On 9, Aug, 2014 a white police man allegedly shot an unarmed African American teenager, Michael Brown, 18, in Ferguson Missouri, USA. Ever since Washington seemed unable to restore calm and tension in the city. However if the USA had invited Special Forces of the current Ethiopian government, the whole public chaos and mob would have been quelled in a matter of hours. For more than the past 23 years the Ethiopian government (EPDRF) has been diligently working in producing Special Forces who … [Read more...] about Ethiopian Special Forces can quell the unrest in Ferguson.
Opinions
የኔ ሃሳብ
የብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ
ስለ ብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ አጠር ምጥን ተደርጎ የተዘጋጀውን ባለ አምስት ነጥብ የዳሰሳ ጥናት (survey) ለዚሁ ጉዳይ ሲባል ብቻ ወደ ተዘጋጀው ድህረገፅ እዚህ ላይ በመጫን በመሄድ ድምፅዎን ያሰሙ። የዝምተኛው ብዙሃን ድምፅ ጭምር ሳይቀር እስቲ ይሰማ! ፖለቲካውንና ፍልስፍናውን አርባ አመት አውጠንጥነን አረጀንበት። እንዲሁ ስንባዝን እድሜያችን አልቆ አንድ ባንድ ወደ ሞት ልንሄድ ነው። እርቅና መግባባትን ማን ጠላ? መላው ጠፍቶብን እንጂ። አይ መላውም አልጠፋን እንደ እውነቱ ከሆነ። ኢትዮጵያ መፍትሔ ሊያመጡ የማይሳናቸውን ልጆች ወልዳ ሳለ እንደ መካን ቁጭ ብላ መቆዘም አይገባትም። እስቲ የልበ ሰፊው፦ የአስተዋዩና የጨዋው ሕዝብ ድምፅ እንስማው። ባለስልጣኑ በራሱ ጡንቻ ተማምኖ ተቃዋሚውን ከመንጫጫት በላይ ምን ያመጣል ብሎ ሲንቅ፦ ተቃዋሚው ምንም ይሁን ምን ባለስልጣኑ … [Read more...] about የብሔራዊ እርቅና መግባባት ጉዳይ
The perils of outsourcing the fight for freedom
I could have titled this piece ‘Obama and his Africa peace keepers’ but that would not be fair. Anybody with half a brain can see that I am trying to make my issue to be his problem. Excuse me just because fighting for my right is beneath my dignity there is no reason to impose on him that I am unable to do for whatever reason. Dear Mr. President we Africans are not amused! This is what appeared on The Guardian ‘According to President Obama, who announced a series of American support and … [Read more...] about The perils of outsourcing the fight for freedom
ኢትዮጵያዊነት ማለት ክፍል ፩
“ ኢትዮጵያዊነት ማለት፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ፣ ኢትዮጵያን ማፍቀር፤ የኢትዮጵያን መንግሥት በተገቢው መንገድ መደገፍና፤ ይህ መንግሥት የተሳሳተ መንገድ ሲይዝ መቃወም ማለት ነው። በሥልጣን ላይ ያለው ክፍል ፀረ-ኢትዮጵያዊያንና ፀረ-ኢትዮጵያ ሲሆን፤ ያንን ክፍል በማንኛውም መንገድ ማስወገድ፤ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊና የያንዳንዷ ኢትዮጵያዊት፤ ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። ” አብዛኛዎቻችን በየጊዜው የምናነሳው ጉዳይ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ ሀቅና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ነው። ኢትዮጵያዊ ነኝ ወይንም አይደለሁም የሚለውን ጥያቄ አይደለም። በየቦታው፣ በተገኘው አጋጣሚ፣ በየዕለቱ በሕዝቡ ላይ የሚደረገውን በደል እናውጠነጥናለን። ኢትዮጵያዊያን ናቸው ወይንም አይደሉም የሚለው ከጥያቄያችን መካከል አይደለም። መቼም አርባ ዓመት ሙሉ፤ በአረመኔው መንግሥቱ … [Read more...] about ኢትዮጵያዊነት ማለት ክፍል ፩
የዘንዶ ሱባዔ?
መግቢያ ሱባዔ፦ በሰው፤ በቦታና በሰአት ስለሚከናወን የሶስቱም ማለትም የሰአት፤ የሰባዊነትና የመካን ድምር ነው። ሱባዔ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥልቅ፤ ረቂቅና ምጡቅ ግንዛቤ አለው። በመንፈሳችንና በሥጋችን መካከል ያለውን ሚዛን አለመሰበሩንና አለማጋደሉን፤ በፈጣሪያችንና በራሳችን መካከል፤ በህዝባችንና በራሳችን መካከል ያለንን ግንኙነት የምንፈትሽበት ነው። በሩቅና በቅርብ ያለውን አካባቢያችንን ማየት የምንችልበት ተራራ ነው። ውስጣዊ ህሊናችንን የምናይበት ረቂቅ መስታወት ነው። የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ የሚያሳየን፤ እመቀ እመቃት፡ አየረ አየራት፡ ያሉትን ሁሉ ፍጥረታት የምንፈትሽበት ተራዛሚ መነጽር ነው። ሱባዔ፦ በሰው ብቻ የተወሰነ አይደለም። በደማቸው ሞቃትነትና ቀዝቃዛነት የሚለያዩ ፍጥረታት በየደረጃቸው ሱባዔ ይገባሉ። የፍጥረታትን ቅደም ተከተል በመጠበቅ … [Read more...] about የዘንዶ ሱባዔ?
በዓሉን የበላው ደርግ “አይደለም”፣ የሰው ጅብ ነው!
እውኑን ቀርቶ ምስሉንም እንኳን አይቸው የማላውቀው[1] በዓሉ ግርማን አውቀዋለሁ። ህይወትን እና ሰውን የሚወደውን፣ ውብ ሰብዕና ያለውን በዓሉ ግርማን አውቀዋለሁ። በዓሉን፣ ሰብዓዊ እና ሞራላዊ ማንነቱን በጽሁፎቹ ውስጥ አይቻለሁ። በዓሉን አውቀዋለሁ። እናት አባት አያት፣ ቅማያት እና ቅንዝላቶቼ ሁሉ መጣፍ ቅዱስ ዳዊቱን፣ ቁራን ኪታቡን በነጋ በመሸ ቁጥር እየደገሙ እና እያነበቡ የኖሩትን ያህል፣ እኔ ደግሞ በዓሉን አንብቤያለሁ። በተለይ ኦሮማይን፣ ቢያንስ ከእጄ ከገባበት (ከ1978 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ) ምናልባትም ከሶስት እና አራት ጊዜ በላይ ደጋግሜ ሙሉውን ያነበብኩትን ያህል፣ ለአምስት ወይም ስድስት አመት አካባቢ ደግሞ፣ ጧት ጧት ከእንቅልፌ ነቅቼ ከምኝታዬ በተነሳሁ እና ቤት ውስጥ በገባሁ በወጣሁ ቁጥር እንደሥሥት ልጅ ደጋግሜ እያነሳሁ በየቀኑ፣ ከጄ የገባውን አንድ ሁለት ገጽ … [Read more...] about በዓሉን የበላው ደርግ “አይደለም”፣ የሰው ጅብ ነው!
ከላይ ሆነን ስናይ
በቅርቡ የኣሜሪካ ፌደራል ኣቪየሽን ኣስተዳደር (FAA) በዓለም ላይ ለበረራ ኣደገኛ የሆኑትን መስመሮች በካርታው ላይ ከቦ ኣስጠንቅቆ የነበረ ሲሆን በሪፖርቱ ላይ እንደሚታየው እነዚህን ኣደገኛ ቦታዎች በሁለት ከፍሏቸዋል። ኣንደኛው መስመር ኣደገኛነት ያለው ክልል (potentially hostile region) ሲሆን ሁለተኛው ክልል ግን በረራን ጨርሶ የከለከለ(Flight prohibited) ክልል ነው። ኣደገኛነት ኣላቸው ተብለው ኣብራሪዎች ከግምት እንዲያስገቡ የተመከሩባቸው ክልሎች ኬንያ፣ ኣፍጋኒስታን፣ ኢራን፣ ሶሪያ፣ ማሊ፣ የመን፣ ኮንጎና ግብጽ ሲናይ ናቸው። የበረራ መስመር የተከለከለባቸው ኣካባቢዎች ደግሞ ዩክሬን ውስጥ ድኒፕሮፐትሮቭስክ (ይህ ኣካባቢ በሶቪየት ዮኒየን ጊዜ የኒውክሌር ማምረቻ ተቋም የነበረበትና በኣሁኑ ሰዓት ደግሞ በራሽያ የሚደገፉ ገንጣዮች የሚንቀሳቀሱበት ክልል … [Read more...] about ከላይ ሆነን ስናይ
የሴት ልጅ ግርዛት ጎጂ ወይስ ጠቃሚ?
ጥናታዊ ጽሑፍ! በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ አንዳች ጥናት ቢጤ ማድረጌን አምና በግብረ ሰዶማዊያን ጉዳይ ላይ በጻፍኩት ጽሑፍ ሳይቸግረኝ ጠቆም በማድረጌ ብዙኃን መገናኛዎችን የሚከታተሉ ሰዎች በኢሜይልና በስልክ በአካልም ጭምር በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያዘጋጀሁትን ጥናታዊ ጽሑፍ ለንባብ እንዳበቃላቸው እጅግ ወተወቱኝ፤ አይ ረጅም ነው ለመጽሐፍ እንጅ ለዚህ ዓይነት መስተንግዶ አይሆንም ረዘመ ትላላቹህ ብልም ሊቀበሉኝ አልቻሉም ጨቀጨቁኝ እንግዲህ ካልተውኝ ምን አደርጋለሁ ብየ አቀራረቡን ግን ለብዙኃን መገናኛ በሚሆን ቀየርኩትና ተዛማጅ የሆነ ጠቃሚና አስፈላጊ ጉጋይ አክየበት ጽፌላቹሀለሁ ያውላቹህ፡- ይሄንን ጥናት ያደረኩት ከስድስትና ከሰባት ዓመታት በፊት ነበር፡፡ በዚህ ጥናት ከ800 ያላነሱ ሰዎች በቀጥታ በሽዎች የሚቆጠሩ በተዘዋዋሪ የጥናቴ ግብአት በማድረግ ተጠቅሜያለሁ፡፡ ጥናቴን … [Read more...] about የሴት ልጅ ግርዛት ጎጂ ወይስ ጠቃሚ?
የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
አገራችን ኢትዮጵያ በጥሩ ልትጠራባቸው የምትችላቸው ጉዳዮች እንዳሉ ሆነው በድህነት በሰብዓዊመብት አያያዝ፣ በሙስና እና ሃሳብን ነጻነት በመግለጽ መብት የተለመዱ የምናፍርባቸው ጉዳዩች ሆነው መቀጠላቸው እሙን ነው፡፡ ሃሰብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ ሶስት ወራትን ከፈጀ ምርመራ በኋላ በብዙ የፓሊስ ድብብቆሽ ሂደት የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ላይ ባለፈው አርብ ክስ መመስረቱም አብሮ ይታወሳል፡፡ ጓደኞቻችን ከታሰሩ ጊዜ ጀምሮ መንግሰት ያቀረበውን ውንጀላ አስመልክቶ በተለያየ ወቅት ሃሳባችንን ለመግለጽ አስበን ምናልባት የምንሰጠው ሃሳብ አሁንም በመንግሰት እጅ የሚገኙት ጓደኞቻችን ላይ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ በመፍራት እነዲሁም ለመንግሰት እድሉን በመስጠት ኦፌሻል ክሱን እስክናይ ድረስ በጠቅላላ ሃሳቦች ላይ አስተያየት ከመስጠት ውጨ ብዙም ሳንል ቆይተናል፡፡ አሁን ግን ክሱ አንድ … [Read more...] about የዞን ዘጠኝ ጦማርያንና ጋዜጠኞችን ክስ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
“ፋክት መጽሔት”
ከሁለት ሳምንታት በፊት በ9-11-2006ዓ.ም. አንድ የፋክት መጽሔት ደንበኛ የሰፈር ሰው አንድ ጸሐፊ በፋክት መጽሔት ላይ አንድ ጽሑፌን መነሻ አድርጎ ያልኩትንም ያላልኩትንም እየቀላቀለ አብጠልጥሎኝ ኖሮ ይሄ ቁጭት ፈጥሮባቸው ስለነበር ባገኙኝ ጊዜ “ባይ ባይ ምንም የለም ለምንድን ነው መልስ የማትሰጠው?” ሲሉ ጠየቁኝ፡፡ ለማን? ስል መለስኩላቸው ፋክት መጽሔት ላይ ስምህን ላጠፋው ሰው ነዋ! አሉኝ፤ ማን ነው ስሜን ያጠፋው? ስላቸው እንዴ! አላየኸውም ማለት ነው? አንዱ እኮ ጻፈብህ አሉኝና ወደ ቤታቸው ገብተው መጽሔቱን ይዘው መጡ ያሉትን ጽሑፍ አነበብኩት ልክ ወያኔ ዜጎችን “የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ” እያለ እንደሚያሸማቅቀው ሁሉ ይሄም ሰው እኔን “ባረጀውና ባፈጀው መንገድ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሚታገል ሰው፣ የብሔረሰቦችን እኩልነት የማይቀበል” ምንትስ እያለ እንደ ወያኔ በፈጠራ ክስ … [Read more...] about “ፋክት መጽሔት”










