መግቢያ
ሱባዔ፦ በሰው፤ በቦታና በሰአት ስለሚከናወን የሶስቱም ማለትም የሰአት፤ የሰባዊነትና የመካን ድምር ነው። ሱባዔ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥልቅ፤ ረቂቅና ምጡቅ ግንዛቤ አለው። በመንፈሳችንና በሥጋችን መካከል ያለውን ሚዛን አለመሰበሩንና አለማጋደሉን፤ በፈጣሪያችንና በራሳችን መካከል፤ በህዝባችንና በራሳችን መካከል ያለንን ግንኙነት የምንፈትሽበት ነው። በሩቅና በቅርብ ያለውን አካባቢያችንን ማየት የምንችልበት ተራራ ነው። ውስጣዊ ህሊናችንን የምናይበት ረቂቅ መስታወት ነው። የራቀውን አቅርቦ የረቀቀውን አጉልቶ የሚያሳየን፤ እመቀ እመቃት፡ አየረ አየራት፡ ያሉትን ሁሉ ፍጥረታት የምንፈትሽበት ተራዛሚ መነጽር ነው።
ሱባዔ፦ በሰው ብቻ የተወሰነ አይደለም። በደማቸው ሞቃትነትና ቀዝቃዛነት የሚለያዩ ፍጥረታት በየደረጃቸው ሱባዔ ይገባሉ። የፍጥረታትን ቅደም ተከተል በመጠበቅ የደመ ሞቃት እንስሳትንና፤ የዘንዶን ሱባዔ ከዳሰሰን በኌላ፤ የዘመናችን በተለይም የመነኮሳት ሱባኤ ከጥንታዊት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሱባዔ ተቀይሮ፤ ከደመ ሞቃት እንስሳት ምን ያህል እንደራቀና ወደ ዘንዶ ሱባዔ እንደተቀረ በማነጻጸር፤ ይህ የዘንዶ አይነት ሡባዔ የማይታረም ባለበት የሚቀጥል ከሆነ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ሁሉ ወንዱም ሴቱም በተለይ ትዳር ያፈረሰ በዝሙት በሌብነት በዘራፊነት የተከሰሰ ሁሉ ቆቡን እያጠለቀ፤ ምንኩስና ቁምስና ወደ ተላበሰ ቅስናና ሊቀ ጳጳስና እኛም እንግባ ብሎ መነሳቱ መፍትሄው ይመስለኛል። ሁሉንም አይተን ከምዳሜ ለመድረስ ከደመ ሞቃት እንስሳት ሱባዔ እጀምራለሁ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)
Leave a Reply