መቼም እኔና አንቺን ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን ይሄው ደግሞ ተሰደንም ልንስማማ አልደፈርንም። ሳትሰሚኝ አጣጥመሽ እኔም ያንቺን ሳላውቅልሽ መግባባቱ እንዳቃተን በየአቅጣጫው ተበታትነን ስንፋተግ ዕድሜ ገፋን። እውነታውን ስንሸሸው፣ መወያየት ስንፈራ ቀለብ ሆነን ሀሜት ጉራ። በይ ተይው ግዴለም፣ ድሮውንም ሲፈጥረን ጉዳችሁ አይለቅ ያለን ነን። ለነገሩ ትተነውስ ወዴት ልንደርስ ግደለሽም እኛው ደፍረን እንዋቀስ የዕለት የዕለቱን ትተነው ዘላቂውን እንመርምረው። የጋራ ችግራችንን ተነጋግረን በጋራ እንፈታለን እያልን በአፍ ብቻ ስንወተውት ከልብ አጣን ስምምነት። ስለሀገሬ ስለሀገርሽ አንቺም ስሚኝ፣ እኔም ልስማሽ! የማተያት፤ የማልተዋት የጋራችን አንድ ሀገር ናት። ታዲያ … [Read more...] about እኔና አንቺ … ፩
Archives for October 2013
ጥያቄው ሃይማኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ…
‹‹መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጣልቃ አይገባም፡፡›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 11 ንዕስ አንቀፅ 3፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው የማሰብ፤ የሕሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው፡፡ ይህ መብት ማንኛውም ሰው የመረጠውን ሃይመኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣ የመከተል፣የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለጽ መብትን ያካትታል፡፡›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕሱ አንቀፅ 1፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን እምነት ለመያዝ ያለውን ነጻነት በኃይል ወይም በሌላ ሁኔታ ማስገደድ ወይም መከልከል አይቻልም፡፡›› ሕገ መንግስት አንቀጽ 27 ንዕስ አንቀፅ 3 ፡፡ የሙስሊሞች ጥያቄ 1ኛ. በስልጣን ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች … [Read more...] about ጥያቄው ሃይማኖታዊ ነፃነት መብት ወይስ ፖለቲካዊ…