• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢንተርኔት በመዘጋቱ በትንሹ 9 ሚሊዮን ኪሣራ ደርሷል

October 22, 2016 02:05 am by Editor Leave a Comment

ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ለ30 ቀናት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ማጣቷን መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው ጥናት ጠቋሟል።

የብሩኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ዳረል ዌስት ባቀረቡት ጥናት በቅርብ ዓመታት ተጠቃሚዎች የሚገለገሉባቸውን የተወሰኑ አፕልኬሽኖች፤ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አሊያም መላውን የኢንተርኔት አገልግሎት መንግስታት ማቋረጥ እና መዝጋት እየተለመደ የመጣ ክስተት መሆኑን አትተዋል። ከእነዚህ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች። ከሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ለ30 ቀናት በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ይኸው ጥናት ጠቁሟል።

«መንግስታት ብሔራዊ እና የሕብረተሰብ ደሕንነት፤ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮች» የኢንተርኔት አገልግሎትን ለመዝጋት እንደ ምክንያት የሚያቀርቧቸው ምክንያቶች መሆናቸውን የሚናገሩት ብሩኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ዳረል ዌስት የመንግስት እርምጃ በውጭ ባለሐብቶች ላይ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ይናገራሉ።

«በእርግጠኝነት በውጭ ባለወረቶች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። እንዲህ አይነት የአገልግሎት መስተጓጎል ከተመለከቱ ገንዘባቸውን በአገሪቱ በሥራ ላይ ከማዋል ሊታቀቡ ይችላሉ። የኢንተርኔት አገልግሎትን መዝጋቱ የሚያስከፍለው ኤኮኖሚያዊ ዋጋ የከፋ ነው። ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴውን ያዳክመዋል። የገቢ ግብር ይቀንሳል። በንግዱ ሕብረተሰብ እና በመንግስት መካከል ያለውን መተማመንም ይጎዳዋል። ከዚህ በተጨማሪ በሸማቾች ላይም ተፅዕኖ አለው። ምክንያቱ በርካታ ሰዎች በሞባይል ገንዘብ ያንቀሳቅሳሉ።»

state-of-emergency-socialበሥልጣን ላይ ያለው መንግስት ከገጠመው ተከታታይ ህዝባዊ ተቃውሞ በኋላ የኢንተርኔት አገልግሎቱን መገደብ ብሎም ማቋረጥን መርጧል። የአገልግሎቱ መቋረጥ በቅርብ ጊዜ መልስ የሚያገኝ አይመስልም። በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር የሆኑት ሜቴ ታይጌሰን በትዊተር የማሕበራዊ ድረ-ገፃቸው እንዳሰፈሩት የኢትዮጵያ መንግስት የሞባይል ኢንተርኔት እና የማሕበራዊ ድረ-ገፆች አገልግሎት መልሰው ግልጋሎት የሚጀምሩበትን ተጨባጭ ጊዜ ማስታወቅ አልቻለም። የመንግስት የኮምዩንኬሽን ፅ/ቤት በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠው ማብራሪያ ነበር ይህን ያስታወቀው።

በኦሮሚያ እና የአማራ ክልሎች እንደ ዋትስአፕ እና ቫይበር ያሉ አገልግሎቶች ከተቋረጡ ሰነባብተዋል። ፌስቡክ እና ትዊተርን የመሳሰሉ የማሕበራዊ-ድረ-ገፆችም አዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የአገሪቱ ክፍሎች አገልግሎታቸው ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል አሊያም ከፍተኛ ገደብ ተጥሎበታል። ዳረል ዌስት እንደሚሉት አብዛኞቹ መንግስታት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሲያቋርጡ የሚያስከትለውን ጣጣ ከግንዛቤ ውስጥ አያስገቡም። ዳረል በጥናቱ የተዘጋው ኢንተርኔት ከአገሪቱ ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ጋር ያለውን ትስስር ለመፈተሽ ሞክረናል ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

«በጥናቱ መረጃውን ለማጠናቀር የተጠቀምኩበትን ሥሌት ይፋ በፅሁፉ አካትቼዋለሁ። በዋናኛነት የአገሪቱ አመታዊ የምርት መጠን፤ የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ የሚቆይበትን ጊዜ ርዝመት፤የዲጅታል ኤኮኖሚውን ስፋት በኢትዮጵያ ያለውን የሞባይል ተጠቃሚ ብዛት እና ኢንተርኔት መዘጋት የሚፈጠረውን ተደራራቢ ተፅዕኖ ፈትሸናል።»

ቀድሞም እጅግ ደካማ የቴሌኮምዩንኬሽን መሰረተ ልማት እና ከአጠቃላይ የአገሪቱ የህዝብ ቁጥር አኳያ ውስን የኢንተርኔት ተጠቃሚ የሚገኝባት የኢትዮጵያ መንግስት አገልግሎቱን ሳንሱር ያደርጋል እየተባለ ወቀሳ ይቀርብበታል። የኢትዮጵያ መንግስት ከጎርጎሮሳዊው 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ውስብስብ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የተጠቃሚዎችን የማሕበራዊ ድረ-ገፆች ይበረብራል መረጃዎችንም ያግዳል ሲል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ፍሪደም ሐውስ ይተቻል። ከኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ እንዳይደርሱ ገደብ የሚጣልባቸው ድረ-ገፆች መንግስትን የሚተቹ መረጃዎች እና የግለሰቦችን አስተያየቶች የሚያሰፍሩ መቀመጫቸውን በውጭ አገራት ያደረጉ ናቸው።

በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መልእክት ኢንተርኔትን ጨምሮ  በሞባይል፣ በፅሁፍ፣ በቴሌቭዥን፣ በፌድዮ፣ በማህበራዊ ሚድያ የሚደረጉ የመረጃ ልውውጦችን አግዷል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ ውሳኔ ከመድረሱ በፊት ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ጥቆማ ሰጥቶ ነበር።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት 71ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የታደሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ባደረጉት ንግግር ካነሷቸው ርዕሰ-ጉዳዮች መካከል የማሕበራዊ ድረ-ገፆች አጠቃቀም አንዱ ነበር። አቶ ሐይለማርያም በማህበራዊ ድረ-ገጾች የሚሰራጭ መረጃ በቀላሉ እንዴት እንደሚዛመት እና ሰዎችን በተለይም ወጣቶችን እንደሚያሳስት እየታዘብን ነው ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እውነተኛ ጥያቄ ያላቸው ሰዎችን ለፅንፈኞች መጠቀሚያ እያደረገ ነው። ጥላቻን ለማስፋፋት እየተጠቀሙበትም ነው ብለው ነበር። በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ ኩባንያዎችም ይሁን ሥራ ፈጣሪዎች እድሉ የላቸውም። የአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በኢትዮቴሌኮም ቁጥጥር ሥር ነው። የአገሪቱ መንግሥት ዘርፉን ለውጭ ባለሐብቶች እንዲከፍት የቀረቡለትን ጥሪዎች ሁሉ ውድቅ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ባንኮች፤ አገር አስጎብኚ ድርጅቶች እና የገንዘብ ዝውውር ተቋማት ግልጋሎታቸውን ከኢንተርኔት ጋር በማቆራኘት ለማፋጠን ሲያደርጉ የከረሙት ጥረት በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ፈተና ይገጥማዋል።  «በኢንተርኔት የሚሰጡ አገልግሎቶች በሁሉም አገሮች የአመታዊ የምርት መጠን ላይ እድገት እንዲፈጠር እያደረጉ ነው። ሰዎች በኢንተርኔት የሚያገኟቸው ግልጋሎቶች እና የሚያደርጓቸው ግብይቶችን እየወደዷቸው መጥተዋል።ብዙ ሰዎች ለመሰረታዊ ሸቀጦች ግብይት እና አገልግሎቶች ኢንተርኔትን መምረጥ ጀምረዋል። መንግስታት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሲያቋርጡ ራሳቸውን በዚያ ቦታ ላይ አድርገው መመልከት አለባቸው። ምክንያቱም የራሳቸውን የንግድ ሥራ እና ኤኮኖሚ እየጎዱ ነው።» ይላሉ ዳረል ዌስት

ብሩኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ዘገባ መሰረት ባለፈው ዓመት በ19 አገሮች የተከሰተ የኢንተርኔት መቋረጥ የ2.4 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ማድረሱን አትቷል። የዘገባው ጸኃፊ ዳረል ዌስት የኢንተርኔት መቋረጥ ወይም እንደ ዋትስአፕ እና ቫይበር ያሉ ማንቀሳቀሻዎች መታገድ ቤተሰብ፤ ጓደኛሞች ያላቸውን ግንኙነት ላይም የከፋ ጫና እንደሚያሳድር ገልጠዋል። በአነስተኛ የገንዘብ አቅም አዳዲስ የሥራ ኃሳብ ይዘው ገበያውን ለሚቀላቀሉ ጀማሪ ኩባንያዎች የኤኮኖሚ እንቅስቃሴውን በማዘግየት አሊያም ጨርሶ በማቆም የሚያሳድረው ጫና አለ። በዳረል ዌስት ዘገባ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ የኢንተርኔት መዘጋት ወይም መቋረጥ ከሚከሰትባቸው እንደ ሕንድ እና ሳዑዲ አረቢያ ተርታ ተቀምጣለች።

የኢንተርኔት አገልግሎት በተቋረጠባቸው አገራት የደረሰው ኤኮኖሚያዊ ጫና በሕንድ ከፍተኛ ነው። አገልግሎቱ በመቋረጡ ሕንድ 968 ሚሊዮን ዶላር፤ ሳዑዲ አረቢያ 465 ሚሊዮን ዶላር፤ ሞሮኮ 320 ሚሊዮን ዶላር፤ ኢራቅ 209 ሚሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጥሟቸዋል። የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚዘልቅ በመሆኑ የኢንተርኔት ግልጋሎቱ ወደ ነበረበት መቼ እንደሚመለስ ማወቅ ይቸግራል። በዚሁ ከቀጠለ ግን ኪሳራው ከፍ ማለቱ አይቀርም። (መረጃውን ያጠናቀሩት የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ባልደረቦቹ እሸቴ በቀለ እና ሒሩት መለሰ ናቸው)

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule