• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ማስታወቂያ ለህጻን ኢንቨስተሮች ከዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

March 8, 2015 07:41 am by Editor Leave a Comment

አሁን የምጽፈውን በደንብ አንብቡ።  መቶ በመቶ እውነተኛ ነው። እውነተኛ ኩሸት።

“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጆችን አንጉዳ። ሕጻናት የምታስቡት ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው። እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው። አሁን ዋናው ጉዳይ ህጻናት ህልማቸውን እንድናሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው።  ሕጻናት ሆይ 20 ሚሊዮን ዶላር ባትይዙም ቢሮዬ ብቅ በሉ!”

አይቴ ቴድሮስ በፌስ ቡክ ገጻቸው የለቀቁት መልእክት ይህ አልነበረም። ይህ አሸባሪዎች በርዘው የለቀቁት እንጂ፣ የዶ/ር ቴድሮስ ትክክለኛው መልእክት እንዲህ ይነበባል።

“ያልተገባ ነገር እየፃፍን ልጅቷን ባንጐዳ፡፡ ያሰበችው ፕሮጀክት የተቀደሰ ነው እንደሚሳካም እምነቴ የፀና ነው፡፡ አሁን ዋናው ጉዳይ በሪቱ ጃለታ አሕመድ ህልሟን እንድታሳካ የማበረታታትና የመደገፍ ነው፡፡ Galatoomaa በሪቱ፡፡ አላህ ይባርክሽ፡፡ Rabbi si haaeebbisu በርቺ፡፡ Jabaadhuu“

በማህበራዊ ድር-ገጾች ብዙ ፉገራዎች ከተራው ሰው ሲሰራጩ ቢታዩም፤ ነጭ ፉገራን በሚንስትር ደረጃ  ስናይ ግን የመጀመርያው መሆኑ ነው።

በፌስቡክ ላይ “የጀርመን ነዋሪ ነኝ” ያለችው ልጅ ፒያሳ ባር ስታስተናግድ ተገኘች። የፌስቡክ ጓደኞችዋ በድንገት ሲያገኟት ልጅት ምንም አልመሰላት። “ለምን ዋሸሽ?” ቢሉዋት። አይኗን በጨው አጥባ መልስ ሰጠች።

“መዋሸት ብርቅ ነው እንዴ?”  አለች። የሷን ፉገራ በመቶ እጅ የሚበልጡ ፉገራዎች ስለሚያጽናኗት ቅንጣት ያህል አልደነገጠችም።  ጣትዋን በቴድሮስ አድሃኖም ላይ እያነጣጠረች ጓደኞችዋን አረጋጋች።

የዚህችን ወጣት ውሸት ማካበድ እንደማያስፈልግ የተረዱት ጓደኞችዋ፣  ከውቅያኖስ የጠለቀውን፣ ከባህር የሰፋውን የቴድሮስ ውሸት ከሰሙ በኋላ ነበር።

“አበስኩ ገበርኩ . . . የባሰ አታምጣ።” ይላሉ እናቶች።

በአጼ ምኒሊክ ግዜ ለፍርድ ሙግት የቀረበ አንድ ሰው እጁን እያወራጨ ሲናገር ብብቱ ይታይ ነበር። እብብቱ ስር ያለ ጸጉሩም አጎፍሮ ነበር።  የብብቱን ጸጉር ያስተዋሉ ዳኛ፣  ችሎት በመድፈር ወንጀል 50 ጅራፍ ቀጡት። ሰውየው ቅጣቱን ሳይግደረደር ተቀበለ። ይህንን 50 ጅራፍ ለምን ሳይከላከል እንደጠቀበለ በጓደኛው ሲጠየቅ፣  ለብብቴ 50 የቀጡኝ የታችኛውን (የሃፍረተ ስጋዬን) ጎፈር ቢያዩ 100 ይሉኝ ነበር አለ።

“. . . የባሰ አታምጣ።” ነው ነገሩ።

ከዚህች ተራ ወጣት የባሰው ነጭ ውሸት በተጋለጠ ጊዜ፣

“የ14 አመትዋ ልጅ  በአውስትራሊያ የ8ኛ ክፍል አስደናቂ ውጤት በማስመዝገብ  ያገኘችውን 20 ሚሊዮን ዶላር  በኢትዮጵያ ለልማት ለማዋል ወሰናለች ያልኩት ፍጹም ስህተት ነው። ስለ ጥፋቴ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ተናገሩ።

የሚል ዜና ብንጠብቅ፣ ብንጠብቅ፣ ብንጠብቅ እስካሁን ልንሰማ አልቻልንም።  አቤ ጎርጉሮ ያወጣውን ቅሌት በፌስቡክ ከተለቀቀው የልደት ውስኪያቸው ጋር አወራርደውታል። ውሸቱ አሸማቆ፣ አሸማቆ፣ ይገድላቸዋል . . .  ድንጋጤው ይጥላቸዋል ብሎ የገመተ ጥቂት አይደለም።  ግን  እንዴት አይነት ፈጣጣ ናቸው። ያንን ጉድ ይዘው ቢሮ ሲገቡ ምንም እንዳልተፈጠረ መስለው ብቻ አይደለም። ውሸታቸውን ስልቅጥ፣ ዋጥ አድርገዋት ሌላ ጥፋት ደረቡበት።

“ህጻናትን ወደኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው።” የሚለውን የክርስቶስ ጥቅስ ቀየር አድርገው የራሳቸውን ፈንጠዝያ ሊነግሩን ሞከሩ።

“… ህፃናትና ታዳጊዎች የዋሆች እንደሆኑ ክፋት እንደሌላቸው ከኔ ጋር የምትስማሙ ይመስለኛል። በዚህ ምክንያትም ህፃናትና ታዳጊዎች የሚነግሩኝን ማመን እመርጣለሁ።  ስህተትም ቢኖራቸው ከየዋህነት ካልሆነ ከክፋት አይመነጭም። ህፃናትን ማመን ስህተት ከሆነ መሳሳትን እመርጣለሁ።…”

አይቴ ቴድሮስ በዚያ በልካቸው ባልተሰራ ወንበር ላይ ተቀምጠው ከሰሞኑ በርካታ ህጻናትን እንደሚያስተናግዱ ይጠበቃል። ከውጭም ከሃገር ውስጥም ኢቨስተር ህጻናት ወደ ቴድሮስ ቢሮ ይጎርፋሉ። በሚሊዮን እና በቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት እናደርጋለን ብለው ይዋሻሉ። ቴድሮስም በፌስ ቡክ ገጻቸው ታሪኩን ይለቀልቁልናል . . . ውሸቱንም ይለቁልናል። እነሆ ህጻናትን ማመን ስህተት አይደለምና እንዲዋሹ ተፈቅዶላቸዋል።

አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል የሚባለው እውነት ነው። ጭንቅላት ሲገለጥ ደግሞ ገመና ይወጣል። በህወሃት መዋሸት አዲስ ነገር አይደለም። ሰዎቹ በቀን ከመቶ ግዜ በላይ ይዋሻሉ። በስነልቦና ተመራማሪዎች እነዚህን ሰዎች ፓቶሎጂካል ውሸታሞሽ ይላቸዋል። ይህ በሽታ ሰዎች ካሉበት ችግር ለማምለጥ ወይንም ከተቆራኛቸው የበታችነት ስሜት ይመጣል። ውሸት መናገር፥ አንዳች ጥቅም ለማግኘት ሲባል ሆን ተብሎ የሚፈፀም ድርጊት ነው። ለዚህ  የስነ ልቦና ችግር ከጥቅሙ ይልቅ የረጅም ጊዜ ጉዳቱ ያመዝናል። የሚዋሸው ሰው  በሰዎች ዘንድ የሚኖረውን ተቀባይነትን የሚያሳጣ ስብዕናም ያላብሳል። ችግሩ የስነልቦና ነውና መፍትሄውም የስነ-ልቦና ህክምና ነው።

አንድ አባት ልጁን ይጠራውና “ልጄ፣ ጥፋት ካጠፋህ የቤታችን ውሻ ስለሚነግረኝ ተጠንቀቅ” ይለዋል። ልጁ ውሻ የሚሰማ እና የሚናገር ይመስለው ኖሮ ውሻውን እየቀረበ ያናግረው ነበር። ነብስ እስኪዘራ ድረስም ይህንን ውሽት አምኖ ተሸወደ።

የቴዎድሮስ አድሃኖም ግን ተገላቢጦሽ ሆነብን።  ነብስ እስኪዘራ ድረስ . . . ህዝቡን መሸወድ ተያይዞታል። በዚህ የመረጃ ዘመን ነጭ ውሸት ዋሽቶ ሲያበቃ፣ ውሸቱ ሲነቃ ሌላ ታሪክ መፍጠር ህዝቡን ዝቅ አድርጎ መመልከት አይመስልም? 20 ሚሊየን ዶላር እኮ ከ20ሺ ዶላር ይበልጣል። 20 ሚሊዮን ዶላር ከ 200 ሺም ይበልጣል። 20 ሚሊዮን ከ 2 ሚሊዮንም በ10 እጥፍ ይበልጣል። 20 ሚሊዮን  በጣም ተጋነነ። ከአንድ ጀምረው ቀስ በቀስ እያሳደጉ ወደዚያ ቢደርሱም አንድ ነገር ነው።

ጃፓኖች  እንዲህ ይላሉ። “የሚታመን ውሸት ለመዋሸት ከፈለግህ የማይታመን እውነት አትናገር።”

አይቴ ቴድሮስ በቅድሚያ ውሸትን በማንኪያ . . . ውሸትን በትንሹ ያለማምዱን! . . . ታዲያ እንደጀመሩ ይጨርሱልን።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule