በኢሊባቦር ዞን ዳሪሙ ወረዳ ዱጳ ከተማን ለማውደምና ለመዝረፍ አልሞ የመጣው የአሸባሪው ሸኔ ቡድን መመታቱን በስፍራው የሚገኘው የክ/ጦር ዋና አዛዥ ተናገረዋል።
የዘራፊው ስብስብ ቡድን ሠላምና ፀጥታ በመንሣት አካባቢውን የሽብር ቀጠና ለማድረግ እና የህብረተሠቡን የተረጋጋ ኑሮ ለማወክ አቅዶ ቢመጣም ከክ/ጦሩ ጋር የተጣመረው የፀጥታ ኃይሉ በከፍተኛ ቁርጠኝነት ሙትና ቁስለኛ በማድረግ አካባቢውን ከስጋት ነፃ ማድረግ መቻሉን ዋና አዛዡ ገልፀዋል።
ዋና አዛዡ አክለውም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል እና ማህበረሰቡ ያደረገውን ተጋድሎ በማመስገን ለቀጣይም ጠንክረው ለአካባቢያቸው ሠላም ከፀጥታ አካላቱ ጋር ተባብረው እንዲሠሩ መልዕክት አስተላልፈው የአሸባሪውን ሸኔ ስብስብ በገባበት ገብተን ለመደምሰስ ቀን ከሌት እንሠራለን ብለዋል።
ክፍለ ጦሩ እግር በእግር ተከታትሎ ከመታው የሸኔ ዘራፊ ቡድን ከህብረተሠቡ የዘረፋቸውን ኮምፒውተሮች፣ ሞተር ሣይክሎችን ጨምሮ የሽብር ቡድኑን የሚመሩት ናስር ኢብራሂም ፣ገመቹ ኢተፋ እና ገመቹ ወላኔ መማረካቸውን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ገልፀዋል። (FDRE Defense Force – የኢፌዴሪ መከላከያ ማርቆስ አለሙ ፎቶግራፍ ጥላሁን አለሙ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply