• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አጭር ማስታወሻ በሰማያዊ ፓርቲ የተቃውሞ ሠልፍ

September 5, 2013 08:57 am by Editor 2 Comments

ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ሰማያዊ ፓርቲ ታላቅ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱ የሚታወቅ ነው፤ ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት እንደሰፈር ጉልበታኛ ዱንኳን ሰባሪ ዘው ብሎ በሃይማኖት ስበብ ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ በህግ አግባብ ሣይሆን በጉልበት ሠልፍ መሰል ሠልፍ ማካሄዱ የሚታወቅ ነው፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተቃውሞ ሠልፍ በማድረግ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የተቃውሞ ሠልፈኞች እንዲሁም የአገር ውስጥና የውጪ የመገናኛ ብዙሃን በተገኙበት መንግስት ሊመልሳቸው የሚገባ ጥያቄዎችን የጠየቀ ሲሆን ለጥያቄዎቹም ምላሽ የሰጠው የጊዜ ገደብ ሦስት ወር መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ መንግስት በተሰጠው ጊዜ የተጠየቀውን ጥያቄ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ፓርቲውን በመወንጀል እና ስም የማጥፋት ዘመቻውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ መንግስት ላሣየው ቸልተኝነት እርማታ እንዲያደርግ በመግላጫ የጠየቀ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ከ1 ወር በፊት በፓርቲው ጽ/ቤት በተሰጠ መግለጫ ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ፓርቲው ቀድሞ ለጠየቃቸው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ በድጋሚ በተጠናከረ መልኩ የተቃውሞ ሠልፍ መጥራቱን ለመንግስትም ለህዝብም ተገልፃል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በሠላማዊና በህጋዊ መንገድ የሚታጋል እንደመሆኑ መጠን ለአ/አ መስተዳደር በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 30 ንዑሰ አንቀፅ 1 መሰረት በማድረግ ነሀሴ 13 ቀን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ስብሰባ ማሳወቂ ቢሮ ነሀሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም የተቃውሞ ሠልፍ አንደሚያካሂ ያሳወቀ ሲሆን፤ የከንቲባ ፅ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ስብሰባ ማሳወቂ ቢሮ ነሀሴ 15 ቀን ለፓርቲው በላከው በአስቸኳይ የደብዳቤ መልዕክት ሦስት ጥያቄዎችን ለፓርቲው ሲጠይቅ ሰማያዊ ፓርቲ ነሀሴ 17 ቀን የተጠየቁትን ጥያቄ በመመለስ የማሳወቂያ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡

ይሁን እንጂ የከንቲባ ፅ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍ ስብሰባ ማሳወቂ ቢሮ ምንም ዓይነት ምላሽ አልሰጠም፤ይህ ደግሞ የማሳወቂያ ደብዳቤ ከገባ በ48 ሰዓት ውስጥ ምንም ዓይነት ምላሽ ካልተሰጠ የተጠራው የተቃውሞ ሠልፍ እውቅና እንዳለው ይቆጠራል ተብሎ በአዋጅ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ሰማያዊ ፓርቲ በ48 ሰዓት ውስጥ ምንም ዓይነት ምላሽ ስላልደረሰው የህጉን ስርዓት ጠብቆ ለተቃውሞ ሠልፉ ዝግጅቱን አጠናክሮ በመቀጠል ላይ እንዳል ነሀሴ 20 ቀን የሀይማኖት ጉባሄ የተባለ በመንግስት ድጋፋ የሚንቀሳቀስ አካል ሰማያዊ ፓርቲ በጠራው ቀንና ሰዓት እንዲሁም ቦታ ሠልፍ መጥራቱ ታወቀ፡፡

ይህ ደግሞ ተገቢ አለመሆኑ ምን አልባትም ከመረጃ እጥረት ከሆነ ወይም ሌላ ምክንያትም ቢኖርም ሰማያዊ ፓርቲ የህግ አግባብ ተከትሎ ቀድሞ የያዘው ፕሮግራም መሆኑ እና ለተፈጠረው የፕሮግራም መደራረብ መንግስት በአስቸኳይ ማስተካኪያ እንዲያደርግ፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠሩ ማናቸውም ችግሮች መንግስት ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ሰማያዊ ፓርቲ በሰጠው መግለጫ አሳስቧል፡፡

ይህ በእንዲ እንዳለ ነሀሴ 24 ቀን 2005 ዓ.ም የአዲስ አበባ ፖሊሲ ኮሚሺን ሦስት የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን የንወያይ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ጥሪውን በማክበር በቦታው ተገኝተዋል፡፡ ‹‹የአ/አ አስተዳደር ፓርቲያቹ ለጠራው የተቃውሞ ሠልፍ እውቅና አልሰጠም በዚህም መሰራት ሰልፉን ማካሄድ አትችሉም›› በማለት ፖሊስ መስጠንቀቂያ የሰጠ ቢሆንም፤ የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ‹‹ፖሊስ ይህን የማለት መብት የለውም፤ የአ/አ አስተዳደር ፓርቲያችን ላስገባው ደብዳቤ በ48 ሰዓት ውስጥ የሰጠው ምንም ዓይነት ምላሽ የለም ይህ ደግሞ የጠራነው የተቃውሞ ሠልፍ የህግ አግባብነት ያለው ነው፤ በመሆኑም ምንም ዓይነት የህግ ስእተት ባለመፈጸማችን ሰልፉን እናካሂዳልን በዕለቱም ፖሊሲ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለበት››በማለት አሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ሰማያዊ ፓርቲ ዝግጅቱን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ነሀሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም ከ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ የፓርቲው አመራሮችና አባላቶች እንዲሁም ደጋፊዎች በፓርቲው ጽ/ቤት ቅጥር ጊቢ በማግስቱ እሁድ ለሚደረገው የተቃውሞ ሠልፍ እጅና ጎንት በመሆን ከምንም በላይ በሚያስቀና ጎዳዊ ስሜት ሲንቀሳቀሱ ማየት ብርታትም ፍቅርም የሚሰጥ ነው፡፡ይሁንእንጂ በመንግስት ሚዲያ በዕለቱ ማለትም ቅዳሜ ከ 7 ሰዓት ጀምሮ በማከታተል ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ህገ-ወጥ መሆኑና ሠልፉ ቢካሄድ ፓርቲው ሃላፊነቱን እንደሚወስድ በፖሊስ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎ በአባላቶች መካከል ሠልፉ ይካሄዳል ወይስ ምን ይሆን በማለት የእርስ በእርስ ንግግር ሲያደርጉ ሞቅ ሞቅ ያለው እንቅስቃሲ ከዝናቡ ጋር ተዳምሮ በጊቢ ውስጥ ቀዝቃዛ ስሜትን ፈጠረ፡፡

የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች አስቸኳይ ስበሰባ በማድርግ ፖሊስ በሰጠው ማስጠንቀቂያ ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ ላይ እያሉ አባላቶች ከስብሰባው ምን አይነት ውሳኔ ይተላለፍ ይሆን በማለት በጉጉት ይጠብቁ ነበር፡፡የፓርቲው አመራሮች ስብሰባ እንደጨረሱ ከአበላት ጋር በመሰብሰብ አመራሩ የደረሰበትን ውሳኔ የተቃውሞ ሠልፉ እንደሚካሄድ መንግሰት አየተከተለ ያለው የህግ ጥሰት አገባብ እንዳልሆነ እና ይህን አስመልክቶ የተቃውሞ ሠልፉ አብይ መፈክር ‹‹የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ ዘመቻ›› እንደተባለና አባላቶች አጠናክረው ስራቸውን እንዲቀጥሉ በሙሉ ድምፅ ውሳኔ ላይ መደረሱን ሲገልፁ በስብሰባው ላይ የተገኙ አባላቶች ጭብጨባና ደስታ እንዲሁም ያሳዩት የነበረው ቁርጠኝነት አመራሩ ያስተላለፈው ውሳኔ ትክክለኝነትን አጉልቶ የሚያሳይ ነበር፡፡

ዘመቻ ለህግ የበላይነት ከ10፡30 ጀምሮ በጊቢ ውስጥ እንደ ፍም እሳት ይፋጅ ጀመረ፤ አገራዊ ሙዚቃዎች ድምፃቸው ከፍ ብሎ ሲሰማ ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው እንደሚባለው ወጣትና አንጋፋ የፓርቲው አባላቶች የፓርቲውን ዓርማ በመያዝ ያሳዩት የነበረው እንቅስቃሴ እና ለአገራቸው ያላቸው ተቆርቋሪነት እንዴት ያለ የአገር ፍቅር ልክፍት ነው? ያስብላል፡፡ ወጪ ወራጁ መንገደኛ ሲጀምር የአግርሞትና አድናቆት እይታ ሲብስበት ተቀላቅሎ የድረጊቱ አንደ አካል ለመሆን ያሳይቱ የነበረው እንቅስቃሴ ሌላው አስደሳች ክስተት ነበር፡፡

ዘመቻ ለህግ የበላይነት በሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት ማምሻውን በድምቀት እየተካሄደ እንዳል በ4 የተለያዩ መኪናዎች ተጭነው የመጡ ሙሉ የጦር መሳሪያ ትጥቅ የታጠቁ የፌዴራል ፖሊሶች የፓርቲው መውጫና መግቢያ መንገዶችን በ50 ሜትር ዙሪያ በቅድሚያ ከበባ አካሄዱ፤ ቀጥሎም ቁጥራቸው ወደ 30 የሚጠጎ ሌሎች የፌዴራል ፖሊሶች የፓርቲው ጊቢ ጥሰው በመግባት መስኮትና በር በሃይል በመስበር ወደ ቤሮ በመግባት አባላትን በማገት በቤሮ ውስጥ የሚገኝ ንብረቶችን በማውደም የተቀሩትን በመኪና በመጫን ካሸሹ በኃላ የፓርቲው አመራርና አባላትን በመኪና ይዘው ሳይሆን ጭነው ወደ ጃንሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ይዟቸው ሄዱ፡፡

ወጣትና አንጋፋ የፓርቲው አባላቶች በጃንሜዳ የጠበቃቸው ነገር መጀመሪያ ሁሉም የሞባይል ስልካቸውን እንዲያጠፉና እንዲያስረክቡ፤ቀጥሎም ጫማቸውን እንዲያወልቁና እንዲንበረከኩ ሲሆን ከዚህ በኃላ የሆነው ነገር ስሜትን የሚነካና የሚያስቆጭ ነው፡፡ በፖሊስ ጣቢያ ጊቢ ውስጥ በሚገኝ የሽንት መውረጃ ቆሻሻ ቦታ ላይ በጀርባ በማስተኛት በብረትና በዱላ ፍፁም ሰብአዊነት በገደለው ሁኔታ አህያ እንኳን የማይችለውን ዱላ በሰው ገላ ላይ ፖሊስ ድብደባ ፈጸመ በዚህም ምክንያት በአባላቶች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰ፡፡

ይህ አይነቱ ኢሰብአዊ ድረጊት ከምሽቱ 3፡30 ፍፃሜ አገኘ፤ ወጣትና አንጋፋ የፓርቲው አባላቶች አብዛኞቹ ቆመው ለመሄድ በጣም ይቸገሩ ነበር ፤መኖሪያ ቤታቸው ቅርብ የሆኑ ወደ ቤታቸው ሲሄዱ ራቅ የሚሉት ደግሞ በጉሩፕ በመሆን ሰብሰብ በማለት በተለያዩ የፓርቲ አባላት መኖሪያ ቤት ለማደር ችለዋል፡፡

yidnekachew
ይድነቃቸው ከበደ የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሃላፊ

ወጣትና አንጋፋ የሰማያዊ ፓርቲ አባላቶች ይህን ሁሉ የዱላ ውርጂብኝ በመቋቋም በድጋሚ እንዲ ሲሉ ዘመሩ፤

የትግል ጉዞው ታሪካዊ

ዓላማው ፍጹም ህዝባዊ

ራዕይችንም ኢትዮጵያዊ

ሰማያዊ ሰማያዊ

ፓርቲያችን ነው ሰላማዊ

(ይድነቃቸው ከበደ  የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ሃላፊ)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Law Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Dersso says

    September 6, 2013 04:25 pm at 4:25 pm

    WE NEVER GIVE UP!!!
    The Ilegal measurment (Dictatorial Governance) of Woyane is his day to day action. We didn’t forget our vote which is amazinglly eatten by woyane during the 1997 E.C. ELECTION.
    Similarlly,the illegal action w/c is taken on BLUE PARTY(PEACE FULL PARTY) recently shows the terrorist is him self woyane 100% b/c he always don’t the CONNSTITUTION.This indicates that the END of woyane comming soon.The whole Dictatorial action give us strength!!!.
    We adult Ethiopians need a change &
    Our peace full stragle will continue !!!

    We Never give up!!!

    STOP HUMAN RIGHT VIOLENCE!!!

    LONG LIVE FOR ETHIOPIA !!!
    N.B.
    Internal & External medias (BBC) should invite during the dimonastration which show for the world illegal action of woyane.

    Reply
  2. asdf says

    April 15, 2014 02:41 pm at 2:41 pm

    Try to incorporate or unite or work together with ethnic parties. (Oromian ethnic parties, Sidama ethnic parties, Wolayita ethnic parties and so on)

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule