ኢትዮጵያውያን በታሪካችን የታወቅነው በኩራታችንና ራሳችንን በማክበራችን ነበር፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የስዊስ አምባሳደርን ወያኔ አስፈራራውና በኢሰመጉና በሱ መሀከል የነበረውን ልዩነት አደባባይ አወጣው፤ ስለኢሰመጉ የሆነ ያልሆነውን ለመናገር መብት ያገኘህ የመሰለህ አሥር ሺህ ዶላር ስለሰጠኸን ነው፤ ይህንን አሥር ሺህ ዶላር መኪናዬን ሸጬም ቢሆን እመልስልሃለሁ ብዬ በጋዜጣ አወጣሁ፤ ይህንን ያነበበ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ እቤቴ ድረስ መጥቶ የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ሰጠኝና መከናህን አትሸጥም፤ ይኸውልህ አፍንጫው ላይ ወርውርለት ብሎኝ ሄደ፤ እኔም ለስዊስ አምባሳደር የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ላክሁለት፤ እሱም አልተቀበለኝም፤ በመቀስ ቆርጦ መለሰልኝ፤ ልናገር የፈለግሁት ዋናው ነገር ሁለት ነው፤ አንዱ ክብራችንን በገንዘብ የማንሸጥ እንደነበርን ለማስታወስ ሲሆን ሌላው ደግሞ ደጉን ጓደኛዬን አባተ የኔውን ለማስታወስ ነው፤ ግን ከዚህ ጋር ተያይዞ በአውሮፓና በአሜሪካ ኤምባሲዎች የነበረው መገረምና (እንደስድብም የወሰዱት ነበሩ) መደነቅ ነበር፤ አንዴት አንድ የደሀ አገር ሰው አሥር ሺህ ዶላር እጁ ከገባ በኋላ ይመልሳል! ይህ ዕብሪት ነው! አሉ፤ እኔ ደሀነት የሚያሳፍር መሆኑን ሳላውቅና ሳይሰማኝ እዚህ ደርሻለሁ፤ አልሸጥም ማለትም ዕብሪት አይደለም፡፡
እምሩ ዘለቀ says
We never expect less from Professor Mesfin.
His noble gesture and proud patriotism is an example to all.
selam says
Excellent, that is the Ethiopia I know and aspire to. While we should celebrate prosperity and success, we should never sell principle for avarice. That is the proud history I inherited and will never compromise it. Superb prof!
shemelsyimam says
EPRDF is a vagavoned gambler colaction l never expacetGOODTEINEGS from EPLF sane