህዝብ ደህንነት (public safety)፣ የማህበራዊ ፖለቲካን ጉዳይ እሳት ከማጥፋት ጋር ከማነጻጸር በላይ ይጠበቃል።

jawar-mቢያንስ ከተሸከመው “የፖለቲካ ተንታኝ፣ አክቲቪስት፣ የማህበረሰብ ተመራማሪ. . .” ማዕረግ አንጻር ሲታይ፣ ጃዋር የፖለቲካ ድሃ ነው። ወይም እያወቀ በፖለቲካ የደኸየ ሰው ነው። ሲመስለኝ፣ ኢትዮጵያዊያን በተለይም የኦሮሞ ተወላጆች፣ ጃዋርን ሰቅለው ሰቅለው፣ አሁን ማውረጃው ያጠረባቸው ይመስለኛል፣ እየተጋፈጡት ያሉ በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ በተለይም ከኦሮሞ ነገድ አባላት በየቦታው የመውጣታቸው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ።

እስኪ አሁን “. . . ህዝብ እግር ከሆነ፣ የፖለቲካ አመራር ጭንቅላት ከሆነ . . . ህዝቡን እግሩም አስረን አንድ ላይ እንዲንቀሳቀስ ነው ያደረግነው. . .” የሚባል ትንተና ምን ማለት ነው? እንዲያው ምን የሚሉት የፖለቲካ ትንተና ነው? ለመሆኑስ “ኦሮሞና አማራ ሲርየስሊ መነጋገር አለባቸው. . .” ሲል፣ ኢትዮጵያን የሚወክሉት ኦሮሞ እና አማራ ብቻ ናቸው? ደግሞስ አሁን ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ እስራት፣ አፈና፣ የሃገር ሃብት ዝርፊያ . . . እና ይኼ ሁሉ በዚህ ከቀጠለ እና የህወሃት እድሜ ከተራዘመ ሊያስከትል የሚችለውን ምስቅልቅል ለማስቀረት፣ እውነት ይኼን ያህል የፖለቲካ መራቀቅ ያስፈልገዋንል? . . . ምንስ አይነት የአማራ እና የኦሮሞ ሲርየስ ንግግር ነው የሚያስፈልገው? ምን አይነት ውይይት ነው የሚያስፈልገው? ቢያንስ እሱ እወክለዋለሁ የሚለው የኦሮሞ ብሄረሰብ ብሄረተኞች የነበሩ እና ኦሮሞን የሚወክሉ አንጋፋ መስራቾች የተሳተፉበት፣ የኦሮሞ ብቻ ሳይሆን የአፋር እና የሲዳማ ህዝቦችን (አማራም በግለሰብ ደረጃም ቢሆን የተወከለበት) ስብሰባ በተደረገ ማግስት “. . . ኢትዮጵያን እናፈራርሳለን. . .” ብሎ የሚፎክር የፖለቲካ ተንታኝ እውነት የፖለቲካ ተንታኝ ነው?

ጃዋር አገር ቤት ውስጥ ህዝብ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ እና ትግሉ እጅግ በተጧጧፈበት፣ እና በሞቀበት ሰዓት፣ ቀዝቃዛ ውሃ መቸለስን ያውቅበታል። ለህወሃት መተንፈሻ ቦታ መክፈት (ፋታ መስጠት)፣ በእንግሊዝኛ “pent up emotion”ን ማስተንፈስ እንደሚሉት ነው (ይኸን በዝርዝር እና ከነማስረጃዎቹ ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ)።

ከወር በፊት አፈርሳታ ላይ “. . .ህወሃት የአማራን ህዝብ አያውቀውም፣ የኦሮሞን ህዝብ አያውቀውም. . .” ሲል ምን ማለቱ ነው? ጃዋር እንደ ግለሰብ ኦሮሞን እና አማራን የሚያውቀውን ያህል መንግስት የሆነው ህወሃት፣ ያገሪቱን ደህንነት፣ ሃብት እና ሰራዊት የያዘው ህወሃት የአማራን እና የኦሮሞን ህዝብ አያውቀውም? ይኼ ለኔ እንቶ ፈንቶ ነው። ደግሞስ “. . . የአማራ እና ኦሮሞ ህዝብ ከሺ አመት በላይ አብሮ የኖረ ህዝብ ነው. . .ከማንም በላይ የሚተዋወቀው ደግሞ ሁለቱ ነው. . .” ያለን ጃዋር፣ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ለንደን ላይ አማራን፣ ትግሬን፣ ከንባታን ሲዳማውን . . . ወዘተ በጥቅሉ ኢትዮጵያን ስለማፈራረስ ይነግረናል። የሚናገራቸውን በሙሉ ላዳመጠ ሰው፣ ምንም አይነት “consistency” እና “integrity” የላቸውም። ጃዋር ለንደን ላይ “ኢትዮጵያን ስለ መበተን” የተናገረው፣ በአራቱ ድርጅቶች የተመሰረተውን፣ እንዲያውም የኦሮሞን ህዝብ የሚወክል ድርጅትም የተሳተፈበት የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ በተመሰረተ ማግስት መሆኑ፣ ለህወሃት ትልቅ ፋታ፣ ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ ሞት፣ እልቂት፣ እስራት እና መከራ መራዘም ነው ውጤቱ።

mamma-lomiየልጃቸው አስከሬን በማዳበሪያ ተጠቅልሎ የተሰጣቸው እና “. . .የሞተ አይመለስም. . .የተበታተኑትን ልጆቼን መልሱልኝ. . .” ሲሉ የሚናገሩት የሟች እናት ወ/ሮ ሎሚ ዋቀዮ የሜዲያ አጋጣሚውን ስላገኙ ነው እንጂ፣ ምንም አይነት የስልክም ሆነ ማንኛውም የመገናኛ ብዙሃን መንገዶች ሁሉ ሆን ተብለው በተዘጉበት ሁኔታ፣ እያለቁ፣ እየተሰቃዩ ያሉትን ወጣቶች፣ አንጀታቸው ተቆርጦ በየመንደር እና ገጠሩ ሁሉ እያለቀሱ ያሉ የወ/ሮ ሎሚ አይነት እናቶች በርካታ ናቸው።

አገሪቱ በሙሉ ወደ እስር ቤትነት ተቀይራለች፤ አደባባይ ሳይወጣ እና ለዜና እና ቀባሪ ሳይበቃ በየከተማ እና ገጠሩ እያለቀ ያለውን ህዝብ እግዜር/አላህ ይቁጠረው (መቼም መቁጠር አይሰለቸውም)።

ስለዚህ አሜሪካ እና ለንደን ውስጥ ሆኖ “ኢትዮጵያን እናፈርሳለን. . .” ብሎ የሚናገር ሰው እና አገርቤት ውስጥ እየደረሰ ያለውን እና ለወደፊትም ሊሆን የሚችለውን  ግድያ፣ እስራት እና በአጠቃላይ ህወሃት እያደረሰ ያለውን ሽብር፣ ከሁሉም በላይ እያደረሰ ያለውን ማህበረሰባዊ የሞራል ቀውስ፣  (ለ25 አመታት የሆነውንማ በየቀኑ እየሰማን እያየን እየለመድነው. . . አለን። አሁን ትላንት ወዲያ በኢሳት የቀረበውን፣ ዶ/ር ካሳሁን በዛብህን እንዴት እንደገድሏቸው እና የዶ/ሩንም ወንድም፣ ዶ/ሩ ራሳቸውን እንደገደሉ አድርጎ ካልተናገረ ምን እንደሚደርስበት በዚህ ቃለ-መጠይቅ ላይ ዛሬ የሰማሁት፣ እንደ ህዝብ “. . .በአጠቃላይ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ የሞራል መሰረት እንደገደሉት” ነው የምለው እኔ) እንዴት እንደገደሏቸው ለማገናዘብ የማይችል ጃዋር ለኔ የፖለቲካ ተንታኝ አይደለም።

“ሳትፈጨው እኮ እንጀራ አታደርገውም፣ አይደለም እንዴ. . ..”፣ “ኦሮሞ እና አማራ በመተባበሩ [ህወሃቶች] . . . መምቦቅቦቅ አለባቸው. . .” ብሎ የሚጠቀምበት ቋንቋ ራሱ የፖለቲካ ተንታኝ ነኝ የሚል ሰው የሚጠቀምበት ቋንቋ አይደለም።jawar-preaching-muslims-and-chritian-oromos-not-to-go-to-ethiopia-churchs-and-mosque

“Discourse analysis” ያጠና ሰው የለንም ይሆን? ጃዋር የሚናገራቸው ነገሮች “ኢንተግሪቲ”፣ እና “ፍሰት (መፍሰስ) የሌላቸው መሆናቸው (ለምሳሌ ዋሺንግተን ዲሲ ላይ ይመስለኛል “Ethiopia out of Oromya” እላለሁ ብሎ “Oromya out of Ethiopia” . . . ብሎ የተናገረው አይነት የንግግር መምታታት) [‘አንድ ሰው ከልቡ፣ በእውነት እና በከፍተኛ ስሜት ተመስጦ genuinely & honestly የሚናገረው ነገር፣ ንግግሩ እንደ ዘይት ይፈሥሳል፣ አይቆራረጥም፣ ቃላትም ሊጠፉበት አይችልም’ የሚል ማንበቤ ትዝ ይለኛል]፤ ጃዋር ባደረጋቸው እጅግ በርካታ ንግግሮች ውስጥ እንዲህ አይነት ንግግሮች  በርካታ ናቸው)፤ ጃዋር ሲናገር በፊቱ ላይ የምታየው ኢሞሽን፣ ፈገግታው ተጀምሮ የሚያልቅበት ቅጽበት፣ የሰውነቱ እንቅስቃሴ እና የሚያደርጋቸውን ንግግሮች ይዘት እና መቼት (ጊዜ እና ቦታ) ላስተዋለ ሰው፣ የጃዋር ንግግሮች እና አቋሞች እና ሁለንተና እና ሁኔታው ለ“Discourse analysis” የሚጋብዝ ነው።

ከአፈርሳታ ቃለ መጠይቅ እንደተረዳሁት ከሆነ ጃዋር ሌላ ስራ ያለው አይመስለኝም።

“ወያኔ አንድ ታንክ ከመግዛት፣ በ10 ሚሊዩን ዶላር አንድ ከፋፋይ አክቲቪስት መግዛት ትመርጣለች” መስፍን ፈይሳ ሮቢ

ታፈሰ ወርቁ (tafeseworku2016@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Ras Dejen says

    November 25, 2016 02:48 pm at 2:48 pm

    This Jewar is either:

    – a highly disguised TPLF cadre
    – or an irrational Oromo Ethiopian who failed to critically analyse the optimal solutions and advantages even to the people to whom he is claiming fighting for!

    Let us leave him alone to figure out his way or come forward openly! Because as I said “he is disillusioned or hired!”

    Please don’t give him interview! Let us boycott or ignore him!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am
  • ከያቤሎ አዲስ አበባ የተላከ ኮንትሮባንድ ጉለሌ ተያዘ September 7, 2023 01:40 pm
  • “እንኳን ተለያይተንና እርስ በርስ ተባልተን በአንድነት ቆመንም ወጀቡን መሻገር አቅቶናል” September 7, 2023 01:31 am
  • ራሱን መሪ አልባ የሚያደርገው አማራ ክልል August 24, 2023 11:50 pm
  • ጀብደኛው August 24, 2023 10:06 am
  • ጎንደርና ባሕር ዳር ከተሞች ወደ ቀድሞ ሰላማቸው ተመልሰዋል August 13, 2023 10:55 pm
  • ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ግዙፍ ወታደራዊ ኃይል አስመረቀች August 13, 2023 10:26 pm
  • ሪፖርተር የፓርላማ ወንበር አስልቶ የአስቸኳይ አዋጁ በፓርላማ እንዳይደገፍ አቅጣጫ አመላከተ August 13, 2023 09:11 pm
  • ወደ ኤርትራ በኮንትሮባንድ የሚሻገሩ ቆሳቁሶች እየተያዙ ነው August 11, 2023 12:52 pm
  • የአማራ ክልል ትልልቅ ከተሞች ተኩስ ዓልባ ሆነው ውለዋል August 10, 2023 04:31 pm
  • “አንድ ሰው ለመግደል ኅንፃውን ማቃጠል” የኢ-ዲሞክራሲና ጽንፈኛ ኃይሎች ቅዠት፤ (ክፍል ሁለት) August 10, 2023 09:44 am
  • “አርበኛ” መሳይ – “የድል ዜና” ሳይበርድ 50ሺህ ዶላር በጎፈንድሚ August 10, 2023 09:08 am
  • በሕዝቡ ድጋፍ ከተሞች ከዘራፊው መንጋ ሥጋት ነጻ መሆናቸው ይፋ ሆነ August 9, 2023 11:47 am
  • ትህነግ አራተኛውን ሞት ሞተ  August 8, 2023 05:47 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule