• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት

August 4, 2014 11:44 pm by Editor 2 Comments

ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል።

“በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል።

ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው በማለት ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሣደር የነበሩትና የጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ዴቪድ ሺን መናገራቸውን ያሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ዘግቦ ነበር፡፡

ከሱዳኑ ፕሬዚዳንት በስተቀር ያልተጋበዙት መሪዎች አለመጋበዝ ትክክለኛ ውሣኔ ነው ብለው እንደማያስቡም ተናግረዋል – አምባሳደር ሺን፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የመጭው ሣምንት የአፍሪካ መሪዎች የዋሺንግተን ጉባዔ ይህንን ጉባዔ የረጥነው ከአፍሪካ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሳደግ መወሰናችንን መልዕክት ለማስተላለፍ ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የሥልታዊ ግንኙቶች የብሄራዊ ፀጥታ ምክትል አማካሪ ቤን ሮድስ ተናግረዋል፡፡

ሚስተር ሮድስ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ-ግሪንፊልድ እና የዩናይትድ ስቴትስ የብሔራዊ ፀጥታ ምክር ቤት የልማትና የዴሞክራሲ ከፍተኛ ዳይሬክተር ጌል ስሚዝ ጉባዔውን አስመልክቶ ከትናንት በስተያ ምሽት ላይ ከጋዜጠኞች ጋር ባካሄዱት የአንድ ሰዓት የስልክ ቃለ-ምልልስ የመጭውን ሣምንት ጉባዔ ይዘትና አካሄድ አብራርተዋል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉን በተመለከተ በድምጽ የተጠናቀረውን ለማዳመጥ እዚህ  ወይም እዚህኛው ላይ ይጫኑ::

(ምንጭ: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ)

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Kiros says

    August 6, 2014 06:05 pm at 6:05 pm

    Here is funny. Thanks
    http://erecycler.wordpress.com/2014/08/06/africas-big-men-2/

    Reply
  2. Addisu Abebe says

    August 15, 2014 12:50 pm at 12:50 pm

    16/12/2006
    ሰላም አንዴት ናችሁ፡፡ ሰሞኑን በተለያዩ የነጻው ፕሬስ ሚዲያዎች ላይ የተከፈተው ዘመቻ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ የአዲስ ጉዳይ እና የፋክት መጽኄት ባለቤቶች፣ ጋዜጠኞች እና አምደኞ ላይ የሚደርሰው ወከባ ማስፈራሪያና ዛቻ በመብዛቱ የተወሰኑት አገር ጥለው መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ሰሞኑን በተሰማ ዜና በአዲስ ጉዳይ መጽሄት ላይ በክሪኤቲቭ ራይቲን የሚታወቀው ሐብታሙ ስዩም እና ታሪክ በሰሞነኛ ጉዳይ አምድ አቅራቢ ሳሙኤል አሰፋ እና ሌሎች ምደኞች ካልታወቁ ሰዎች ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰን ነው በሚል አገር ጥለው መሄዳቸው እየተወራ ነው፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
Copyright © 2026 · Goolgule