• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጅዳ ቆንስል ሃላፊ ዘነበ ከበደ ከኃላፊነታቸው ተነሱ!

February 12, 2014 05:48 am by Editor 1 Comment

* ትናንት ረፋዱ ላይ በገደምዳሜ  “ጉልቻ ቢቀያየር …” ብለን ያንሹካሾክነው መረጃ ተረጋገጠ!

* ለጊዜው ቆንስል ጀኔራሉን ተክተው በጊዜያዊነት ቆንስል መስሪያ ቤቱን ለቀጣይ ሁለት ወራት የሚያስተዳድሩት በቆራጥ አመራራር ብቃታቸው የማይመሰገኑት ቆንስል ሸሪፍ  ከይሩ ናቸውም ተብሏል።

* ቆንስል ጀኔራል አቶ ዘነበ ከበደ ትናንት ምሽት ጉዳዩን ለማሳወቅ የኢህአዴግ ድርጅት  አባላት ስብሰባ ጠርተው እንደነበርና አብዛኛው አለመገኘታቸው ታውቋል። ድርጅት አባላት በተለይም ከጎናቸው የማይጠፉ የነበሩት ተጽዕኖ ፈጣሪ የህወሃት አባላት እንኳ አልተገኙም ተብሏል።

አቶ ዘነበ ከበደ በቆንስሉ ዙሪያ የህወሃት አባላትን አምባገነንነትን በማውረድና በማቀዝቀዝ፣ በሙስና፣ በድለላ፣ በማጭበርበር ስራ በቆንስሉ ዙሪያ የነበሩትን በማጥፋት እና በሌብነት አካባቢውን በማጽዳት ይታወቃሉ።

ህግ አዋቂ ሆነው በህግ ማዕቀፍ የመጡ ዜጎች ግፍ ሲፈጸምባቸው በመከላከሉ የረባ ስራ አልሰሩም የምላች  ሃላፊው ስልጣን ከተረከቡ ወዲህ ሶስት ከባባድ የህዝብ ማዕበል የተነሳባቸውን ፈተናዎች በጽናትና በቆራጥ አመራራቸው ድል ነስተው ማለፋቸውን አውቃለሁ።  ሃላፊው በአንጻሩ በመረጃ ልውውጥ የማያምኑ ፍትሃዊ በመሆኑ ሳይሆን በግላቸው ላመኑበት ጉዳይ ግንባራቸውን የሚሰጡ ኋላፊ ነበሩ።

አቶ ዘነበ ከበደ  በሳውዲ ከፍተኛ ሃላፊዎች ዘንድ ክብር የሚሰጣቸው በአማርኛም ሲናገሩ ወጋቸውን ለማስረዳት ተረት የሚያበዙ፣ ከዚህ በፊት ከነበሩት ኃላፊዎች እንግሊዝኛ አቀላጥፈው የሚናገሩ  አንደበተ ርቱዕ ግርማ ሞገስ ያላቸው፣ በአለባበሳቸው ጸዳ ያሉ ትክክለኛ የአንድ ሃገር ዲፕሎማት ክብርን የተጎናጸፉ ኃላፊ ነበሩ።

ከግማሽ ሚሊዮን የማያንሱ ኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች ባለፉት ሶስትና አራት አመታት የገቡ ሲሆነ ኮንትራት ሰራተኞች ስለመጡበት ውል አቶ ዘነበ በጀርመን ራዲዮ ውይይት ፕሮግራም ተጠይቀው በኢትዮጵያና በሳውዲ በመንግስት መካከል የሁለትዮሽ የስራተኛ ልውውጥ ስምምነት አንደሌለ በግላጭ የነገሩን ኀላፊም ናቸው።

አቶ ዘነበ ከበደ ከዚህ በፊት በቆንስሉ ውስጥ የነበረውን የበከተ ቢሮክራሲና ኢ ፍትሃዊ አመራር በአደባባይ የተናገሩ ደፋርም ናቸው። ነዋሪው በግዳጅ ምንም የገንዘብ መዋጮ ሲጠይቁ ያልተሰሙ፣ ኮሚኒቲው ያልሆነ ምንገድ ሲሄድ እንደ በላይ ጠባቂነት ኢ ፍትሃዊ አካሔዱን እያዩ ሲያልፉም ታይተዋል። ለዚህ ተጠቃሹ ትምህርት ቤቱ በኮሚኒቲው ለከፋ አደጋ ሲዎድቅ የተመለከቱበት አካሔድ ሲሆን በመጨረሻው ሰአት ገብተው 120 ሽህ የሳውዲ ሪያል ከዝርፊያ አዳንኩ ብለው ቢነግሩንም  ዛሬ ድረስ የ3000 ታዳጊዎችና የ200 መምህራንና ሰራተኞች ያቀፈው መመኪያችን በጅዳ የኢትዮጵያውያን አለም አቀፍ ትምህርት ቤቱን ከአደጋ አላወጡትም። ያም ሆኖ ለትምህርት ቤቱ የተዝረከረከ አሰራር ምክንያትየየተባሉ አንዳንድ መሰረታዊ ለውጦችን ግን በቅርብ ተንቀሳቅሰው አምጥተዋል!

አቶ ዘነበ ከበደ እንደርሳቸው ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ እንደ እርሳቸው ከስልጣን የተነሱትን አምባሳደር መርዋንን እና 12 አመት የጅዳን ቆንስል አንቀጥቅጠው የመሩት  የህወሃት ከፍተኛ ሰው አምባሳደር ተክለ አብ ከበደን አስተዳደር ብልሹ አካሔድ  ብቻ ሳይሆን የቆንስሉን ሰራተኞች በአደባባይ መመንቀፋቸው በኢህአዴግ የድርጅት አባላትና በሰራተኞች ዘንድ የተፈሩ ሲያደርጋቸው ለዛሬ ከስልጣናቸው መነሳትም የህወሃት አባላት ተጽዕኖ እንዳለበት ራሳቸው ህወሃቶች እየነገሩን ነው። ትናንት አንባሳደር መርዋንን ከስልጣን በማስነሳቱ ረዥም እጅ የነበራቸው ህዎሃትን ጨምሮ የተቀሩት የኢህአዲግ አባል ድርጅቶች ዛሬም በውጭ ጉዳ ከፍተኛ ሃላፊዎች ተጽዕኖ ፈጣሪነት በገሃድ ማሳያው ቀድምው የነገሩን እየደረሰ ማየት መጀመራችን ነው !  ዛሬም ማን ሊመጣ የሚችለው ሃላፊ የዲፕሎማሲያዊ እና የአስተዳደር ብቃት ሳይሆን አነጣጥሮ ተኳሽነቱና የዋለበትን የጦር አውድማ ድረስ በአድናቆት የህወሃት ካድሬዎች  ይነግሩን  ጀምረዋል።

ጉልቻ ቢቀያየር …

ከረፋድ እስከ ቀትር (ትናንት  ማክሰኞ መሆኑ ነው) አንዱ መረጃ ከተለያየ አቅጣጫ እዚህም እዚያም ደረሰኝ፣ በሹክሹክታ ስሰማው የሰነበትኩትን መረጃ እውነትነት ለማረጋገጥ ቢገደኝም የጭምጭምታውን አንድምታ ለማጣራት መሞከሬ አልቀረም። ብዙ ጣርኩ ግን ከመንግስት የቀረቡት ምንጮቸ እያወቁ “አናውቅም” ያሉኝ! ወደው ሳይሆን የእንጀራ ነገር ሆኖባቸው እንጅ አዲስ ነገር እንዳለ በከባቢው የሚታየው ድባብ ያሳብቃል … ይህን እያሰብኩ እያለሁ አንድ የማለዳ ወግ ርዕስ ከአፊ ገባ “ሳያልቅ የተጠናቀቀው ዘመቻና አልረጋ ያለው የጅዳ ቆንስል ወንበር …” ብየ ጀመርኩት … መቀጠል ግን አልቻልኩም!

በሰሞነኛው በባጀንበት የሳውዲ ኢትዮጵያውያን ክራሞት ዙሪያ የወገን እንግልት የሚያማቸው ወንድም አሉኝ። እኒሁ ከወደ ጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሁሌም መረጃ የሚያጋሩኝን ወዳጀን “ሹም ሽር ይደረጋል!” ተበሎ ሰምተው ያልተረጋገጠውን መረጃ ሲያቀብሉኝ “ስማው ብየ እንጅ ፣ እውነት እንኳ ሆኖ ወንበር ቢቀያየር ምን ዋጋ አለው፣ ለፖለቲካቸው የሚጠቅማቸውን እንጅ ለስደተኛው የሚፈይደውን አይልኩልን!” ነበር ያሉኝ … ” ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም !” እንዲሉ …

የሚፈለገው ሁሉ  ይሆናል … የሚያቆመው የለም! ለሁሉም አንድየ የሚበጀንን ይስጠን፣ ከሁሉም በላይ ለሃገራችን ምድር አብቅቶ በሰላም በፍቅርና በህብረት የምንኖርባት ሃገር፣ መድልኦ የማያውቅ፣ ሃገርና ህዝቡን የሚወድና ለዜጎቹ መብት የሚቆረቆር መንግስት ይሰጠን …ትናንት የሚፈለገው ሁሉ  ይሆናል… የሚያቆመው የለም ብለን ነበር የተለያየነው  ! አዎ  የሚፈለገው ሁኗል ፣ ይሆናል … የሚያቆመው የለም!…

“ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይሾማል፣ የኢህአዴግ የድርጅት አባላትና ካድሬዎች ተጽዕኖ ፈጥረው በተናጠልና ተሰብስበው ያሽሩታል ፣ እንዲህ ተጉዘን የት እንደርስ ይሆን? ”  ነበር ያሉኝ አንድ አልረጋ ያለውን የጅዳ ቆንስል ሹም ሽር ያስገረማቸው እህት …

እስኪ ቸር ያሰማን

ነቢዩ ሲራክ

Filed Under: Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. temesgen mera says

    February 14, 2014 02:11 pm at 2:11 pm

    I would like to say thank you ! Because it true&true

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule