በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የወያኔን ቡድን ከሥልጣን ለማውረድ የሚደረገው ትግል አሁንም ቀጥሏል። ይህ ትግል አንድነት የለውም። ይህ ትግል አንድ ማዕከል የለውም። ይህ ትግል አንድ መሪ የለውም። ያለንበትን መርምረን ወደፊት እንዴት እንደምንሄድ መወያየት አለብን። ለዚህ ይረዳ ዘንድ፤ በኔ በኩል መደረግ አለባቸው የምላቸውን እጠቁማለሁ። ይቺ ሀገር ያንቺም፣ ያንተም፣ የነሱም፣ የኛም የሁላችን የኢትዮጵያዊያን ሀገር ናት። ስለሆነም ሁላችንም ለወደፊቷ እኩል ባለጉዳዮች ነን። ማንም የነገዋን ሀገራችን እድል ሲወስን፤ እኛ የበይ ተመልካች መሆን አይገባንም። “ከወያኔ የተሻለ እስከመጣ ድረስ እኔ ምን ቸገረኝ!” ብለን ለሌሎች ጉዳዩን የምንተወው ሊሆንም አይገባም። አዎ የሚሻል ይኖራል። ያባሰም አለ። የሚሻለውም ሆነ የባሰው ሲመጣ የራሱን አጀንዳ ይዞ ስለሆነ የሚመጣው፤ እኛም ሆነ የሀገራችን ጉዳይ … [Read more...] about የተመሠቃቀለውን የፖለቲካ ውጥንቅጣችንና ነፃነታችን።
የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው
“አዲሱ ቴሌ እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ/ኢንሳ” በሚል ርዕስ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ያዘጋጀው ጥናታዊ ሪፖርት የታላላቅ አገር የስለላ ተቋማት፣ ለጉዳዩ አግባብ ያላቸው መምሪያዎችና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትኩረት መሳቡ ታወቀ። ሪፖርቱን አገራቱ በራሳቸው ቋንቋ በመተርጎም የህወሃት/ኢህአዴግን የስለላ መረብ ከተለያየ አቅጣጫ እየመረመሩት ነው። የጎልጉል ምንጭ የሆኑ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንዳስታወቁት አኢጋን የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም አዲሱ ቴሌን (ኢትዮ ቴሌኮምን) ከዋንኛው የስለላ መ/ቤት ብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ ወይም በእንግሊዝኛው … [Read more...] about የህወሃት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ እየተበረበረ ነው
ሕልም እንኳ የታለ?
ሕልም እንኳ የታለ? በሕልሜ ተኝቼ፣ ሸጋ ሕልም አይቼ በአገሬ በአፍሪካ ዲሞክራሲ በቅሎ ፍትህ፣ እኩልነት፣ መብቱ ተደላድሎ ወገኔ ሲያጣጥም የሰላምን ፍሬ ሽብር ተወግዶ በመላው አገሬ . . . ይህን እያለምኩኝ አልጋ ውስጥ አርፌ . . . ጥይት ቀሰቀሰኝ ከሞቀው እንቅልፌ፡፡ ሰሎሞን ሞገስ (ፋሲል) ከፀሐይ በታች መድብል 2004ዓ.ም “መሰላል” በሚል ርዕስ ላወጣነው የግጥም ጨዋታ ድንቅ ምላሽ በመስጠት ጨዋታውን ላደመቃችሁት በለው፣ ዱባለ፣ አሥራደው (ከፈረንሳይ) እና yeKanadaw kebede ከፍ ያለ ምስጋናችን ይድረሳችሁ፡፡ እያንዳንዳችሁ የቋጠራችሁት ግጥም በራሱ የግጥም ጨዋታ ሆኖ ሊቀርብ የሚችል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ዛሬ ለጨዋታ ያቀረብነው ግጥም ከዚህ በፊት “ሕልመኛው” በሚል ካወጣነው ጨዋታ ጋር በ“ሕልም” እንኳን የማይገናኝ መሆኑን ለመግለጽ … [Read more...] about ሕልም እንኳ የታለ?
በአረቢያ ምድር ለኢትዮጵያውያን ሽያጭ ተጠያቂው ማነው?
ሰው በፈለገበት ቦታና አገር የመዘዋወር መብቱ በሕገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል፡፡ በኮንትራት በቤት ሠራተኝነት ወደ አረብ አገሮች የሚሄዱ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስባቸዉ በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ መባባሱ ይሰማል። ኢትዮጵያውያኑ ላይ ከፍተኛ የሆነ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እየደረሰ ነው። ለዚህም በዋነኛነት ማሳያ የሚሆነው በተለያዩ የዓረብ አገሮች በቤት ሠራተኛነት በሚሄዱት እህቶቻችን ላይ የሚታየው የሞት፣ የአካል መጉደል፣ የመደፈርና ያለደመወዝ ማባረር ጥቂቶች ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት እንኳን ከዓለም ደቻሳ ጀምሮ በድብደባ ህይወታቸውን ያጡትን ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የተዳረጉትን የተደፈሩትን ከፎቅ የተወረወሩትን ለአእምሮ መቃወስ የተዳረጉት የትየለሌ ናቸው ኢትዮጵያዉያን የኮንትራት ሰራተኞች በአሰሪወቻቸው የሚደርስባቸውን ጥቃት ታዋቂ የሳዉዲ ጋዜጦች ሳይቀሩ በዝርዝር እየዘገቡት … [Read more...] about በአረቢያ ምድር ለኢትዮጵያውያን ሽያጭ ተጠያቂው ማነው?
“ቤ/ክናችን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች”
የዘመናት ታሪክ ባለቤትና ከትውልድ ወደ ትውልድ በመተላለፍ፤ ወደፊትም ለዘለዓለም የምትኖር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ የክርስቶስ ማደሪያ የምትባለው ዛሬ ኖሮ ነገ ለማይኖረው አምባ ገነንና ዘረኛ አገዛዝ መሣሪያ ሳትሆን ከተበደለውና መብትና ነጻነቱን ከተገፈፈው የኢዮጵያ ሕዝብ ጎን መቆም የቻለች እንደሁ ብቻ ነው። (ሙሉው ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about “ቤ/ክናችን አደጋ ላይ ነች፤ አድኑኝ ትላለች”
የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን
የዘወትር የድረገጻችን ተሳታፊ የሆኑ ይህንን ጽሁፍ እንድናነበውና እንድናትመው በላኩልን መሠረት እነሆ ለአንባቢዎቻችን አቅርበነዋል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ለጸሐፊዋ ማሕሌት ፋንታሁን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን አነጋገራችንን፣ አካሄዳችንን፣ አበላላችንን፣ አስተያየታችንን ባጠቃላይ የምናደርገውን ማንኛውም እንቅስቃሴ ላይ ቀጥጠኛ አስተዋፅኦ ካላቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው በኪሳችን ያለው ገንዘብ ዋነኛው ነው፡፡ ገንዘብ ከምናገኝባቸው አንዱ መንገድ ደግሞ ተቀጥሮ መሥራትና ወር ሲያልቅ የሠራንበትን ክፍያ/ደሞዝ ማግኘት ይገኝበታል፡፡ አብዛኛው በከተማ አካባቢ የምንኖር በዚህ መስመር ውስጥ እንገኛለን፡፡ ደሞዝ ተቀብሎ ቀጣዩን የደሞዝ ቀን እንደ ምፅአት ቀን በጉጉት የማይጠብቅ ካለ ይህ ሰው ከደሞዙ ውጪ ሌላ ተጨማሪ ገቢ አለው ወይም አንድ ቀልድ ላይ … [Read more...] about የደሞዝ Vs. የጠብሽ* ሰሞን
ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል
ሙስና በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱን ኢህአዴግ አይክድም። ኢህአዴግ ባለስልጣኖቹ በሙስና ስለመዘፈቃቸው ማመኑን የገለጸው “የመንግስት ሌቦች አስቸገሩኝ” በሚል ነው። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ “በሙስና የተለከፉ ዋጋቸውን ያገኛሉ” ሲሉ ስልጣን በያዙ ማግስት መዛታቸውን የሚያስታውሱ በስተመጨረሻ “ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል” የሚል ድምዳሜ ላይ ነው። “ትልቅ ጫካ ሰርታችሁ የኛንም የናንተንም ሌቦች መደበቅ በመቻላችሁ ሁሉንም መመንጠር ስላልቻልን እየተተራመስን ነው” በማለት ጣታቸውን ወደ ነጋዴው ህብረተሰብ በመቀሰር ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በአገሪቱ ያለውን ሙስና አስከፊነት በገለጹበት መድረክ “ስልጣን የመክበሪያ ብቸኛው መንገድ በሆነበት አገር ዘላቂ ሰላም ይኖራል ማለት ዘበት ነው። በኪራይ ሰብሳቢነት እንደ መንግስትም፣ እንደ ባለሃብትም መቀጠል አንችልም። እንደ … [Read more...] about ኢህአዴግና ኢህአዴግ ተፈራርተዋል
ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የ2012 ዓመተ ምህረቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ
እንደማንኛውም የአሜሪካ ኅብረተሰብ ሁሉ፤ በኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን፤ ማንኛውንም ምርጫ ከራሳችን ጥቅም አንፃር መመልከቱ ለሕልውናችን አስፈላጊ ጉዳይ ነው። እናም የ2012 ዓመተ ምህረቱን የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ምርጫ የምንመለከተው፤ ከዚህ ተነስተን ነው። እኛ ምን ሠራን? ምን ተጠቀምን? ምን ተጎዳን? ምን አገኘን? ምን ቀረብን? ምን ማድረግ ነበረብን? በመጨረሻ ደግሞ፤ ምን ትምህርት ወሰድን? ይህ ነው ለምርጫው ግምጋሜ ጠቅላላ ይዘቱ፤ ከኢትዮጵያዊ አሜሪካዊነታችን አንፃር ሲታይ። የባራክ ኦባማ ከጥቁር ዝርያ መሆኑ ወይንም የሚት ራምኒ ነጭ መሆን ቦታ አልነበረውም። የዴሞክራቲክ ፓርቲው ማቸነፍ ወይንም የሬፑብሊኩ ፓርቲ መቸነፍ፤ ለኛ ትርጉሙ በፓርቲነታቸው ሳይሆን፤ የኛን ጉዳይ በሚመለከት ባላቸው አቁዋም ነው። በአሜሪካን ፓርቲ ስሌት ደግሞ፤ የምንፈልገውን ለማግኘት፤ የሚተማመኑበት የአንድ … [Read more...] about ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያንና የ2012 ዓመተ ምህረቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ
ከእሁድ እስከ እሁድ
ኢህአዴግን በኃይል ለማስወገድ ጥሪ ቀረበ በኢትዮጵያ ያለውን አገዛዝ ለመጣል ይቻል ዘንድ ለቀድሞው ሰራዊት፣ አሁን በስራ ላይ ላሉት የመከላከያ አባላትና በአገር ውስጥና በውጪ ስደት ላይ ላሉ ዜጎች ሁሉ የትግል ጥሪ ቀረበ። “የግንቦት 7 ሕዝባዊ ኃይል” በሚል ስያሜ ጥሪውን ያስተላለፈው ክፍል ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ከሚመሩት ድርጅት ጋር ግንኙነት እንዳለው ለማጣራት ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት ኢሳት ዘወትር እሁድ በሚያቀርበው የሳምንቱ ዜናዎች ላይ አስታውቋል። ኢሳት በሰበር ዜና ያቀረበው ይህ ዜና ከዋናው የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ጋር ግንኙነት እንዳለውና እንደሌለው ለማጣራት ያደረገው ሙከራ ለጊዜው ባይሳካለትም፣ በቅርቡ ግን መረጃዎችን በማሰባሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ማብራሪያ የሚያቀርብ መረጃ ለመስጠት እንደሚተጋ አስታውቋል። በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለ ህዝብ ይሁንታ ላለፉት ሃያ አንድ … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ከሶሪያ መሪዎች ጋር የሚደረገው ንግግር ጊዜው አልፎበታል፤
የኮፊ አናን ተልዕኮ በሶሪያ ላለው ትርጉም ያለዉ ዉጤት ማስገኘቱ አያስተማምንም። ይህ፤ ግጭቱ በየትኛዉም መልኩ መመለስ የማይችልበት ጠርዝ ላይ በመድረሱ ብቻ ሣይሆን፤ ከጅምሩም ምናአልባት የሶሪያ ገዥዎች ከወዲሁም ቢሆን በሰላም ሽግግሩ እንዲከናወን ፈቃደኛ አይሆኑምና ነው። የበሺር አል አሳድ ገዢ ቡድን፤ ቅንጣት የለዉጥ ሙከራ ሳያደርግና ተቃዋሚዎችን ሳያግባባ፤ ለምን በኃይል እንቅስቃሴዉን ለማጥፋት የወሰነበትን፤ መረዳት ያስፈልጋል። ባለፈው ዓመት፤ የመካከለኛው ምሥራቅ አምባገነን ገዥዎችን፤ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች አናግተዋቸዋል። ሶስት ዓይነት ዉጤቶች ተከስተዋል። በቱኒሲያና በግብፅ፤ ያለ ብዙ ሕይወት ጥፋት ፈላጭ ቆራጮቻቸዉን አስወግደዋል። ዚን ኤል አቢዴን ቢን አሊ እና ሆዝኒ ሙባረክ፤ ያለ ሕዝባዊ የርስ በርስ ግጭት ከሥልጣናቸው ተባረዋል። በግብፅ፤ ሙባረክ የመጨቆኛ ክንዱ አድርጎ … [Read more...] about ከሶሪያ መሪዎች ጋር የሚደረገው ንግግር ጊዜው አልፎበታል፤