• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ማስተር ፕላኑና ተቃውሞው

December 4, 2015 01:46 am by Editor Leave a Comment

የሰሞኑ ርህራሄ የጎደለው የመንግስት እርምጃን የሚያሳዩ ዜናዎችና ምስሎችን ማየት እጅጉን ያማል፡፡ ገዢዎቻችን የህዝብን ቅሬታ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት የሚባል ነገር ከራቃቸው ሰነባብተዋል፡፡ በውይይት ከያዙት አቋም የተመለሱበት ጊዜያት ጥቂት ቢሆንም፣ ከህዝብ ተቃውሞ ሲነሳ ተወካዮችን በማስመደብ እና ሽማግሌዎችን በመላክ ድርድሮችና ውይይቶች ይደረጉ የነበሩበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በመንግስትም ላይ ሆነ በስሩ በሚያስተዳድራቸው ተቋማት ላይ ለሚነሱ ማንኛውም አይነት ተቃውሞዎች ዘግናኝ እርምጃዎች መውሰድን እንደ ብቸኛ አማራጭ ተያይዞታል፡፡ ከሰሞኑም በአዲስ አበባው ማስተር ፕላን ዙሪያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ድረስ እየተወሰደ ያለው ዘግኛኝ እርምጃ የስርአቱን ማን አለብኝነትና የአመራሩን ጭካኔ በግልፅ የሚያሳይ ነው፡፡police

የተቃውሞው መንስኤ የሆነው የአዲስ አበባ አዲስ ማስተር ፕላን ይህን ያህል ደም ማፍሰሱና ለብዙ አካልና ንብረት መጉደል ምክንያት መሆኑ ያሳዝናል፡፡ ይህንኑ ፕላን ከአመት በፊት የትግበራ እንቅስቃሴውን በመቃወም በተነሳው ተቃውሞ በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች በተወሰደ እርምጃ የብዙ ንፁሃን ህይወት ተቀጥፏል፡፡ በማስተር ፕላኑ ስር የተካተተው የኦሮሚያ አጎራባች ከተሞችን በአዲስ አበባ ስር የማካተት እቅድና በቦታው ላይ ሰፍሮ የሚገኘው ህዝብ እጣ ፈንታ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል፡፡ እንደዚህ አይነት እቅድ ህገ መንግስቱ ያፀደቀውን የፌደራሊዝምን መርህ ጥያቄ ውስጥ ከማስገባቱም በላይ ሀገሪቱ የምትከተለው የከተማ ልማት ፖሊሲ ግድፈቶች ማሳያም ጭምር ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ የፖሊሲ ግድፈቶቹንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአጭሩ ለመቃኘት ተሞክሯል፡፡

ያልተመጣጠነ የከተማዎች እድገት

አዲስ አበባ የሃገሪቱ ዋና ከተማ እና የትላልቅ አለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ እንደመሆኗ ከሌሎች ከተሞች በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴም ይሁን በአገልግሎት አቅርቦቷ የተሻለች እንደምትሆን ቢጠበቅም አሁን እንደሚስተዋለው ከሌሎች ከተሞች አንፃር የተጋነነ ልዩነት መኖሩ የሃገሪቱን የከተማ ልማት ፖሊሲ ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል፡፡ ኢትዮጵያ ማለት አዲስ አበባ ማለት እስኪመስል ድረስ (ምናልባትም ከተወሰኑ የቱሪስት ከተማዎች ውጪ) የመንግስትም የህዝብም ንብረት፣ እውቀትና ገንዘብ አዲስ አበባ ላይ እየፈሰሰ ይታያል፡፡ ከሌሎች ከተሞች ጋር ያላት ልዩነትም እያደር በተጋነነ መልኩ እየሰፋ ይገኛል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አዲስ አበባ እጅግ የተጨናነቀች ከተማ ሆናለች፡፡ የከተማዋ ኢንፍራስትራክቸር መሸከም ከሚችለው በላይ ህዝብ እያስተናገደ እንደሆነ የትራንስፖርት፣ የገበያ፣ የጤና ተቋማት በመሳሰሉ የህብረተሰብ አገልግሎቶች መስጫ ቦታዎች ላይ የሚስተዋለውን ከመጠን ያለፈ ትርምስ እንደምሳሌ መውሰድ ይቻላል፡፡ ይሁንና የተሻለ የስራ እድል፣ የተሻለ አገልግሎቶች እና የተሻለ ብሩህ ተስፋ ይኖራል ተብሎ እስከታሰበ ድረስ ወደ አዲስ አበባ የሚደረገው ስደትም፣ ትርምስና መጨናነቁም ይቀጥላል፡፡

addis_oromia_sp_zoneአንድ ሀገር እድገትን ማስመዝገብ ሲጀምር ከተማዎች ላይ የሚኖረው የህዝብ ቁጥር እየጨመረ ይመጣል፡፡ ስለዚህም የከተማዎች ማደግና መስፋፋት የአንድ ህዝብና ሀገር ተፈጥሮአዊ ሂደት ይሆናሉ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ግን ሚዛናዊ የሆነ የከተማ እድገት ፖሊሲ እስካልተከተልን ድረስ በተለይ እንደኛ ፌደራላዊ ስርአትን እከተላለሁ በምትል ሀገር ላይ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮችን መፍጠሩ አይቀሬ ነው፡፡ አሁን የተከሰተው ተቃውሞም የዚህ ማሳያ ነው፡፡ ሌሎች ተወዳዳሪና አማራጭ ከተሞች እንዲመሰረቱ እና እንዲያብቡ፣ ላሉትም በቂ ድጋፍና ማበረታቻዎችን በማድረግ ማሳደግ እስካልተቻለ ድረስ ያልተመጣጠነ የከተማዎች እድገት በተወሰኑት ላይ ጫና በመፍጠር የቀውስ መንስኤ ከመሆን አይወገድም፡፡ መሪዎቻችን የአዲስ አበባ መስፋት የእድገታችን ትሩፋት መሆኑን ሲነግሩን ያልተመጣጠነ የከተማዎች እድገት ያስከተለው ፖሊሲያቸው ደግሞ ሀገሪቱ በታቀደ እና በተጠና መንገድ እየሄደች እንዳልሆነ እንደሚያሳብቅባቸው ልንነግራቸው ይገባል፡፡

ህዝብን ያላማከለ ከተሜነት

አንድ ገጠራማ የሆነ አካባቢ ወደ ከተማነት ለመቀየር የቦታው ባለቤት የሆኑትን ገበሬዎችንና የመሬት ባለቤቶችን ማፈናቀሉ አይቀሬ ነው፡፡ አዲሱ ማስተር ፕላንም በአዲስ አበባ አካባቢ ያሉ የኦሮሚያ ክልሎችን በስሩ ለማካተት ሲያቅድ ተመሳሳይ ነገር እንዲተገብር ይገደዳል፡፡ ሀብት ንብረቱን የሚያጣው የአካባቢው ነዋሪ በቂ ካሳ ሳይከፈለው ሲቀር ከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገባል፡፡ በግብርና ለብዙ ትውልድ ሲተዳደር ለነበረ የህብረተሰብ ክፍል የንብረቱን ተመጣጣኝ የገንዘብ ካሳ ቢሰጠውም እንኳን ህይወቱን ሊለውጥ ይቅርና ባለበት ለማስቀጠል የሚያስችል ከግብርና ውጪ የስራ ክህሎት ይኖረዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይህም ከተሜነቱ ሀብት ንብረቱን በማሳጣት የኑሮ ደረጃውን ወደታች የማሽቆልቆሉ እድል ሰፊ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህም አይደለም እንደኛ ሀገር በቂ የንብረት ካሳ በማይሰጥበት ሀገር ይቅርና በቂ ካሳ ቢሰጥም እንኳን የገበሬውን ህይወት በነበረበት ለማስቀጠል ተጨማሪ መንግስታዊ ድጋፎችን ይሻል፡፡

ለዚህ አዋጭ የሆነው አማራጭ ካሳን በአግባብ ከመክፈል ባለፈ ህብረተሰቡ ሊደረግ በሚታቀደው ልማት ቀጥተኛ ተጠቃሚ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ የለውጡ መሪም፣ ተግባሪም፣ ተጠቃሚም መንግስትና በአካባቢው ያሉ አጃቢዎቹ ሲሆኑ ህብረተሰቡ የሚሰራው ልማት ለእሱ ጥፋት እንደሆነ ቢሰማው ተወቃሽ አይሆንም፡፡ የከተማዎች ግንባታ እንደሚታየው በወረራና በጅምላ በማፈናቀል ሳይሆን ከካሳ ክፍያው በተጨማሪ ህብረተሰቡን ጊዜ ሰጥቶና እድሎችን አመቻችቶ የመተዳደሪያ ምንጩን ከግብርና ወደ ሌላ አማራጮች እንዲቀይር በትምህርት፣ በስልጠና እና በፖሊሲ በመደገፍም መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ሲሆን የከተሜነቱን ሂደት ቀድሞ የነበረውን ነዋሪ ያካተተ በማድረግ ጤናማ የሆነን ኢኮኖሚና ማህበረሰብን ለመገንባት ያግዛል፡፡

ህገ-መንግስታዊ እክል

ሀገራችን በፌደራላዊ ስርአት በተግባርም ባይሆን መተዳደር ከጀመረች ሃያ አምስት አመት ሊሞላት ነው፡፡ ፌደራላዊ ስርአት ሲባል የተለያዩ ራስ ገዝ የሆኑ አስተዳደሮች/ክልሎች በበጎ ፈቃድ አንድ ላይ ብንሆን የተሻልን እንሆናለን ብለው በማመን በጋራ ስምምነት ላይ የተመሰረተ የራስ ገዝ ግዛቶች ስብስብ ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ባለው ህገ መንግስት ደግሞ ከብዙ ሀገራት በተለየ መልኩ የመገንጠልን ነፃነት መጨመሩ ክልሎችን የራስ ገዝ ደረጃ ከፍ ያደርገዋል፡፡ በክልሎች መካከልም ያለው ወሰን በሀገራት መካከል እንዳለ ወሰን ጠንካራ ያደርገዋል፡፡ በዚህ አግባብ ውስጥ የአዲስ አበባ አስተዳደርን የኦሮሚያ አዋሳኝ ከተሞችን በስሩ ለማካተት ማሰቡ በመርህ ደረጃ የሌለ ሀገርን ግዛቶች ከመውረር ጋር ተመሳሳይ ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ አይደለም ገበሬዎችን ከይዞታቸው ያፈናቅላል፣ ገንዘብ ንብረት አልባ አድርጎ ወደ ድህነት ይወረውራቸዋል፣ በቂ ካሳ አይሰጣቸውም የሚሉ ክርክሮች የፕላኑ አተገባበር ፍትሃዊ በማድረግ ሊቀረፉ ይችላሉ፡፡ ከላይ የተጠቀሰው ህገ-መንግስታዊ እክል ግን በመርህ ደረጃ አዲስ አበባ እንደዚህ አይነት እቅድም ማውጣት እንደማትችል ያሳየናል፡፡Wallaggaa

የመፍትሄ አቅጣጫ

አዲስ አበባ ታቅዶም ይሆን ሳይታቀድ እያደገችና እየሰፋች ያለች ከተማ መሆኗ ግልፅ ነው፡፡ የከተማዋ አጎራባች ከተሞችም ከከተማዋ ተርፎ እየፈሰሰ ያለው ከተሜነት በከፍተኛ ፍጥነት እየወረራቸው ይገኛል፡፡ ይህንን መስፋፋት መስመር በያዘና በታቀደ መልኩ እንዲፈስ ማድረጉ አስፈላጊነቱ አያጠራጥርም፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ግን ያለው የአገሪቱ ፌደራላዊ አወቃቀርና ከዚህ በፊት የነበሩ የተመሳሳይ እቅዶች አፈፃፀም የነበራቸው መጥፎ አሻራዎች ከፍተኛ እክል ሆኖበት ይገኛል፡፡ በሀገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ የተቀሰቀሰውም ተቃውሞ በትክክልም ህገ መንግሥታዊ እና ሞራላዊ መሰረት እንዳለው ከዚህ አንፃር በግልፅ ማየት ይቻላል፡፡ የእንደዚህ አይነት ሁለት ፌደራላዊ ግዛቶችን የሚያካትት እቅድ በሁለቱ ከተሞች ህዝቦችና አስተዳደሮቻቸው ስምምነት እና ትብብር መተግበራቸው የግድ ይላል፡፡

ሁለቱ ክልሎች ተባብረውና ተናበው እስከሰሩ ድረስ የአዲስ አበባ አጎራባች ከተሞች የግድ አዲስ አበባ ውስጥ መካተት አለባቸው ማለት ህገ መንግስታዊ ድንጋጌዎችን ከመናዱም በላይ አላስፈላጊ ግትርነት ነው፡፡ የአካባቢዎቹን ልማት በኦሮሚያ ውስጥ ማድረጉ የሀገሪቱን የከተማዎች ስብጥር የተሻለ እንዲሆን የሚያደርገው ሲሆን አተገባበርም ላይ ህገ መንግስታዊ ድንጋጌን እንዳይጥስ ያደርገዋል፡፡ ከተሜነቱን ተከትሎ የሚገኘውም ገቢ በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ በክልሉ ውስጥ ለሌላ ልማታዊ ስራዎች ጥሩ የገቢ ምንጭ ይሆናል፡፡ ከዚህ መሰረታዊ ለውጥ በተጨማሪ በከተማ መስፋፋቱ ለሚፈናቀሉ ገበሬዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች በቂ ጊዜ በመስጠት ህይወታቸው መስተጓገል ሳይደርስበት ወደ አዲሱ ህይወት እንዲሸጋገሩ ማገዙ ግድ ይላል፡፡ ልማት ህግን አክብሮ እና ህዝብን ተጠቃሚ አድርጎ ሲመሰረት ዘላቂነቱም ቅቡልነቱም ሰፊ ይሆናል፡፡

በአብዱረዛቅ ሑሴን (የፌስቡክ ወዳጃችን ይታተም ዘንድ የላኩልን ነው)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule