በሀገር፣ በሕዝብና በቤተ ክርስቲያን ላይ በደል ሲፈጸም የጥንታዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት የሚያሰሙት ድምጽ
“ዘወሀብከነ ሥልጣነ በመንፈስ ንኪድ ኩሎ ኃይሎ ለጸላኢ ከመ ንፍታህ ዘኢይትፈታህ” ማለትም፦ “ጠላት ሰይጣን እንዳይፈታ አርጎ የቋጠረውን የችግር ሰንሰለት እንፈታ ዘንድ የቅስናዋን መንፈሳዊት ሥልጣን የሰጠኸን አምላክ” እያልን በምንገልጻት ተልእኮ በጥንታዊት ኢትዮጵያ ኦርቶቶዶክ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ያሰማራንን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን እያልን፤ እኛ ቀሲስ ዶ/ ር አማረ ካሳዬ እና ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ሐምሌ ፳፰ ቀን ፳፻፮ ዓ/ ምህረት በዋሸንግተን ዲስ በተደረገው ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ይህችን የቤተ ክርስቲያን ድምጽ አቀረብን።
ከኛ በፊት በህዝባችንና በአገራችን ላይ መከራና ስቃይ በደረሰባቸው ጊዜዎች ሁሉ፤ አባቶቻችን ቀሳውስት የእምነትና የስነ ልቡና ምንጭ የሆኑትን ቃላት የተጻፉበትን (ታቦተ ሕግ) ተሸክመው በገጠር በከተማ በቆላ በደጋ በተራራ በሸለቆ አቀበቱን ቁልቁለቱን በመውጣትና በመውረድ ከህዝባቸው ጋራ የእምነታቸውን የዜግነታቸውንና የቅስናቸውን ሀላፊነት ተወጥተዋል። አሁንም ወያኔ/ኢህዲግ አሰባስቦ ባዋቀረው መንግስት ከህዝባቸው ጋራ ከደብራቸው የተሰደዱ የተገረፉ የተገደሉ፤ ቀሳውስት ብዙ ናቸው። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply