• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ትልቁ ሽልማታችን የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ማውለብለብ ነው” ከ190 ሀገራት 2ኛ የወጡት ተሸላሚዎች

October 18, 2024 09:32 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ190 ሀገራት በላይ የተሳተፉበት ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር በቅርቡ በግሪክ አቴንስ ታካሂዷል፡፡

7 አባላት ያሉት የኢትዮጵያ የፈርስት ግሎባል ቡድን በውድድሩ ተሳትፎ ከዓለም 2ኛ ደረጃ በመያዝ የብር ሜዳልያ ተሸልሟል፤ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ስሟን ማስጠራት ችሏል፡፡

ተማሪዎች የሳይንስ የቴክኖሎጂ የኢንጂነሪንግ እና የሂሳብ እውቀትን በመጠቀም ለአሁናዊ የዓለም ችግሮች ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመጠቀም መፍትሄ እንዲያመነጩ የተለያዩ እድሎች ይፈጠራሉ፡፡

እድሎችን በመጠቀም የራሳቸውን የቤተሰባቸውን የአከባቢያቸውን የሀገራቸውን እንዲሁም በዓለም ለሚታዩ ችግሮች መፍትሄ ያፈላልጋሉ፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የሶፎትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ ዳግማዊ ግሩም የቡድኑ መሪ ሲሆን ስለ ውድድሩ ሲናገር የዘንድሮው ውድድር ትኩረት የወደፊቷን ዓለም መመገብ (Feed The Future) የሚል ቻሌንጅ ነበር፡፡

የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምግብ ከማምረት እስከ ማጓጓዝ ያለውን ሂደት እንዴት በቴክኖሎጂ መስራት ይቻላል የሚለውን የመፍትሄ ሀሳብ ማስተማሪያ ሮቦቲክስ መስራት ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የቀረበ ፈተና እንደነበር ይናገራል፡፡

ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (ሮቦቶችን) በመጠቀም እንዴት ምግብ መማረት እንደሚቻል፤ የተመረተውን ምግብ ወደ ማከማቻ መጋዘን እንዴት ማጓጓዝ ይቻላል? ሮቦቶችን በመጠቀም በግብርን ስራ ላይ የተሻለ ምርታማ መሆን ብቻ ሳይሆን የተመረተውን ምግብ   ወደ መጋዘን በአግባቡ ማጓጓዝ ይቻላል የሚለውን በቴክኖሎጂ አስተማሪ ሮቦት መስራት በመቻላችን 2ኛ ደረጃ መያዝ ችለናል ብሏል፡፡

ከ100 በላይ ኪቶች ያሉት ሮቦት ተበታትኖ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች ተላከልን፤ ስራውና ዓላማው አንድ የሆነ ሮቦት ዲዛይን እንድንሰራ ቻሌንጅ ተሰጠን፤ የተላከውን የሮቦት ኪት በመጠቀም በውድድሩ ለማሸነፍ የተሻለና የተለያዩ ዲዛይን በመጠቀም ዓላማውን ማሳካት የሚችል ሮቦት መስራት መቻላቸውን ይናገራል ወጣት ዳግማዊ፡፡

የ18 ዓመቷ ወጣት ፅዮን ፍፁም ከሳፋሪ አካዳሚ የተገኘች የመጀመሪያ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት፡፡ “ውድድሩ አድካሚ ነበር፡፡ መጀመሪያ አከባቢ ባጋጠመን የቴክኒክ ችግር ጥሩ መጫወት ባንችልም ችግሩ ተስተካክሎ በጥሩ ሁኔታ መጫወት ችለናል፤ በልምምድ የሰራነውን በውድድሩ በመድገም ጥሩ ውጤት ማሳየት በመቻላችን 2ኛ ደረጃ መውጣት ችለናል፡፡” ብላለች፡፡

“ሀገራችንን ወክለን በውድድሩ 2ኛ ደረጃ መውጣታችን ሲነገረን በጣም ደስተኞች ነበርን፡፡ ይህም ደስ የሚል ትልቅ ስሜት ፈጥሮብናል፡፡ በሮቦቲክስ ውድድሩ ከዓለም 2ኛ ደረጃ በመውጣት ያገኘነው ትልቁ ሽልማታችን የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ማውለብለብ ፤ ሀገራችንን በዓለም መድረክ ስሟን ማስጠራት መቻላችን ነው” ብላለች፡፡

ወደፊት ብዙ ሰርታ በውድድሮች በመሳተፍ ሀገሯን ዳግም ማስጠራት እፈልጋለሁ የምትለው ታዳጊዋ በኢትዮጵያ ስለ ሮቦቲክስ ያለው አመለካከት እየተሸሻለ ቢሆንም አሁን ሰፊ ክተቶች አሉ ባይ ናት፡፡ ለዘርፉ ተገቢ ትኩረት መስጠት ከተቻለ ወደፊት የተሻለ ውጤት መምጣት እንደሚቻልም ታምናለች፡፡ ት/ቤቶች፤ መንግስት ለሮቦቶክስ ቴክኖሎጂ ምቹ አውድ ቢፈጠሩ ብቃት ያላቸው ታዳጊዎችን ማፍራት ይቻላል ብላለች፡፡

ኖህ ጌታቸው በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የ4ኛ ዓመት የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪና የፈረስት ግሎባል ቡድን የቴክኒክ ቡድን መሪ ነው፡፡ ከህፃንነቱ ጀምሮ ለቴክኖሎጂ ለፈጠራ ፍላጎት ያለው ሲሆን ከተሳተፉ 7 አባላት አንዱ ነው፡፡

ስለ ውደድሩ ሲናገር “አራት ኳስ መያዝ የሚችል ሮቦት መስራት ችለናል፡፡ እኛ ማሸነፍ የቻልነው ሆልሞኒክ ድራይቭ የሚባለውን ማለትም የሰራነው ሮቦት እየሄደ እያለ ወደ ፈለገው አቅጣጫ መዞር ሲፈልግ ወዲያው መዞርና ወደ ሁለም አቅጣጫ መሄድ አንዲችል አድርገን ነው የሰራነው፤ በዚህም ጊዜ መቆጠብ ይቻላል፡፡ አብዛኛዎቹ ሌሎች ተፎካካሪዎች የሰሩት ሮቦት 2 ኳስ ነበር የሚይዘው እኛ ግን በአንዴ 4 ኳስ መያዝ የሚችልና ዓላማውን ማሳካት የሚችል አስተማሪ ሮቦት ሰርተናል፡፡ ይህም እንድናሸንፍ በጣም አግዞናል” ብሏል፡፡

በሮቦቲክስ ውድድሩ ከዓለም 2ኛ ደረጃ በመውጣት ያገኘነው ትልቁ ሽልማታችን የሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ በስፍራው ማውለብለብ፤ ሀገራችንን በዓለም መድረክ ስሟን ማስጠራት መቻላችን ነው ሲሉ የፈረስት ግሎባል ቡድን አባላት ተናግረዋል፡፡

በአቴንስ በነበራቸው ቆይታ ከ30 ሀገራት 12 ጨዋታዎችን ማድረጋቸውን፤ የፈጠራ አቅማቸውን፤ የተግባቦት ክህሎታቸውን ማሳደግ መቻላቸውን የሚናገሩት የቡድኑ አባላት ወደፊት የሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ እና የሒሳብ እውቀትን አጣምሮ በመጠቀም ለተማሪዎች ተደራሽ ማድረግ ዓላማቸው መሆኑን ታናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ተስጥኦና ፍላጎት እያላቸው ግን እድል ያላገኙ ወጣቶች ብዙ ናቸው፤ ለእነዚህ እድል መፍጠር አቅማቸውን በማውጣት ለችግሮች መፍትሄ እንዲዘይዱ፤ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች መስራት እንደምንችል ለማሳየት የጀመርናቸውን ጥረቶች  ወደፊት አጠናክረን እንቀጥላለን  ብለዋል፡፡

ሮቦቱ ውስብስብ ቢመስልም ፍላጎት ካለ፤ ትኩረት መስጠት ከተቻለ አይከብድም፡፡ ወደፊት በኢትዮጵያ ሮቦቲክስን ማስፋፋት በውድድሮች ማሳተፍ፤ ሰው ሰራሸ አስተውሎትን እውቀት የሚጠይቅ ስለሆነ ፍላጎት ላላቸው ምቹ ሁኔታ ቢፈጠር ጥሩ ነው የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ሮቦት ሲባል የመጫወቻ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ስለ ሮቦቲክስ ያለው ግንዛቤ አነተስኛ ነው፡፡ ሮቦቲክስ ሰዎች እንደሚያስቡት መጫወቻ ሳይሆን ትልቅ ችግር ፈቺ የሆነ ኃላፊነት የሚጠይቅ ቴክኖሎጂ ነው፡፡ ስለ ሮቦቶ ሁሉም ሰው ትክክለኛ ግንዛቤ መፍጠር ይገባል፡፡ መንግስትም ለዘርፉ እድገት የጀመራቸውን የመሰረት ልማት ግንባታ አጠናክሮ ከቀጠለ ወደፊት የተሻለ ውጤት መምጣት ይቻላል  ብለዋል የቡድኑ አባላት፡፡ (ኢቢሲ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, News Tagged With: Ethiopia AI, Ethiopia First Global, Ethiopia Robotics, Feed The Future

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
Copyright © 2026 · Goolgule