ኢትዮጵያውያን በታሪካችን የታወቅነው በኩራታችንና ራሳችንን በማክበራችን ነበር፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የስዊስ አምባሳደርን ወያኔ አስፈራራውና በኢሰመጉና በሱ መሀከል የነበረውን ልዩነት አደባባይ አወጣው፤ ስለኢሰመጉ የሆነ ያልሆነውን ለመናገር መብት ያገኘህ የመሰለህ አሥር ሺህ ዶላር ስለሰጠኸን ነው፤ ይህንን አሥር ሺህ ዶላር መኪናዬን ሸጬም ቢሆን እመልስልሃለሁ ብዬ በጋዜጣ አወጣሁ፤ ይህንን ያነበበ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ እቤቴ ድረስ መጥቶ የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ሰጠኝና መከናህን አትሸጥም፤ ይኸውልህ አፍንጫው ላይ ወርውርለት ብሎኝ ሄደ፤ እኔም ለስዊስ አምባሳደር የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ላክሁለት፤ እሱም አልተቀበለኝም፤ በመቀስ ቆርጦ መለሰልኝ፤ ልናገር የፈለግሁት ዋናው ነገር ሁለት ነው፤ አንዱ ክብራችንን በገንዘብ የማንሸጥ እንደነበርን ለማስታወስ ሲሆን ሌላው ደግሞ ደጉን ጓደኛዬን … [Read more...] about “አልሸጥም ማለትም ዕብሪት አይደለም”
Opinions
የኔ ሃሳብ
የፕ/ር አስራት መታሰቢያ
በስዊድን የኢሳት እርዳታ ማስተባበሪያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
የኢሳት መዝሙር ተበረከተ ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. (ፌብሪዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.) በስዊድን የተደረገው የኢሳት መርጃ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ። ዝግጅቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት (13፡ 00) የተጀመረ ሲሆን፣ የዕለቱን ዝግጅት የመሩት ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አቶ በረከት ንጉሱ ነበሩ። በቦታው ላይ ዝግጅቱን ለመካፈል የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ በክብር እንግድነት የተገኙት ደግሞ ታዋቂዎቹ የኢሳት ጋዤጠኞች መሳይ መኮንን እና አበበ ቶላ (አቤ ቶክቻው) እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ከተንገላቱት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ውስጥ ዮሀን ፐርሾን ናቸው። ዝግጅቱን በጸሎት የከፈቱ በክርስትና ኃይማኖት በኩል ቄስ ፍስሀ ተስፋዬ፣ ሙስሊሙን በመወከል ደግሞ የተናገሩት ሀጂ ሁሴን ሺፋ ሲሆኑ፤ የጸሎቱ ሥነሥርዓት … [Read more...] about በስዊድን የኢሳት እርዳታ ማስተባበሪያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
የአድዋ ድልና እኛ
1.መቅድም ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው። ጳውሎስ ኞኞ ኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በሚለው መጽሃፉ እኛ ስለራሳችን ስንጽፍ እናጋንናለን ስለዚህ የውጭ አገር ምእራባውያን የመሰከሩልንን ተጠቅሜያለሁ ይላል። የጳውሎስ አንደኛውን ምክር ከልብ ማድረግ ነው። ሁለተኛ ቢያሳዝንም እውነት ስለሆነ የሰዎች ስም በክፉ ይነሳል፤ አያት ቅድመ አያት ለሰራው ባንጠየቅም የአያቶቻችን ስም ሲነሳ አለመቀየም ነው። ከተቀየማችሁም ምን ይደረጋል ከመጻፍ አይቀርም። ራስ ደስታ ዳምጠው በሁለተኛው የጣሊያን ጦርነት የደቡቡን ውጊያ የመሩ ለጣሊያን … [Read more...] about የአድዋ ድልና እኛ
ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ። መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት። "ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው። ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!" አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት እንጂ፣ የዶ/ር ቴድሮስ ትክክለኛው መልእክት እንዲህ ይነበባል። "ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጅቷን ባንጐዳ፡፡ ያሰበችው ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ በሪቱ ጃለታ አሕመድ ህልሟን እንድታሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው፡፡ Galatoomaa በሪቱ፡፡ አላህ ይባርክሽ፡፡ Rabbi si … [Read more...] about ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም
አዲሱ የወያኔ ዘመቻ!
በመጽሐፈ ገጽ (በፌስ ቡክ) ጓደኝነት ጥቂት የማልላቸው የኢትዮጵያዊነትን የሀገር የወገን የማንነት የቅርስ ተቆርቋሪነትን ስሜት የተላበሱ የሚያስቀናና የሚንቀለቀል ወኔ የተሞሉ እኅቶች ወንድሞች የመጽሐፈ ገጽ ጓደኝነት እየጠየቁኝ እየተቀበልኳቸው በተቻለኝ መጠንም እያበረታታሁ በጉድኝነታችንን እስከአሁን ቀጥለን ነበር፡፡ ለካ እነኝህ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሱና ወኔ የተሞሉ ቁጭት የሚበላቸው እያልኩ የማወድሳቸውና የተቻለኝን ያህልም ሳበረታታቸው የነበሩ ወንድሞችና እኅቶች ወያኔዎች ያሁሉ ስሜትና ተቆርቋሪነታቸውም ጭንብል ወይም ሽፋን ኖሯል ለካ ሰሞኑን እነኝህ ሰዎች በዘመቻ በየአቅጣጫው “ከአሁን በኋላ አማራ ስለ ራሱ ብቻ ማሰብ ይኖርበታል፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ስለራሱ ማሰብ ትቶ ለ80 ምናምን ብሔረሰብ ሁሉ ማሰብ ለድንበር መበላሸት አለመበላሸት ማሰብ የለበትም፣ አሁን 30 ምናምን ሚሊዬን … [Read more...] about አዲሱ የወያኔ ዘመቻ!
የዘንድሮ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እኮ አለፈኝ!
"ዋ…!ድምፄ ባከነ" ብዬ አምርሬ ልበሳጭ ዳድቶኝ ነበር፡፡ ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡ "ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል" ብሎ የሚያውቀውን ይመርጣል፡፡ ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡ "የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች" ብሎ የብብቱን ይመርጣል፡፡ ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡ "በቅሎ ማሰሪያዋን በጠሰች፤ በራሷ ላይ አሳጠረች" ብሎ አሳሪውን ይመርጣል፡፡ ወትሮስ፤ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን በሚሻልባት ሀገር፤ የብብት እንደተያዘ የቆጡ በማይወርድባት ሀገር፤ ማሰሪያዋን የበጠሰች በቅሎ ነፃ በመውጣት ፈንታ እስርዋን በምታጠብቅበት ሀገር፤ የኔ ድምፅ መጣ …ቀረ ልዩነቱ ምንድነው!? (ምንጭ: ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር - Hiwot … [Read more...] about የዘንድሮ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እኮ አለፈኝ!
ምርጫ እና ምርጫ በ2007!
ምርጫ 2007ን ከሌሎች ምርጫዎች ሁሉ ልዩ የሚደርገው ምርጫ ቦርድ ከምርጫው በፊት ፓርቲዎችን (ተፎካካሪ) በማፍረስ ጀምሮ የሰማያዊ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪዎችን (ከ200 በላይ) አልመዘግብም ማለቱ እና በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል ደግሞ ወደ ምርጫው ለመግባት ተወዳዳሪው በዕጣ መለየት አለበት ማለቱ ነው፡፡ ዕጣው ደግሞ ለሁሉም ፓርቲዎች ሳይሆን ሰማያዊን ጨምሮ ጥቂቶች ላይ የተደረገ ነው፡፡ ይኸውም በማፍረስ እና በመከልከል ተጀምሮ ”ምርጫ በሎተሪ” መሆኑ ነው፡፡ በዓለም ላይ በታሪክ ዴሞክራሲ በዕጣ ይረጋገጣል ሲባል ኢትዮጵያ ብቸኛ እና የመጀመርያ አገር ስትሆን በኢትዮጵያም ለመጀመርያ ጊዜ ሰማያዊ ፓርቲ በመወዳደሩ እና እንደሚያሸንፍ ስለታመነ እንጅ በ2002 በአንድ የምርጫ ክልል ከ18 በላይ ፓርቲዎች መወዳደራቸው አይካድም፡፡ እርግጥ ነው ህግ ከተባለ አዋ/ቁ 532/99 አንቀጽ 49 እንደ … [Read more...] about ምርጫ እና ምርጫ በ2007!
አስቂኙ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ!
የኢሳት ራዲዮና ቴሌቪዥን (ነጋሪተ ወግና ምርዓየ ኩነት) ጋዜጠኞች ከሕዝባዊ ግንባር መሪ አቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ተከታተልነው፡፡ ያው አስቀድሜ እንደገመትኩት በአሮጌው ድሪቶ ላይ አሮጌ ጨርቅ ድረታና እብለት ክህደት እንጅ የነበረውን አሮጌውንና ያላዋጣውን በመተው በአዲስና በተመከረ በተማረ ልብ አዲስ ሐሳብ አዲስ መንገድ ለመቀየስ አልተፈለገም፡፡ የሚጠበቀውና አስፈላጊው ግን ይሄኛው ነበር፡፡ ለነገሩ ከአንባገነን ሥርዓት ባለሥልጣናት ይሄ የሚጠበቅ አይደለም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እንኳን በአንድ ሰው ዕድሜ ሽህ ዓመታት የመኖር ዕድል ቢሰጣቸው እንኳን እስከ መጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ሱሪያቸውን በአንገት ለማጥለቅ እንደታገሉ ያልፋሉ እንጅ አይ ሐሳቤ መንገዴ ይሄንን ያህል ዘመን ብታገልም ሊሠራ አልቻለም፡፡ ሊሠራ ያልቻለበትም የራሱ ምክንያት ችግር ስላለበት ሳይሆን … [Read more...] about አስቂኙ የአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ!
የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ
እለተ ሰኞ ፌብሯሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ማለዳ አንድ ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767 የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ቆፍጠን ብሎ አኔ ነኝ ! ማለት። አንተ ማን? ምነው ምን ፈልገህ ነው ወደ አየር ክልላችን የገባኸው? የአየር ክልል ተቆጣጣሪዎቹ ቀጣይ ጥያቄ ነበር ። የበርካታ ወገኖቹን የብሶትና የግፍ መልዕክት ይዞ በስዊዝ አየር ላይ የሚያንዣብበው ሃይለመድህንም "ለጊዜው የምፈልገው የስዊዝ መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጠኝ ፣ ለኢትዮጵያ … [Read more...] about የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ










