“ዋ…!ድምፄ ባከነ” ብዬ አምርሬ ልበሳጭ ዳድቶኝ ነበር፡፡
ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡
“ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን ይሻላል” ብሎ የሚያውቀውን ይመርጣል፡፡
ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡
“የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች” ብሎ የብብቱን ይመርጣል፡፡
ደግነቱ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ለተረቱ ታማኝ ነው፡፡
“በቅሎ ማሰሪያዋን በጠሰች፤ በራሷ ላይ አሳጠረች” ብሎ አሳሪውን ይመርጣል፡፡
ወትሮስ፤
ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን በሚሻልባት ሀገር፤
የብብት እንደተያዘ የቆጡ በማይወርድባት ሀገር፤
ማሰሪያዋን የበጠሰች በቅሎ ነፃ በመውጣት ፈንታ እስርዋን በምታጠብቅበት ሀገር፤
የኔ ድምፅ መጣ …ቀረ ልዩነቱ ምንድነው!?
(ምንጭ: ነቆራ እና ሌሎችም ወጎች ከሕይወት እምሻው ጋር – Hiwot Emishaw Facebook)
Leave a Reply