የሩስያ ኮሚኒስት አምባገነኖች ሕዝቡን ሰንገው በሚገዙበት ዘመን፤ አንድ ስመጥር ፈረንሳዊ ደራሲ ወደ ሞስኮ ጎራ ይላል፡፡ በጊዜው የመንግሥት ታጣቂዎች ተቃዋሚዎችን በማፈንና በመግደል ተጠምደው በማየቱ አዝኖ ቅሬታውን ላንድ ካድሬ ገለጸ፡፡ ካድሬው ቅሬታውን ከሰማ በኋላ “እንቁላል ፍርፍር ለመሥራት ከፈለግህ እንቁላሉን መስበር አለብህ” ብሎ ተፈላሰፈ፡፡ ደራሲው የዋዛ ስላልነበረ እንዲህ ብሎ መለሰት፤ “እዚህም እዚያም የእንቁላል ስብርባሪ ይታየኛል፡፡ ግን ፍርፍሩ የታል?” እስከቅርብ ጊዜ ስንሰማው የነበረው፤ “ዲሞክራሲን ቸል ያልነው ቅድሚያ ሕዝቡን ዳቦ ለመመገብ ነው” የሚለው መከራከርያ ውሃ በልቶታል፡፡ ዳቦውም ሆነ ዲሞክራሲውም ገደል ገብቷል፡፡ የምለው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡ በሀገሪቱ በየቦታው እየተፈጸመ ያለውን ግድያ በጊዜ አቁሙ! ገባሩ ህዝብ የሚላችሁን ስሙ፡፡ ስለ “ዘለቄታዊ … [Read more...] about “ሕዝብ ከሸፈተ ሠራዊት አያቆመውም” መለስ ዜናዊ
Opinions
የኔ ሃሳብ
ወያኔ በራሱ ወጥመድ
ራስን ሳያታልሉ ሌላውን ማታለል አይቻልም፤ ለራስ ካልዋሹ ለሌላ ሰው መዋሸት አይቻልም፤ ዞሮ ዞሮ ወደቤት እንደሚባለው ዞሮ ዞሮ ማታለልም ሆነ ውሸት ማደሪያ ሲያጡ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፤ ያኔ ፈጣሪና ፍጡር ይፋጠጣሉ፤ ፍጡር የማታለያ ልብሱን አውልቆ በዓለም ፊት ራቁቱን ይቆማል፤ በከመረው ውሸት መጠን ነቀፌታ ተሸክሞ ያቃስታል፡፡ የታወሩት ዓይኖቹ ይከፈቱና ሕይወት ነጠላ አለመሆኑን፣ በማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ውጣ-ውረድ መኖሩን፣ ጥላቻና ፍቅር፣ ጤንነትና ሕመም፣ ደስታና ሐዘን መፈራረቃቸውን፣ የግለሰብ ሕይወት በሞት ተሸንፎ መሻሩን፣ ገንዘብ የማይገዛው ነገር መኖሩን፣ ገንዘብ በከበደ መጠን ማቅለሉን አለማወቅ፣ ገንዘብ የማይመክተው ጦርና በገንዘብ ሊታጠቀው የማይችል መሣሪያ መኖሩን አለማወቅ፣ የደከመ እንደሚያይልና ያየለ እንደሚደክም፣ ዓለማችን በጣም የተያያዘና የተቆራኘ በመሆኑ አንዱን … [Read more...] about ወያኔ በራሱ ወጥመድ
የሞረሽ የአቋም መግለጫ
እኛ የሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት ማዕከላዊ ምክር ቤት አባላት እሑድ ኅዳር ፳፮ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. (Sunday December 6, 2015) ባደረግነው የማዕከላዊ ምክር ቤቱ ሰባተኛ መደበኛ ስብሰባ ፣ በማዕከላዊ ምክር ቤቱ ስድስተኛ መደበኛ ስብሰባ በጸደቁት የ፮(ስድስት) ወራት የሥራ ዕቅዶች አፈጻጸም ምዘና ሪፖርት፣ በድርጅቱ የቁጥጥርና ፍተሻ የአካላትና የአባላት የሥራ እንቅስቃሴና የገንዘብ አሰባሰብና አጠቃቀም ሪፖርት በአንክሮ አዳምጠን አስፈላጊውን ውይይት በማድረግ ሪፖርቶቹ ከምክር ቤቱ አባሎች የቀረቡትን ገንቢ ሀሳቦችን አካትቶ የድርጅቱ ቋሚ ሰነድ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወስነናል። ከሁሉም በላይ በዚህ መደበኛ ስብሰባ ምክር ቤቱ አጽንዖት ሰጥቶ ሠፊ ጊዜ ወስዶ የተወያየበት «የድርጅቱን ዓላማና ተልዕኮ በተሻለ መንገድ እንዴት ማከናወን ይቻላል?» ለሚለው ጥያቄ ተገቢና ሁነኛ መልስ … [Read more...] about የሞረሽ የአቋም መግለጫ
ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ?
ሐሙስ 20 – 01 – 2003፣ ጋምቤላ ከተማ፡ የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አዲሱን የስራ ዘመኑን የመጀመሪያውን የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ በማጽደቅ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ በመዝጊያው ስነ ስርዓት ላይ በጊዜው የክልሉ ፕሬዝደንት የነበሩት ኡሞት ኡባንግ ባደረጉት ንግግር፡ ‹‹ጋምቤላን ወደ ቀድሞው ክብሯ እንመልሳታለን፡፡ ያችን አኙዋዎች፣ ኑዌሮች፣ መዠንገሮች፣ ኦፖዎች፣ ኮሞዎችና ደገኞች አንድ ላይ በሕብረት የሚኖሩባትን - ጋምቤላ፡፡ ሁላችንም አፍሪካዊያኖች ነን፡፡ ጥላቻና ልዩነት ለማናችንም አይበጁንም…›› በማለት የሁሉንም ተሰብሳቢዎች ልብ የሚነካ ሃሳብ አቀረቡ፡፡ 156 መቀመጫዎች ያሉት የክልሉ ምክር ቤትም በጭብጨባ ተናጋ፡፡ ኡሞት ይሄን ታሪካዊ ንግግር ሲያደርጉ ከኡሞት ጎን የተቀመጡት የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ አሽኔ … [Read more...] about ጋምቤላ: የፌደራሊዝሙ ክሽፈት ማሳያ?
የአቶ ዠ የልማታዊ አርቲስትነት ደብዳቤ
አቶ ዠ ደብዳቤ ጻፉ። 40 አመት ሙሉ መፈክር ሲጽፉ ኖረው፣ ኖረው፣ ኖረው አሁን አርቲስት ለመሆን የሚያበቃውን ዝግጅት የጨረሱ መስሎ ተሰማቸው። ሰሞኑን ለወጣው ማስታወቂያ “ብቁ ነኝ” ብለው አሰቡ። ይድረሥ፣ ለ“ኢሃዲግ ፍቅር” ቴአትር ቤት “ሥራ አስቀማጭ”፣ ይቅርታ በቀድሞ ሥሙ የሃገር ፍቅር ቴአትር ቤት በመባል ለሚታወቀው ... ሥራ አስኪያጅ፣ ጉዳዩ፣ በ 23/2/2008 የወጣውን ማስታወቂያ አስመልክቶ፣ ከታች እንደሚታየው፣ የተለያዩ ኪነጥበባዊ ሥራዎችን ለማቅረብ “ልማታዊ” ፍላጎትን ሥለመግለጽ። የወጣውን ማስታወቂያ አስታኮ የተለያዩ ልማታዊ ኪነጥበባዊ ሥራዎችን ለማቅረብ 40 አመታት ሙሉ ተዘጋጅቻለሁ፣ ብቃት ያለኝም ነኝ። ከዚህ ኪነጥበባዊ ሥራ የሚገኘው ገቢም በከፊል ለታላቁ “ውዳሴ” ግድብ ቦንዳ (ይቅርታ “ቦንድ”) መግዣ እንዲውል ለመስማማት በገዛ ፍላጎቴ እገደዳለሁ። ይቅርታ … [Read more...] about የአቶ ዠ የልማታዊ አርቲስትነት ደብዳቤ
ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው
የሰሞኑ ርህራሄ የጎደለው የመንግስት እርምጃን የሚያሳዩ ዜናዎችና ምስሎችን ማየት እጅጉን ያማል፡፡ ገዢዎቻችን የህዝብን ቅሬታ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የሚባል ነገር ከራቃቸው ሰነባብተዋል፡፡ በውይይት ከያዙት አቋም የተመለሱበት ጊዜያት ጥቂት ቢሆንም፣ ከህዝብ ተቃውሞ ሲነሳ ተወካዮችን በማስመደብ እና ሽማግሌዎችን በመላክ ድርድሮችና ውይይቶች ይደረጉ የነበሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በመንግስትም ላይ ሆነ በስሩ በሚያስተዳድራቸው ተቋማት ላይ ለሚነሱ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች ዘግናኝ እርምጃዎች መውሰድን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተያይዞታል፡፡ ከሰሞኑም በአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ዙሪያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድረስ እየተወሰደ ያለው ዘግኛኝ እርምጃ የስርአቱን ማን አለብኝነትና የአመራሩን ጭካኔ በግልፅ የሚያሳይ … [Read more...] about ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው
እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ!!
ኢቢሲ “በቀኑ ዜና እወጃየ በጎንደር ማረሚያ ቤት ትላንት በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሞተ ሰው የለም ብየ የዘገብኩት ኮማንደር ሰይድ ሃሰን የሚባሉ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ "ዋሽተው" መረጃ ስለሰጡኝ ነው … ሃቁ ግን 17 እስረኞች ከእሳቱ ለማምለጥ ሲሞክሩ እርስ በእርስ ተረጋግጠው ህይወታቸው አልፏል ይህንንም የአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሸን ኮሚሽነር አስተዳደር ሃላፊ በላይ ዘለቀ የሚባሉ (ስሙንማ ይዘውታል) ገልፀውልኛል” ሲል ማምሻውን አስተባብሏል … (አላግጧል) መቸስ የሞተ ሰው የለም ብለው 17 ከሞተ … 17 ሰው ብለው ካመኑ የሟቹ ትክክለኛ ቁጥርም ሌላ ሊሆን ይችላል!! የሆነ ሁኖ ከዚህ የተዘበራረቀ አሳፋሪ ዜና … ሁለት ነገር ተረዳሁ … 1ኛ፡ ብሔራዊ ቴሌቪዥናችን ያልተረጋገጠ መረጃ የሚያቀርብ ግድ የለሽ ተቋም መሆኑን አውቀናል፤ 2ኛ፡ ማረሚያ ቤቶቻችን በስራቸው ላሉት ዜጎች … [Read more...] about እናንተ እውነትን የምትደባብቁ ነግ በኔ በሉ!!
ስለ ችጋር
• ችጋር ምንድን ነው? ሰፊ ቦታንና ብዙ ሕዝብን የሚሸፍን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ ምንም የሚላስ የሚቀመስ ጠፍቶ እንስሳት (ሰውንም ጨምሮ) ዕለት በዕለት የራሳቸውን አካል እስኪያልቅ ድረስ "እየበሉ" በመጨረሻም የሚሞቱበት ሁኔታ ነው፤ ረሀብ አካል ሲዳከም አካልን ለመገንባት የሚደረግ ጥሪ ነው፡፡ • ችጋር የሚያጠቃው ማንን ነው? ትልቁና ዋናው የችጋር እንቆቅልሽ የዚህ ጥያቄ መልስ ነው፤ አብዛኛውን ጊዜ ችጋር የሚያጠቃው ከገበያ ጋር የማይገናኙትን ምግብ አምራቾችን ገበሬዎችን፣ በተለይም እያመረቱ ከእጅ ወዳፍ ብቻ የሚኖሩትን ነው፤ እነዚህ ገበሬዎች የገጠሩ ሕዝብ፣ ማለትም የአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የመጨረሻ ደሀዎች ናቸው፤ ኑሮአቸው ሁልጊዜም በችጋር አፋፍ ላይ ነው፡፡ • ችጋር ከተፈጥሮ ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ነው? ከላይ እንደተባለው በችጋር ላይ የሚወድቁት ገበሬዎች ከገበያ … [Read more...] about ስለ ችጋር
“አብዮቱና ትዝታዬ” ሲያከራክር ዋለ
* ደርግ የረሸናቸው የንጉሡ ባለሥልጣናት 60 አይደርሱም ተብሏል * መፈንቅለ መንግሥቱ ቢሳካ ኖሮ ኤርትራ ከመገንጠል ትድን ነበር? * በዓሉ ግርማ መገደሉን ኮሎኔል ፍስሃ በመጽሐፋቸው ይፋ አድርገዋል በደርግ ዘመን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያገለገሉትና በመጨረሻም የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሌተናል ኮሎኔል ፍስሀ ደስታ፤ከ20 ዓመት እስር በኋላ የፃፉት “አብዮቱና ትዝታዬ” የተሰኘ መፅሐፋቸው፤ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ በሂልተን ሆቴል ሲመረቅ አብዛኛውን ታዳሚ ለክርክር ጋብዟል፡፡ ደግነቱ የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ በምረቃ ሥነ ስርዓቱ ላይ ከታደሙት አብዛኞቹ የ1960ዎቹ ትውልድ አባላት ነበሩ፡፡ የደርግ ባለሥልጣናት፣ ከፍተኛ የጦር አዛዦች እንዲሁም ከደርግ በተቃራኒ ቆመው ሲፋለሙ የነበሩ የኢህአፓ፣ መኢሶንና ሌሎች በወቅቱ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶች … [Read more...] about “አብዮቱና ትዝታዬ” ሲያከራክር ዋለ
አንድ:- ከመጠምጠም መማር ይቅደም
በፌስቡክ የምንሰባሰበው ለመወያየት፣ አንዱ ከሌላው እንዲማር፣ መረጃዎችን በነጻነት እንድንለዋወጥ፣ ይህንን ሁሉ በማድረግ ራሳችንን ለማሻሻል፣ የእኛ መሻሻል እየተራባና እየተባዛ የአገርና የሕዝብ መሻሻል እንዲሆን፣ ከተቻለንም ከአገራችንና ከሕዝባችን አልፈን የምንታይ የዓለም አካል እንድንሆን መስሎኝ ነበር፡፡ ሳየው በዚያ መንገድ ላይ ያለንና ፌስቡክን ለበጎ ዓላማ እየተጠቀምንበት ያለን አይመስለኝም፤ ስለዚህ ወይ መታረም፣ አለዚያም በፌስቡክ ጊዜ ማጥፋቱን መተው ምርጫ ሊሆንብን ነው፡፡ ምናልባት 99.99% በእኔ ሰፈር ያሉ የፌስቡክ ተሳታፊዎች ወደፌስቡክ የሚገቡት ለመናገር ነው፤ መናገር የህልውናቸው ምስክር ወይም ማረጋገጫ አድርገው የሚወስዱት ጥቂት አይደሉም፤ ካልተናገሩ የሌሉ ይመስላቸዋል፤ ዋናው ነገር መናገር ይሆንና የሚናገሩት ነገር ወይም ጉዳይ ሌላው ቀድሞ ከተናገረው ጋር የሚያያዝ … [Read more...] about አንድ:- ከመጠምጠም መማር ይቅደም










