• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኢሰመኮና የሪፖርተሩ ጎዶሎ ሪፖርት ብዙ ይነግረናል – አለ ገና!!

July 20, 2021 11:28 pm by Editor 2 Comments

ራሱን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ትህነግ) ብሎ በመጥራት ለበርካታ ዓመታት አገራችንን ሲያሸብር የኖረው እና በዓለምአቀፉ የአሸባሪዎች ቋት በአሸባሪነት የተዘመገበው፤ በቅርቡም በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት በአሸባሪነት የተመዘገበውን ትህነግ “አሸባሪ” ብሎ ለመጥራት ሲጨንቃቸው የሚታዩ የአገር ውስጥና የውጪ (እንደ ቢቢሲ፣ ቪኦኤ እና ጀርመን ድምፅ) ሚዲያ ተቋማት መኖራቸው በግልጽ እየታየ የመጣ ክስተት ሆኗል።

በቅርቡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ “ሕወሓትን የክልል መንግስት ማለት እና በክልል ደረጃ የመከላከያ ኃይል የሚል ስያሜ መጠቀም የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንን አለማከበር ነው” ካለ በኋላ “እነዚህን ስያሜዎች በሚጠቀሙ ሚዲያዎች ላይ ባለስልጣኑ ፈቃድ እስከመሰረዝ እርምጃ እንደሚወስድ” አስታውቋል።

በአገር ውስጥ የሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ይህንን ሕግ እና መመሪያ በግልጽ የሚጻረር ዘገባ ሰሞኑን አውጥቷል። ይህም በቅርቡ “የጁንታው ተላላኪዎችና አስፈጻሚዎች” ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጠቅሶ ይፋ ያደረገውን መረጃ በመጠቀም ነው።  

“ሪፖርተር ከኮሚሽኑ (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን) የሥራ ኃላፊዎች ባገኘው መረጃ መሠረት፣ ከአዲስ አበባ ከተማ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች የሕግ አግባብን ባልተከተለ መንገድ በተራዘመ እስር ላይ ናቸው” ሲል ከጥቂት ቀናት በፊት በዮሃንስ አምበርብር የተዘጋጀው የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል።

በዘገባው “ከአሸባሪው ትህነግ” ጋር እንዳይል “ተጠርጥረው” ሲል የገለጻቸው የትግራይ ተወላጆችን ነው። በጁላይ 15 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ያወጣውን ዘገባ በሪፖርተር ግንባር ዜና አድርጎ ጁላይ 18 ያተመው ሪፖርተር፣ ይህን ዜና እየሰራ ፖሊስ ለሰሩ ምክንያታዊ መረጃ ያለውን በምስል በማስደገፍ ይፋ አድርጎ ነበር።

በዕቅድ መፈጸሙ፣ በአጭር ሰዓት ውስጥ መከናወኑ፣ በርካታ ንጹሃን የታረዱበት፣ የታረዱት በሙሉ በስም፣ በአድራሻና በማንነት የሚታወቁ መሆናቸውና ምስክሮችም በገሃድ የሚገኙበትን የማይካድራ ዕልቂት ያድበሰበሰው በዶ/ር ዳንኤል የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ሪፖርተር ባተመው መግለጫው “በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርስ እንግልት፣ ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስርና ጥቃት በአፋጣኝ ሊቆም ይገባል” በሚል ርዕስ ነው።

ዮሃንስ አምበርብር “በትግራይ ክልል ግጭት ሳቢያ በአዲስ አበባ የተያዙ ሰዎች አዋሽ አርባ መታሰራቸው ተጠቆመ” በሚል መግቢያ ባቀረበው ዘገባ ከጅምሩ የዜናውን አቅጣጫ ለማስቀየር የሞከረ ሆኗል።
ፖሊስ “አሸባሪው ህወሃትን በተግባር ይደግፋሉ ተብለው የተጠረጠሩ 323 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ዋሉ” ሲል ሪፖርተርን ጨምሮ ለሁሉም መገናኛዎች ከላይ በተባለው ቀን አስታውቋል።

ዮሐንስ “ተጠርጥረው” ሲል “ፓርላማ አሸባሪ” ያለውን ድርጅትና በቁጥጥር ስር የዋሉት ሰዎች ብሄራቸው ሳይሆን ተግባራቸው ከዚሁ ድርጅት ጋር በተገናኘ መሆኑንን ፖሊስ ቢያስታውቅም በሪፖርተር ዜና ላይ አልተካክተተም።

ነዋሪነታቸው እንግሊዝ አገር የነበረው ዶ/ር ዳንኤል የሚመሩት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን “በትግራይ ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በሲቪል ሰዎች ላይ እንግልትና እስር፣ የንግድ ቤት መዘጋት፣ ብሎም በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መከሰቱንና ሕይወት መጥፋቱን፣ እንዲሁም በታሳሪዎችና በምርኮኞች ላይ የሚደርስ ኢሰብዓዊ አያያዝ፣ በስደተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ሕጻናትን ለውትድርና መጠቀም የሚያመላክቱ መረጃዎች እጅግ ያሳስበኛል” ሲል ካሰራጨው ዜና በተጨማሪ ዮሐንስ አምበርበር ስም ሳይጠቅስ ከኮሚሽኑ እንዳገኘ ጠቅሶ ተጨማሪ መረጃ ሲያጋራ ፖሊስ በሰጠው መረጃ ላይ ተኝቶ መሆኑ ሚዛናዊነት የነጠፈው በውጭ አገር ሚዲያዎች ብቻ ሳይሆን በአገር ቤትም በመሆኑ የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ጨምሮ የሚመለከታቸው ትኩረት ሊሰጡት ይገባል።

የኮሚሽኑ ሪፖርት እንዳለ ሆኖ፣ “የትግራይ ተወላጅ” የተባሉት መታሰራቸው ከህግ አግባብ ውጭ መሆኑ በመረጃ ከተረጋገጠ ለዜና ፍጆታ መጠቀሙ ሙያዊ ሆኖ ሳለ፣ ፖሊስ 323 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን፣ በይፋ አስታውቆ ኤግዚቢት ማግኘቱን በምስል አስደግፎ ቢያስታውቅም ለሪፖርተርና ለኮሚሽኑ አልታያቸውም።

በስጋትነት በተለዩ ግሮሰሪዎች፣ ጭፈራ ቤቶች፣ ሆቴሎች እና ሌሎች ንግድ ቤቶች በድምሩ 793 ተቋማት ላይ ፖሊስ ባደረገው ብርበራ እና ፍተሻ 126 ልዩ ልዩ ሽጉጦች፣ 918 የሽጉጥ ጥይት እና 124 የሽጉጥ ካርታዎች፣ 3 ክላሽኢንኮቭ ጠመንጃ፣ 390 የክላሽ ጥይት ከ4 ካርታ ጋር፣ 1 ኤስ.ኬ.ኤስ እና 1 ኡዚ መሳሪያ በኤግዚቢትነት ተይዘዋል።

ከተጠርጣሪዎቹ እጅ በርካታ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የቀድሞ የደንብ ልብስ፣ የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን፣ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ፣ የፖሊስና የሀገር መከላከያ ማዕረጎች እንዲሁም ልዩ ልዩ መለዮዎች እንደተያዙም ኮሚሽነር ጌቱ አብራርተዋል። ከእነዚህ በተጨማሪ ለፖሊስ ምርመራ የሚረዱ መረጃዎች የተገኘባቸው ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ ፍላሾች፣ ታብሌት ስልኮች፣ የባንክ የሂሳብ ደብተሮች፣ ሲም ካርድ፣ የፋክስ ማሽን እንዲሁም ጂ.ፒ.ኤስ. እንደተያዙ ኮሚሽነር ጌቱ ጠቅሰዋል።

የጁንታው ቡድን አባላት ውይይት ሲያደርጉበት የነበረ ቃለ ጉባኤ እና የህወሃት መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የጁንታው መልዕክት የተጫነባቸው ሞባይል ስልኮች መገኘታቸው የጁንታው ተላላኪዎች አደረጃጀት ፈጥረው እና ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሰቀሱ እንደነበር በምርመራ መረጋገጡን ኮሚሽነሩ አብራርተዋል። ፖሊስ ባደረገው ክትትልና ምርመራ ከ175 ሺ በላይ ብር እና 11 ሺ የአሜሪካ ዶላር እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ከጁንታው ተላላኪዎችና ደጋፊዎች እጅ ተይዟል።

በከተማችን አዲስ አበባ መንግስት የወሰደውን የሰላም ዕርምጃ ከሽንፈት የቆጠሩ ተሸሽገውና አንገታቸውን ደፍተው የነበሩ የጁንታው ተላላኪዎች በአንዳንድ መዝናኛ እና ጭፈራ ቤቶች ሰንደቅ አላማችንን በሚያዋርድ መልኩ ያልተገባ ድርጊት እየፈፀሙ ሲጨፍሩ ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል።

“ኮሚሽኑ ታሳሪዎቹ ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅና ለመጎብኘት የሚመለከታቸውን የመንግሥት ኃላፊዎች ቢጠይቅም፣ እስከ ዓርብ ሐምሌ 9 ቀን ድረስ ፈቃድ ማግኘት አለመቻሉን ማወቅ ተችሏል” ሲል ሪፖርቱ አልበቃ ብሎት ዮሃንስ አምበርብር ጉዳዩን ለማጣራት መንጠራራቱን የሚያሳየው ሪፖርት፣ እደጁ የቀረበለትን የፖሊስን መረጃ ባላየ ማለፉ ትልቅ ጥቁር ነጥብ ነው።

የቆየውን ብንተወው እንኳ በቅርቡ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ከመሬት፣ ከኮንዶሚኒየም ቤትና ከሊዝ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ደረጃ ተገምገምው እንዲነሱ መደረጋቸው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዮሐንስ አምበርብር ከእርሳቸው ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ “ስኳር ስኳር” የምትለዋን ዘፈን 50 ሺህ ጊዜ እንድንዘፍናት ያስገድደናል። ለታከለ ኡማ የተሰራው የማስተባበያ ቃለ ምልልስ እንዴትና ለምን በዚያ ደረጃ እንዲሆን እንደተፈቀደ የሪፖርተር ምንጮች በስፋት ያሉትን ለሌላ ጊዜ እናድርገው።

ኮሚሽኑ ያወጣው ሪፖርት፣ ሁሉም ሚዲያዎች የውጪዎቹ ሳይቀሩ የተቀባበሉትና ለእሁድ ሪፖርተር የተነዛ ወሬ ስለሚሆን አዲስ ሃሳብ አክሎ እንደ አዲስ ማቅረቡ ባይከፋም፣ የሚወቀሰው አካል ምክንያቱን በገሃድ አሳውቆ ሳለ ዝም ማለት አሁንም ያቺኑ ዘፈን እንደንደግም፣ እንደ ዜጋም አካሄዱንና ድሩን እንድንመረመር ያስገድዳል። ይህን አግባብ የሚመለከተው አካልም ያጤነዋል።

በጭፍን ኢትዮጵያ ላይ የዘመቱት የውጭ ሚዲያዎችና የውጭ መንግሥታት አጀንዳቸውን ማስፈጸሚያ ላያችን ላይ የተከሉብን የአማርኛ ፕሮግራሞች ብቻ ሳይሆኑ አገር ቤትም ያሉት ተንፈራጋጭ የኅትመት ውጤቶችም ስለመሆናቸው ይህ ዜና እንደ ምሳሌ ያገለግላል። ፖሊስ እንኳን ባይናገር ደውሎ መጠየቅ ያልተሞከረበት አግባብ ብዙ ያሳብቃል። በዜናው “ከአሸባሪው ጁንታ ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች” ብሎ ለመጻፍ የሚጓጉጣቸው ሚዲያዎች ፊትና ኋላቸው በጥብቅ ሊመረመር ይገባል እንላለን።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Editorial, Left Column Tagged With: ethiopian terrorists, operation dismantle tplf, rapist tplf, tplf children soldiers

Reader Interactions

Comments

  1. GI haile says

    July 21, 2021 12:42 pm at 12:42 pm

    ከሕወኣት ገበታ ያልበላ የለም ደግሞም ኣሁንም ሕወኣት ይመለሳል ብለው ሽያጭ በስርቆት፣በወንጀል፣በሙስና የተገኘች መሬት፣ኮንዶሚኒየምና ብር የተቀበሉ ሕወኣት በቀላሉ ከልባቸው ኣትወጣም። ወይ መቆየት ስንቱን የቀን ጅቦች ለራስ እንጅ ለጎረቤት፣ለሕብረተሰብና ለአገር ደንታ የሌላቸው ሕወኣት #2 የሐሰት ሚዲያ ናቸው።

    Reply
    • Miherete Tibebe says

      August 23, 2021 04:45 am at 4:45 am

      ይህን ሀሳብ በድንብ እሳማማበታለሁ!!
      <>

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • Rusted screws, metal spikes and plastic rubbish: the horrific sexual violence used against Tigray’s women July 4, 2025 01:48 am
  • በሞርሞን ቤ/ክ ዕርዳታ የኪዳነምህረት ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ማምለኪያ ሥፍራ አገኘች July 2, 2025 01:28 pm
  • የበረከት ስምዖን “አየር ላይ ትዕይንት” አየር ላይ ተበተነ July 2, 2025 01:24 am
  • “ዐቢይ ይውረድ፣ እኛ እንውጣ፣ በተራችን እንግዛ” ስልቴዎች (ስብሃት፣ ልደቱ፤ ቴዎድሮስ) June 11, 2025 01:56 am
  • ኤሊያስ መሠረት የሚሠራው ለማነው? ለብጽልግና? ወይስ …? June 3, 2025 01:27 am
  • በግንቦት 20 – የሁለት መሪዎች ወግ May 28, 2025 02:01 am
  • በፈቃዳቸው የተመለመሉ ወጣቶች ሁርሶ ሥልጠና ጀመሩ May 22, 2025 09:11 am
  • ድብቁ ሤራ ሲጋለጥ – “ሦስትን ወደ አራት” May 21, 2025 01:01 am
  • ከትግራይ ሾልኮ የወጣው ምሥጢራዊው ሰነድ ምንድነው? May 20, 2025 09:18 am
  • በደቡብ ጎንደር በጸዳሉ ደሴ የተመሩት 72 ታጣቂዎች እጃቸውን ሰጡ May 19, 2025 02:24 pm
  • የተመሠረተው የፋኖ አደረጃጀት ዋነኛ ዓላማው ድርድር መሆኑ ተነገረ May 14, 2025 11:07 pm
  • ከፍተኛ የፋኖ አመራሮች መገደላቸው ተነገረ May 6, 2025 10:40 pm
  • ሃይማኖትን ለተራ የፖለቲካ ሸቀጥ ማዋል ውርደት ነው April 24, 2025 12:43 am
  •  የኬሪያ ኢብራሒም ኑዛዜ “ብትንትናችን ወጥቷል” April 22, 2025 12:08 am
  • ለወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አመራሮች ወታደራዊ ሥልጠና ተሰጠ April 16, 2025 11:44 pm
  • ዓቅም እንደሌለው የገመገመው ሻዕቢያ ፊቱን ከጦርነት ወደ ዲፕሎማሲ እያዞረ ነው   April 15, 2025 12:32 am
  • “አንድ የፋኖ ተቋም (የእስክንድር) ተመሥርቷል፤ ሌሎቹ ደግሞ እንዲሁ አንድ ተቋም መሥርተው ወደዚህ ይመጡ” አበበ ጢሞ April 11, 2025 12:07 am
  • መለስ (ለገሰ) ዜናዊ – ተዋርዶ ያዋረደን! April 9, 2025 10:28 pm
  • የተከዜ ዘብ: የሉዓላዊነት መጠበቂያ April 8, 2025 11:49 pm
  • አዲስ አበባ አስተዳደር የሪፖርተርን የተዛባ መረጃ ኮነነ፤ ሕጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ አለ April 8, 2025 10:06 pm
  • ሀሰተኛውን የሪፖርተር ዘገባ ንግድ ባንክ በጽኑ ተቃወመ፤ እርማትም ጠየቀ April 8, 2025 09:48 pm
  • “ኦሮሚያ ላይ ወይም ሌላ ቦታ ላይ ስታደርገው ከነበረ ትግራይ ወስጥም የማታደርግበት ምንም ምክንያት አይኖርህም” ነው ጌታቸው ረዳ April 7, 2025 10:22 pm
  • “TPLF’s belief in a strong federal government was always tied to its own dominance in Addis Ababa” April 7, 2025 10:15 pm
  • Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation March 31, 2025 02:36 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2025 · Goolgule