ከአዘጋጆቹ፤ በጎልጉል ወዳጅ ወለላዬ ጀማሪነትና አቀናባሪነት ሲስተናገድ የነበረው “እኚህ ሰው ማናቸው?” የተሰኘው ዝግጅታችን እንደገና ተጀምሯል፡፡ ለረጅም ጊዜ በመቋረጡ ይቅርታ እየጠየቅን አሁን ግን በወዳጃችን ወለላዬ ብርቱ ትጋት ለመጀመር በመቻላችን ለወለላዬ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ በዝግጅቱ ስትካፈሉ ለነበራችሁና መልሳችሁን ስትሰጡ ለነበራችሁ ሁሉ አሁንም ይህንኑ ማድረግ እንድትጀምሩ ልናሳስባችሁ እንወዳለን፡፡
የዝግጅቱ ዋና ዓላማ በአገራችን ስማቸውን ተክለው ያለፉ በፎቶ አስደግፎ የግጥም ጥያቄ ማቅረብ ሲሆን ተሳታፊዎችም ምላሻችሁን በግጥም እንድትመልሱ ትደፋፈራላችሁ፡፡ ታሪክ በሥነቃል ታጅቦ ያዝናናል፤ ዝርዝር ጥናት ለማድረግ ለሚፈልግ ደግሞ ብርሃን ይፈነጥቃል፡፡
ለአሁኑ የእኚህን ሰው ፎቶ በግጥማዊ ጥያቄ አጅበን አቅርበናል፡፡ ከላይ እንዳልነው ቢቻል በግጥም ምላሻችሁን ከሥር በመጻፍ እንድትተባበሩ ይሁን፡፡
ጥያቄ
ጀግና የት ይገኛል – በቸገረ ጊዜ
ብሎ የተባለው – የተነገረው ቃል
ተንፏቆ ተንፏቆ – ባሁን ዘመን ደርሷል
እኚህ የሚታዩት – ባለግርማ ኩሩ
ነበሩ በጊዜው – ጣሊያን ያባረሩ
ማናቸው ንገሩኝ – እስከ ማዕረጋቸው
በየትኛው ዘመን – ያዘመቱ ናቸው
Al says
Asrate Kassa
beshah አቦየ says
እንደ ብር እንደ’ቃ-ልጆች የገበረ፤
ትህትናው ሩቅ-ክቡር የከበረ፤
በሃገሩ ጉዳይ-ያልተደራደረ፤
ያበሻ ጀብዱ አንብብ-ካሳ ማን ነበረ?
በሰሜን ጦር ግንባር የለም ያልዋሉበት፤
ማይጨው ተሰበረ የጎራዴው ስለት፤
ሸብረክ የሚያደርገው ግርማ ሞገሳቸው፤
ዛሬ ያልተገኙት ራስ ካሳ ናቸው፤
sia says
Liuel Asrate Kassa, The father of jouralist Mulugeta Assrat.
Biniyam Tefe says
I’m interesting about the current issue for our Country and others. Please informe me.
Thank You!!
Mulugeta Andargie says
ለነጻነት የታገለ ይህ ነው!!