ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ ወደሌሎች ክልሎች በተስፋፋው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት “በሺዎች የሚቆጠሩ” የትግራይ ተዋጊዎች መሞታቸው፣ ሌሎች በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውና ዘላቂ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸዉ የክልሉ ባለስልጣናት ማስታወቃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዳስታወቀዉ በጦርነቱ ለሞቱ የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት፣ ቤተሰቦቻቸው በቅርቡ በይፋ መርዶ ይነገራቸዋል።
ዛሬ በመቐለ ከተማ የትግራይ የጦር ጉዳተኞች ማእከል ስራ ባስጀመሩበት ወቅት ንግግር ያደረጉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ፥ ቁጥሩን በትክክል ባይጠቅሱም “በሺዎች የሚቆጠሩ” ያልዋቸው የቀድሞ የትግራይ ሐይሎች አባላት በሁለት ዓመቱ ጦርነት መሞታቸውን አረጋግጠዋል።
የሟች ቤተሰቦችን ከማርዳት በተጨማሪ መስተዳድራቸዉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። (ዶቼ ቨለ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply