• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

አዲሱ የወያኔ ዘመቻ!

March 8, 2015 12:32 am by Editor 1 Comment

በመጽሐፈ ገጽ (በፌስ ቡክ) ጓደኝነት ጥቂት የማልላቸው የኢትዮጵያዊነትን የሀገር የወገን የማንነት የቅርስ ተቆርቋሪነትን ስሜት የተላበሱ የሚያስቀናና የሚንቀለቀል ወኔ የተሞሉ እኅቶች ወንድሞች የመጽሐፈ ገጽ ጓደኝነት እየጠየቁኝ እየተቀበልኳቸው በተቻለኝ መጠንም እያበረታታሁ በጉድኝነታችንን እስከአሁን ቀጥለን ነበር፡፡ ለካ እነኝህ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሱና ወኔ የተሞሉ ቁጭት የሚበላቸው እያልኩ የማወድሳቸውና የተቻለኝን ያህልም ሳበረታታቸው የነበሩ ወንድሞችና እኅቶች ወያኔዎች ያሁሉ ስሜትና ተቆርቋሪነታቸውም ጭንብል ወይም ሽፋን ኖሯል ለካ ሰሞኑን እነኝህ ሰዎች በዘመቻ በየአቅጣጫው “ከአሁን በኋላ አማራ ስለ ራሱ ብቻ ማሰብ ይኖርበታል፣ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ስለራሱ ማሰብ ትቶ ለ80 ምናምን ብሔረሰብ ሁሉ ማሰብ ለድንበር መበላሸት አለመበላሸት ማሰብ የለበትም፣ አሁን 30 ምናምን ሚሊዬን አማራ ሕዝብ እስከ መኖሩም ለተዘነጋው በችግር በዘረኝነት በረሀብ በሥደት አለንጋ ለሚገረፈው የራሡ ቤተሰብ ብቻ ማሰብ መቻል አለበት፣ ሀገር ማንነት ምናምን እያለ የራሱን ህልውና አደጋ ላይ መጣል የለበትም” ከማለትም አልፈው ካርታ ሠርተው ጎንደር ጎጃም ወሎንና ሸዋን አካለው “መገንጠል ይኖርብናል” በማለት መገኝጠልን በማቀንቀን የምትገነጠለዋንም ሀገር “አማራ፣ ቤተ አማራ፣ አቢሲኒያ፣ ኢትዮጵያ፣ ግዮን” የሚሉ ስሞችን  ለምርጫ አቅርበዋል፡፡ ስለ ወደብ አገልግሎት ጥያቄ ሲመልሱም “እኛ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሀገር ድንበር ማንነት ምንትስ የሚለውን ትተን እራሳችንን ብቻ ካሰብን በራሳችን ጉዳይ ላይ ብቻ ካተኮርን ከሌሎች ጋር ሰላም ስለምንሆን የወደብ አገልግሎትን በጎንደር በኩል ከኤርትራ ማግኘት እንችላለን” ይላሉ፡፡ አንዳንድ ወገኖችንም ይሄ ሴራ የወያኔ መሆኑን ካለማወቅና የጨነቃቸው ወገኖች ያቀረቡት ሐሳብ መስሏቸው ለመደገፍ የዳዳቸው ሁሉ ነበሩ፡፡

ለአንደኛው ምን አልኩት፡-

ወንድሜ ምን ነካህ? ምን ሆንክ? ይሄ እኮ ተሸናፊነት ነው እጅ መስጠት እኮ ነው፡፡ እስኪ አሁን አንተን ከወያኔ ምን እንደሚለይህ ንገረኝ? ኢትዮጵያን ስለተውክ እንዴት ነው እራስህን ልታድን የምትችለው? ውጊያው እኮ አማራ ኢትዮጵያን እስኪተው እስኪጥል ማንነቱን ማለትም አማራነቱን እስኪክድ ድረስ ብቻ ሳይሆን ጨርሶ ዘሩ እስኪጠፋ ድረስ እኮ ነው፡፡ ምን ነው ሲበዛ የዋህ ሆንክብኝ? የትኛውንስ ክፍል ነው የምትገነጥለው? ወያኔ ከጎንደር ከጎጃም ከወሎ ውስጥ አገዎችን ቅማንቶችንና ሌሎች ወገኖችን እያነሣሣ ምን እንዲሉ እያደረገ እንደሆነ አታውቅም? ይሄ አስተሳሰብ የመጨረሻዎቹ የደናቁርቱ የድንቁርና የድንቁርና ብቻም ሳይሆን የጠላትነት አስተሳሰብ ነው የኢትዮጵያ ጠላት አስተሳሰብ፡፡ አንድነት ወይም የኢትዮጵያ ህልውና በምንም ተአምር ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ለሱም እንደ እናት አባቶቻችን ሁሉ የማንከፍለው የመሥዋዕተነት ዓይነት ሊኖር አይገባም፡፡ የኢትዮጵያ ነፍስ ያለው በአንድነቷ ውስጥ ነው አንድነቷ ከፈረሰ በድን ትሆናለች ትሞታለች፡፡ ኢትዮጵያ ከሞተች በኋላ ደናቁርቱና የጠላት ቅጥረኞች ይመስላቸዋል እንጅ በየትኛውም የፈራረሰ አካሏ ላይ ሰው መኖር የሚችልበት ዕድልና ሁኔታ አይኖርም፡፡ ለኢትዮጵያ መፈራረስ ተባባሪ የሆነ ሰው የሚጠየቀው በታሪክ ፊት ብቻ ሳይሆን በቅዱስ ቃሉ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ከ70 ጊዜያት በላይ በክብር በፍቅር በሞገስ በሚጠራት በእግዚአብሔር ፊትም ነው፡፡ ለኢትዮጵያ (ለእግዚአብሔር ሀገር) ጠላት መሆን ያስኮንናልና ተጠንቀቅ፡፡  አልኩት፡፡

ብቻ ምን አለፋቹህ በመጽሐፈ ገጽ ሰሞኑን እያያቹህት እንዳላቹህት ይህ ዘመቻ እንደኛ ናቸው ብለን እናስባቸው በነበሩ አሁን ግን ባልጠበቅነው መንገድ በራሳቸው ጊዜ ማንነታቸውን በገለጡት በወያኔ ካድሬዎች በሰፊው የተያዘ ዘመቻ ሆኗልና እንዳትሳሳቱ እንዳትሰናከሉ ማስጠንቀቅ እወዳለሁ፡፡ ይህ ዘዴ ወያኔ እስከዛሬ የያዘው የአማራን ብሔራዊና የባለአደራነት ስሜት ለማጥፋት የደከመው ድካም በፈለገው ፍጥነትና መጠን ውጤት እንዳላመጣለትና ብዙም ውጤታማ እንደማያደርገው ካወቀ በኋላ አዲስ የቀየሰው ስልት ነው፡፡ ነገር ግን በእኔ እምነት ይሄ የወያኔ አዲሱ የኢትዮጵያዊነትንና የባለአደራነትን ስሜት ከአማራ የማጥፋትና ሀገሪቱን ባለቤት ባለአደራ ተቆርቋሪ የማሳጣት እኩይና ሰይጣናዊ ዘመቻ እንደቀደመውና ሲሠራበት እንደቆየው ዘመቻው ሁሉ ይከሽፋል እንጅ ይሠራለታል ብየ አላስብም፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከሌሎቹ ብሔረሰቦች በተሳካ መልኩ አጥፍቻለሁ ብሎ ያስባል የቀረኝና ያቃተኝ አማራ ብቻ ነው ብሎ ያስባል፡፡ መስሎት እንጅ የኢትዮጵያዊነትን ስሜት ከኢትዮጵያዊያን አጠፋለሁ ማለት ቅዠት ነው፡፡ ከደሙ ጋር ተቀላቅሎ ያለ ነውና፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Garedew Shebebew says

    March 13, 2015 02:54 am at 2:54 am

    To the editor,
    This guy is a scum. I have seen two of his postings and all are aligned with woyane’s agenda. Woyane is smart in detecting ‘treats’ to its existence and works proactively to diffuse them. Woyane knows united and strong Amhara will be a challenge to its ambition to form its WoGaGoda State. That is why they are working 24/7 to alienate and destroy Amhara. So what is wrong if Amharas rise-up and fight back for existence? Amharas fought for Ethiopia for long and will continue to fight to the end. The question is should they continue to deny looking inward while they are being annihilated? How long can they fight for Ethiopia while constantly being destroyed in all aspects of their existence? We will rise! We will fight back! We will destroy woyanee!And we will rebuild our beloved Ethiopia where all its children can leave in degnity!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm
  • “የኢሳያስ አፈወርቂ ውድቀት አይቀሬ ነው … “ፅምዶ” ራዕይ ዓልባ” ነው – ሼትል ትሮንቮል October 26, 2025 10:15 pm
  • አሜሪካ ስላልተቀበለችው ነው “የሽሽግር መንግሥት” ስብሰባው በአምስተርዳም ተካሄደው October 25, 2025 11:09 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule