• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በስዊድን የኢሳት እርዳታ ማስተባበሪያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ

March 11, 2015 12:03 am by Editor Leave a Comment

  • የኢሳት መዝሙር ተበረከተ

ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. (ፌብሪዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.) በስዊድን የተደረገው የኢሳት መርጃ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ። ዝግጅቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት (13፡ 00) የተጀመረ ሲሆን፣ የዕለቱን ዝግጅት የመሩት ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አቶ በረከት ንጉሱ ነበሩ።

በቦታው ላይ ዝግጅቱን ለመካፈል የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ በክብር እንግድነት የተገኙት ደግሞ ታዋቂዎቹ የኢሳት ጋዤጠኞች መሳይ መኮንን እና አበበ ቶላ (አቤ ቶክቻው) እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ከተንገላቱት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ውስጥ ዮሀን ፐርሾን ናቸው።

esat2ዝግጅቱን በጸሎት የከፈቱ በክርስትና ኃይማኖት በኩል ቄስ ፍስሀ ተስፋዬ፣ ሙስሊሙን በመወከል ደግሞ የተናገሩት ሀጂ ሁሴን ሺፋ ሲሆኑ፤ የጸሎቱ ሥነሥርዓት ካበቃ በኃላ ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ ስለስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ አቅም መጎልበት፣ ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት ስለመንደፍ እና ኢሳት ከተመዘገበበት ክፍል ጋር የስራ ትብብር ስለማድረጉ፣ እንዲሁም የድጋፍ ኮሚቴው የሚገለገልበት ድረገጽ ስለ መከፈቱ ገልጸው፤ ወደፊትም ስለተያዙት እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመጨረሻም ለኢሳት አሰራር ያልተቋረጠ ትብብር እያደረገ ላለው ለስዊድን የኢትዮጵያ ድምጽ ራድዮ እና ለፎከስ ቴሌቭዥን ምስጋና አቅርበዋል።

ቀጥሎ የእንግዶቹን ማንነት በሚገልጽ ትውውቅ ከተደረገ በኋላ ገጣሚ ማትያስ ከተማ (ወለላዬ) «…ባቡር ተመረቀ» በሚል ርዕስ ያገራችንን ሁኔታ የሚገልጽ ምጸት የተላበሰ ግጥም አቅርቧል። ከወለላዬ በተጨማሪ አቶ ማትያስ እንግዳዬ ደግሞ ኢሳትን የሚያወድስ ግጥም አቅርበዋል።esat3

ከዚህ በኋላ ስዊድናዊው ጋዜጠኛ ዮሀን ፐርሾን ንግግር አድርጓል። በንግግሩም ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር የቆየበትን ጊዜ የሚገልጽ «438 dagar» (438 ቀናት) በሚል በስዊድን ቋንቋ ከጋዜጠኛ ማርቲን ሺቤ ጋር የጻፉት መጽሐፍ በእንግሊዘኛ ተተርጉሞ ለስርጭት መብቃቱን አብስረዋል። አዲስ የጀመሩትም ”ብላንክ ስፖት” የሚተሰኘ ፕሮጀክት መኖሩን አሳውቀዋል።

esat4ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው በአይነቱ አዲስ የሆነው ለኢሳት የተበረከተው «ኢሳት የኛ ፋና» የተባለው የኢሳትን ግዙፍ ስራ የሚገልጽ መዝሙር ሲሆን፣ መዝሙሩ በሴቶችና በወንዶች ዘማርያን በሙዚቃ ታጅቦ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ ቀርቧል።

የዚህን መዝሙር ግጥም የጻፈው ገጣሚ ማትያስ ከተማ (ወለላዬ) ሲሆን፣ ዜማውን ያቀናበሩት ደግሞ አቶ ሚካኤል ወንድማገኝ (መርሶ) መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል። የመዝሙሩን ሃሳብ አፍላቂና አስተባባሪ ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ እንደሆኑ በተጨማሪ ለመረዳት ችለናል። ግጥሙን ለደረሱት፣ ዜማውን ላቀናበሩት፣ ለዘማሪያኑ እና በመዝሙሩ ዙርያ ተሳትፎ ላበረከቱት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል። በመጨረሻም የመዝሙሩ ዋና ቅጂ ለጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ለኢሳት እንዲያደርስ በአደራ የተሰጠ ሲሆን፣ አቶ አለማየሁ በቀለ ደግሞ በበኩላቸው ያዘጋጁት የኢሳት አርማ እና ጹሁፍ ያለበት በጨርቅ ተሰርቶ የተወጠረ የጥበብ ሥራ ለኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ በስጦታ አበርክተዋል።esat5

ቀጥሎ መድረኩን የያዘው ጋዜጠኛ አበበ ቶላ (አቤ ቶክቻው) ሲሆን፣ አቤ በተለመደ ጣፋጭ አቀራረቡ «ሥልጣንና አይሮፕላን እላይ ላይ ሆነው ሲያዩት ደስ ይላል» በሚል መርኅ-ሀሳብ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚነካ መጣጥፍ አቅርቧል። ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ደግሞ ለኢሳት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ያለውን ችግር በማብራራት የገለጸ ሲሆን፣ የኢሳት ትልቁ ስቱዲዮ ከኢሳት ግዙፍነት ጋር የማይመጣጠን መሆኑን አሳውቋል።

esat6ስለዚህ ኢሳትን ለማጠናከር ሁላችንም መስራት ይገባናል ብሏል። እንዲሁም በኤርትራ ቆይታው ጊዜ የተቀነባበረውን ምስል ለታዳሚው አሳይቷል። ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ በስካይፕ ቀርቦ የቻይናና፣ የበርማ እንዲሁም የወያኔ ኢትዮጵያ ሶሻሊስታዊ አገዛዞች ያላቸውን መመሳሰልና የአስተዳደር ሁኔታ በማብራራት ገለጻ አድርጓል።

ከሳዲቅ ንግግግር ማብቂያ በኋላ በአቤ ቶክቻው አጫራችነት የጣይቱ ሆቴል የቀድሞ ምስል ለጨረታ የቀረበ ሲሆን፣ ጨረታው በደመቀ ሁኔታ ከፍተኛ ፉክክር ተደርጎበት በ64 ሽህ የስዊድን ክሮነር ለአሸናፊዋ ለወ/ሮ የትምወርቅ ተሰጥቷል። መጨረሻ ባለው ሰዓት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በኤርትራ የትጥቅ ትግል ስለመኖሩ፣ የትግል እንቅስቃሴውን የሚያሳይ ቪድዮ አሳይቷል። በቪዲዮው ላይ ከተለያዩ ታጋዮች ጋር የተደረጉ ቃለምልልሶችና እንቅስቃሴ የታየ ሲሆን፣ ስለአንዳንድ ታጋዮችም የጀግንነት ስራ ማብራሪያ ሰጥቷል። ከዚህ በኋላ ዝግጅቱ ተጠናቆ ህዝቡ ተሸኝቷል።

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule