• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጣመው ውይይት ፍሬያማ እንዲሆን ምን ይደረግ?

January 24, 2013 07:47 am by Editor Leave a Comment

በእኔና በአቶ አንዱ አለም ተፈራ መካከል እየተደረገ ያለው ውይይት እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል::  እየተወያየን ያለንው የጋራ ስለሆነችው አገራችን የወደፊት የፖለቲካ ዕድገትና ሁለንተናዊ ለውጥ መምጣት ስለምንችልበትና አሁን ላሉብን ፖለቲካዊ ችግሮች ሊፈቱበት ስለሚገባቸው አግባብ ዙሪያ ነው:: ይህም፣ የተለያዩ ሃሳቦች መንሸራሸርንና ጠንካራ የሃሳብ ፍጭትን የሚጠይቅ ነው:: ለዚህም፣ የሌሎች ተሳትፎ ወሳኝ ነው::

ይሄኛው ምላሼ ትንሽ ዘግየት ብሏል:: አንድም የተወሰኑ ቀናትን ከቤቴ ውጭ ለስራ ጉዳይ በማሳለፌ፤ ሁለተኛም እስኬ ሌሎች እንዲሳተፉ ጊዜ ለመስጥ፤ ሶስተኛም በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ የማቀረበውን ጥናታዊ ጹሁፍ ለማጠናቀርና ለመጨረስ ስሯሯጥ ስለነበር ነው:: መቼም አቶ አንዱ አለም ይረዱኛል ብዬ ተስፋ አረጋለው::

በምናረገው ውይይት ውስጥ “ያልተግባባንበት ጉዳይ ሁለታችንም አንድ ነገር እያልን፤መደማመጡ ላይ ትንሽ የተራራቅን በመሆናችን ነው“:: አዎ፣ በተወሰነ መልኩ መደማመጥ አለመቻል ትልቅ ችግር ነው:: የምናረገውን ውይይት ይበልጥ ፍሬያማ እንዲሆን መደማመጥ እና ሀሳቦቻችንን በግልጽ ማስቀመጥ በጣም ቁልፍ ነገሮች ናቸው:: የተግባባንባቸውን ሃሳቦች ወደ ጎን አድረገን አሁን እየተወያየንባቸው ያሉ መሰረታዊ ሃሳቦች የሚከተሉት ናቸው::

  • በመጀመሪያ ጹሁፌ እንዳመለከትኩት፣ የኔ የመከራከሪያ ጭብጥ በተቃማዊ ኃይሎች መካከል ያለው ትልቁ ችግርና ማዕከላዊ ጉዳይ ሊሆን የሚገባው ውስጣዊ ድክመት ነው ስል፤የእርሶዎ ደግሞ አይደለም ዋናው ችግርና ማዕከላዊ ጉዳይ ሊሆን የሚገባው የግብና የዕቅድ ልዩነት ነው፣
  • በትጥቅ ትግል ዙሪያ ያሉ ሃሳቦች፣
  • በሁለተኛው ጹሁፌ ሰፋ አርጌ ያየሁት እርሶዎ ያቀረቧቸውን 5 ጥያቄዎች ፖለቲካዊ ትርጉማቸው ምን ማለት እንደሆነ በኔ አረዳደድ ነበር ያቀርብኩት:: አሁን ግን የኔ የእርሶዎን 5 ጥያቄዎች አረዳድ ከእርሶዎ ጋር የተለየ መስሎ ይሰማኛል:: ከአምስቱ ጥያቄዎች ከአንድ እስከ ሶስት የተነሱት ሃሳቦች መሰረታዊና ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው:: አራተኛው ጥያቄ የፖለቲካ ባህላችንና የአስተሳሰብ ለውጥን የሚያመለክት ጥያቄ ነው:: በዚህ ጥያቄ ዙሪያ በመርህ ደረጃ ሁሉም ሰው አወንታዊ ሃሳብ ነው ያለው፣ አተገባበሩ ቢለያይም:: የመጨረሻው ጥያቄ እራሱን ችሎ የሚቆም ሣይሆን ከፖለቲካዊ ትንታኔ ተነስቶ አንድ ሰው ድምዳሜ የሚደርሰበትና በምን አይነት መንገድ ጥያቄው መመለስ እንዳለበት የሚደርሰበት ቁም ነገር ነው::
  • ስለዚህም በኔ በኩል እርሶዎን የምጠይቆዎት ከአንድ እስከ ሶስት ያስቀመጧቸውን ጥያቄዎች ፖለቲካዊ፣ ንድፈ-ሃሳባዊና ሀገራዊ ትርጉማቸውን ሊገልጹልን ይችላሉ? እነዚህ ጥያቄዎችን በዚህ መልኩ ማብራራትዎ አቶ ዱባለ (የእርሶዎ አስተያየት ሰጪ) ለነሷቸው ሃሳቦች በጠለቀ ሁኔታ የእርሶዎን ምላሽ ማግኘት ስለሚቻል ነው::
  • በጸረ-ቀኝ ግዛት ትግል ላይ የሰነዘርኩት ሃሳብ  አቶ አንዱ አለምን ቅር እንዳሰኘ ገልጸውልኛል:: በጣም የሚያሳዝነው እውነታውን ግን እኔ ልቀይረው አይቻለኝም:: በምንም አይነት መልኩ ግን ቀኝ ግዛትን እየደገፍኩ አይደለም:: ነጻ-አውጪዎቻችን እራሳቸው ነጻ አውጪ ያስፈልጋቸዋል እያልኩ እንጂ:: በጸረ-ቀኝ ግዛት ትግል ውስጥ የተሳተፉ ሰዎችን በተለይ በአመራር ደረጃ ላይ የነበሩና በኋላም ስልጣን ላይ የተቆናጠጡት እነማን ናቸው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ በቀላሉ የስትራተጂ ግሩፕ አናሊሲስ መስራትና ትልቁን ስዕል ማየት ይቻላል:: ይሄ እውነታ ግን ለነጻነት ሲሉ ለተሰዉት ሰዎች ያለኝን ክብርና አድናቆት አይቀንሰውም:: በነጻነትና በሰላም ስም ስንቱ አልቆ የለ እንዴ? ለዚህም እኮ ነው ታዋቂው ጋናዊ ሊቅ አዬቴ አፍሪካ ነጻ አይደለችም እያለ የሚከራከረው::
Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእምዬ ምኒልክ አዳራሽ October 30, 2023 10:27 am
  • የኢትዮጵያ መከላከያ መሥራች አጼ ምኒልክ መሆናቸውን ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ተናገሩ October 26, 2023 01:30 pm
  • ጥቅምት 15 ለምን? October 26, 2023 01:29 am
  • “በተፈተነ ጊዜ ሁሉ የሚፀና የድል ሠራዊት” October 26, 2023 12:57 am
  • “ውትድርና ሕይወቴ ነው” October 26, 2023 12:13 am
  • መከላከያ በሁሉም መስክ ኢትዮጵያን የሚመጥን ኃይል እየገነባ ነው October 20, 2023 05:07 pm
  • “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትምህርት ቤት እኩል ነው በችሎታው ነው እንጂ የሚመዘነው” ፕ/ር ብርሃኑ October 20, 2023 04:47 pm
  • 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ታሰሩ October 18, 2023 04:29 pm
  • በተማሪዎች ፈተና ውጤት ለታየው ውድቀት ትምህርት ሚ/ር ኃላፊ መሆን አለበት ተባለ October 18, 2023 04:00 pm
  • ቀይ ባሕር እና ዓባይ “የኅልውና ጉዳይ ናቸው”፤ “መተንፈሻ ወደብ ያስፈልገናል” October 13, 2023 10:04 pm
  • ከ3,106 ትምህርት ቤቶች 1,328ቱ (44%) አንድም ተማሪ አላሳለፉም October 10, 2023 01:51 pm
  • “አቋጥሬ” በአማራ ክልል እያጫረሰ ነው፤ ” ኑሮውን መቋቋም አልቻልንም ” ነዋሪዎች October 10, 2023 09:07 am
  • እሸቴ አሸባሪ፤ ቲዲኤፍ/ትሕነግ “ሰማዕት” – የዘመናችን ጉድ! October 7, 2023 06:47 am
  • በወልቃይት 1.1ሚሊዮን ኩንታል ሰሊጥ ለመሰብሰብ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሠራተኛ ይፈለጋል September 27, 2023 10:42 am
  • በአማራ ክልል ሰላም ዕጦት ከ90.5 ቢሊዮን ብር በላይ ፕሮጀክቶች ቆመዋል September 27, 2023 08:41 am
  • ወርቁ አይተነው የሸሹት ከዝርፊያ፣ ውንብድናና ዕዳ ጋር በተያያዘ ነው September 21, 2023 02:38 pm
  • ወደ አማራ ክልል ሊተላለፍ የነበረ መሣሪያና ሰነድ ተያዘ September 19, 2023 04:35 pm
  • በትግራይ መርዶ በይፋ ሊታወጅ ነው September 19, 2023 04:22 pm
  • ጃርቶች ለምን ይጮኻሉ? September 19, 2023 04:37 am
  • “ዐቢይ ግድቡን ሸጦታል” ጌታቸው ረዳ September 11, 2023 10:18 am
  • አቶ አገኘሁ መረጃ አሳልፎ በመስጠት ዋጋ እንደሚከፍሉ ተሰማ September 10, 2023 06:52 pm
  • ለዋዜማ ሬዲዮ “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ” ያደርጋል ያላችሁት ረቂቅ ሰነድ የታለ? September 10, 2023 01:58 am
  • ወደር የሌለው የኅብረተሰባዊት ኢትዮጵያ ጀግና! ብርጋዴር ጄኔራል ተስፋዬ ኃብተማርያም September 8, 2023 02:31 pm
  • የትግራይ መፍረስ በርዕሰ መስተዳደሩ አንደበት September 8, 2023 02:49 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule