በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በተደረገ ክትትል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 1 መቶ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው ዶላር የተያዘው ሚያዚያ 28 ለ29 አጥቢያ 2013 ዓ/ም በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ላምበረት መናኸሪያ ግቢ ውስጥ ከለሊቱ 10 ሰዓት ገደማ ነው፡፡
ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ሊጓዙ የተዘጋጁ ሁለት ተጠርጣሪዎች በያዙት ሻንጣ ላይ በተደረገ ፍተሻ በጥቁር ላስቲክ የተጠቀለለ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን ፖሊስ ያስታወቀው፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ (ኢብኮ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply